Tuesday, September 9, 2014

ለከተማ ባቡር የሚያገለግሉ የኮሙዩኒኬሽን መሣሪያዎች ጥራት በአማካሪ ድርጅቱና በኢንሳ ተመረመሩ

የአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ፕሮጀክት ሥራ ሲጀምር አገልግሎት ላይ የሚውሉ የኮሙዩኒኬሽንና የሲግናሊንግ መሣሪያዎች የምርት ጥራት ደረጃ፣ ከአማካሪ ድርጅቱና ከሌሎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በተወጣጡ ባለሙያዎች ምርመራ ተካሄደባቸው፡፡
ከመረጃ መረብና ደኅንነት ኤጀንሲና ከኢትዮ ቴሌኮም የባቡር መስመር ዝርጋታውን ኮንትራት የወሰደው አማካሪ ድርጅት ስዌድሮድ የተወጣጡ ባለሙያዎች፣ የኮሙዩኒኬሽን መሣሪያዎቹ የሚመረቱበት ቻይና በመሄድ የጥራት ደረጃቸውን በመመርመር ጥራታቸውን ማረጋገጣቸውን፣ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመረጃ መረብና ደኅንነት ኤጀንሲ የኮሙዩኒኬሽን መሣሪያዎች ደኅንነትና  የጥራት ደረጃ የመመርመር ኃላፊነት የወሰደው፣ መሣሪያዎቹ ከአገር ደኅንነት አንፃር ብቁ መሆናቸውን ለመፈተሽ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የኮሙዩኒኬሽን መሣሪያዎችን ለማምረት አጠቃላይ የባቡር ሥራ ኮንትራቱን የወሰደው የቻይናው ሲአርኢሲሲ የመረጠው ሁዋዌ የቴሌኮም ኩባንያ ነው፡፡
የባቡር ሥራ ኮንትራቱ የኢንጂነሪንግ፣ የግዢና ኮንስትራክሽንን አጠቃሎ 475 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽንና የሲግናሊንግ መሣሪያዎችን እንዲያመርቱ በተመረጡ ኩባንያዎች የአመራረጥ ሒደት ውስጥ ጣልቃ እንደማይገባ ታውቋል፡፡
የኮሙዩኒኬሽን መሣሪያዎቹ የሚያገለግሉት ባቡሩ ከአንድ ጣቢያ ተነስቶ ወደ ሌላ ጣቢያ በሚጓዝበት ወቅት ያሉ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር፣ በአንድ ጣቢያ ያለውን የትራንስፖርት ፍላጎት በመመልከት ባቡር ለመመደብ፣ ባቡሩ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች ሙሉ እንቅስቃሴን የሚያሳዩ ካሜራዎችን ለመትከል ነው፡፡
በቁጥጥር ማዕከልና በባቡር እንቅስቃሴ መካከል የሚኖር ገመድ አልባ የመረጃ ልውውጥ የሚደረገው በእነዚህ የኮሙዩኒኬሽን መሣሪያዎች መሆኑ ታውቋል፡፡
የሲግናሊንግ መሣሪያዎችን እንዲያመርት የተመረጠው ካስኮ የተባለ የቻይና ኩባንያ ሲሆን፣ መሣሪያዎቹ የሚያገለግሉት ባቡሩና ተሽከርካሪ መኪኖች በሚገናኙባቸው አካባቢዎች ባቡሩ ቅድሚያ እንዲያገኝ መልዕክት እንዲያስተላልፍ እንደሆነ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡
የተመረቱ ምርቶች በፍጥነት ወደ አገር ውስጥ መግባት አለባቸው ተብሎ በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት፣ ምርቶቹ በአሁኑ ወቅት በመጓጓዝ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የባቡር ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት 75 በመቶ የተጠናቀቀ መሆኑን፣ ቀሪው 25 በመቶ የኮንትራቱ ጊዜ በሚጠናቀቅበት ቀሪዎቹ አምስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኮርፖሬሽኑ ገልጿል፡፡
አንዳንድ ምንጮች ፕሮጀክቱ በተባለው ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደማይገመት እየገለጹ ቢሆንም፣ ኮርፖሬሽኑ ግን በተባለው ጊዜ ለማጠናቀቅ 24 ሰዓት እየተሠራ መሆኑንና እስካሁንም ከኮንትራክተሩ የቀረበለት የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ እንደሌለ  አስታውቋል፡፡

The Zagwe Dynasty

Medhani Alem Church, one of the twelve rock-hewn churches in Lablibela.
Courtesy United Nations Educational, Science, and Cultural Organization
In response to Islamic expansion in the Red Sea area and the loss of their seaborne commercial network, the Aksumites turned their attention to the colonizing of the northern Ethiopian highlands. The Agew peoples, divided into a number of groups, inhabited the central and northern highlands, and it was these peoples who came increasingly under Aksumite influence. In all probability, this process of acculturation had been going on since the first migrants from Southwest Arabia settled in the highlands, but it seems to have received new impetus with the decline of Aksum's overseas trade and consequent dependence upon solely African resources. As early as the mid-seventh century, the old capital at Aksum had been abandoned; thereafter, it served only as a religious center and as a place of coronation for a succession of kings who traced their lineage to Aksum. By then, Aksumite cultural, political, and religious influence had been established south of Tigray in such Agew districts as Lasta, Wag, Angot, and, eventually, Amhara.
This southward expansion continued over the next several centuries. The favored technique involved the establishment of military colonies, which served as core populations from which Aksumite culture, Semitic language, and Christianity spread to the surrounding Agew population. By the tenth century, a post-Aksumite Christian kingdom had emerged that controlled the central northern highlands from modern Eritrea to Shewa and the coast from old Adulis to Zeila in present-day Somalia, territory considerably larger than the Aksumites had governed. Military colonies were also established farther afield among the Sidama people of the central highlands. These settlers may have been the forerunners of such Semitic-speaking groups as the Argobba, Gafat (extinct), Gurage, and Hareri, although independent settlement of Semitic speakers from Southwest Arabia is also possible. During the eleventh and twelfth centuries, the Shewan region was the scene of renewed Christian expansion, carried out, it appears, by one of the more recently Semiticized peoples--the Amhara.
About 1137 a new dynasty came to power in the Christian highlands. Known as the Zagwe and based in the Agew district of Lasta, it developed naturally out of the long cultural and political contact between Cushitic- and Semitic-speaking peoples in the northern highlands. Staunch Christians, the Zagwe devoted themselves to the construction of new churches and monasteries. These were often modeled after Christian religious edifices in the Holy Land, a locale the Zagwe and their subjects held in special esteem. Patrons of literature and the arts in the service of Christianity, the Zagwe kings were responsible, among other things, for the great churches carved into the rock in and around their capital at Adefa. In time, Adefa became known as Lalibela, the name of the Zagwe king to whose reign the Adefa churches' construction has been attributed.
By the time of the Zagwe, the Ethiopian church was showing the effects of long centuries of isolation from the larger Christian and Orthodox worlds. After the seventh century, when Egypt succumbed to the Arab conquest, the highlanders' sole contact with outside Christianity was with the Coptic Church of Egypt, which periodically supplied a patriarch, or abun, upon royal request. During the long period from the seventh to the twelfth century, the Ethiopian Orthodox Church came to place strong emphasis upon the Old Testament and on the Judaic roots of the church. Christianity in Ethiopia became imbued with Old Testament belief and practice in many ways, which differentiated it not only from European Christianity but also from the faith of other Monophysites, such as the Copts. Under the Zagwe, the highlanders maintained regular contact with the Egyptians. Also, by then the Ethiopian church had demonstrated that it was not a proselytizing religion but rather one that by and large restricted its attention to already converted areas of the highlands. Not until the fourteenth and fifteenth centuries did the church demonstrate real interest in proselytizing among nonbelievers, and then it did so via a reinvigorated monastic movement.
Data as of 1991.

የቻይና ኩባንያዎች አዲስ ግዙፍ ፕሮጀክት ይረከባሉ

ሁለት የቻይና ኩባንያዎች፣ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ግንባታ ፕሮጀክት ሊሰጣቸው ነው፡፡ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቱ በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሸካ ተራሮች ተነስቶ ወደ ባሮ በሚፈሰውና ገባ ተብሎ በሚጠራው ወንዝ ላይ የሚካሄድ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በዚህ ሳምንት ሰኞ ጳጉሜን 3 ቀን 2006 ዓ.ም. የሚሰጣቸው ሁለቱ የቻይና ኩባንያዎች ኃይድሮ ቻይናና ቻይና ገዞባ ግሩፕ ናቸው፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች በተለይ ኃይድሮ ቻይና በገናሌ፣ ዳዋ፣ ጨሞጋ ያዳና ለፊንጫ በአመርቲነሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ አፈጻጻማቸው ደካማ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኩባንያዎቹ እንዲያሻሽሉ በተለያዩ ጊዜያት ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ገዞባ ግሩፕ የገናሌ ዳዋ ቁጥር ሦስት ኃይል ማመንጫ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ፕሮጀክት በ2007 በጀት ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ቢታቀድም፣ የኩባንያው የሥራ አፈጻጸም 56 በመቶ ብቻ በመሆኑ በሁለት ዓመት ይዘገያል ተብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ ኩባንያ ፊንጫ አመርቲነሽ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክትን የገነባ ሲሆን፣ የማረሚያ ሥራዎችን እንዲያካሂድና ፕሮጀክቱን እንዲያስረክብ ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል፡፡ ነገር ግን እስካሁን ማረሚያዎቹን አከናውኖ ፕሮጀክቱን እንዳላስረከበ ታውቋል፡፡
ነገር ግን የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ይህንን አይቀበሉትም፡፡ አቶ ዓለማየሁ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እነዚህ ኩባንያዎች ይህ ሥራ እንዳይሰጣቸው የሚያደርግ የአፈጻጸም ችግር የለባቸውም፡፡ ‹‹የገናሌ ዳዋ ፕሮጀክት ትልቅ ተራራ መናድን ይጠይቃል፡፡ አፈጻጸማቸውም 56 በመቶ ሳይሆን 60 በመቶ ነው፡፡ የአመርቲነሽም ቢሆን ሥራ እንዳይሰጥ የሚያደርግ አይደለም፤›› ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
በሌላ በኩልም ‹‹የጨሞጋ ያዳ ፕሮጀክት የኩባንያው ችግር አይደለም፤›› በማለት የተናገሩት አቶ ዓለማየሁ፣ ፕሮጀክቱ መካሄድ ያልቻለው በፋይናንስ ችግር ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ‹‹ኩባንያዎቹ ብቁ አይደሉም የሚያስብል ደረጃ ላይ አይደሉም፤›› በማለት አቶ ዓለማየሁ በኩባንያዎቹ ላይ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ኃይድሮ ቻይና ደግሞ ከሰባት ዓመት በፊት አማራ ክልል ደብረ ማርቆስ አካባቢ የጨሞጋ ግየዳ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ለመገንባት ውል ተፈራርሟል፡፡ ነገር ግን ፋይናንስ አልተለቀቀም በሚል ምክንያት ሥራውን እንዳልጀመረና ድርጅቱ ሥራውን መልክ እንዲያሲዝ ሲጠየቅ መሰንበቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ምንጮች እነዚህ ችግሮች ባሉበት ሁኔታ ሥራው ለእነዚህ ኩባንያዎች እንዴት ሊሰጥ ይችላል? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡
እነዚህ ኩባንያዎች በገባ ወንዝ ላይ የሚያካሂዱትን ፕሮጀክት የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ከሆኑት ሱር ኮንስትራክሽንና የኦሮሚያ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ጋር በእሽሙር ግንባር (ጆይንት ቬንቸር) እንዲያካሂዱ መወሰኑን የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የገባ ወንዝ ከጂማ ከተማ፣ ወደ ሸካ ዞን ዋና ከተማ ማሻ በሚወስደው መንገድ የጨዋቃ ሻይ ልማት እርሻ ከመድረሱ በፊት የሚገኝ ነው፡፡ በዚህ ወንዝ ላይ የሚካሄደው ግንባታ በአገር ውስጥ ኩባንያዎች እንዲካሄድ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም፣ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት እንዲደረግ ማስገደዱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በዚህ መሠረት ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት የተቀላቀሉት ሁለቱ የቻይና ኩባንያዎች፣ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከአገራቸው እንደሚያመጡ በመግለጽ ድርድር በማድረጋቸው የመንግሥትን ይሁንታ አግኝተዋል፡፡ አቶ ዓለማየሁ እንደገለጹት ስምምነቱ በዚህ ሳምንት ሰኞ ጳጉሜን 3 ቀን 2006 ዓ.ም. ይፈረማል፡፡
ለዚህ ፕሮጀክት የሚያስፈልገው ከቻይና ኤግዚም ባንክ ይገኛል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ይህ ገንዘብ መገኘቱ እንደተረጋገጠ፣ አራቱ ኩባንያዎች ወደ ግንባታ ይገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከወንዙ የሚመነጨው ኤሌክትሪክ ኃይል በሚቀጥለው የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንደሚካተት ተገልጿል፡፡    

History

Emperor Yohannes IV (1872-1889)

Following Emperor Tewodros's death, a struggle for succession took place between Tekle Giorgis and his brother-in-law, Dejezmach Kassa of Tigray. In 1872, Dejezmach Kassa of Tigray defeated Tekle Giorgis (1868 -1872) and was crowned under the name Yohannes IV. He established Mekele as his capital when he relocated his power base from Debra Berhane to Mekele in 1881. Yohannes was a committed Christian, nationalist, diplomatic, and a great military leader.
Yohannes continued the unity of Ethiopia started by Tewodros but Prince Menelik of Shewa (who was imprisoned by Tewodros for refusing to submit to him) and the British undermined his ambitions. The British let the Egyptians control the source of Nile, Lake Tana, and they occupied Gundet, Gura and Bogos regions. They betrayed Yohannes who was an ally of the British during the campaign against Tewodros at the Battle of Metema, in 1869. Even though Yohannes allowed Menelik back to rule Shewa after 10 years imprisonment, Menelik continued to play internal politics by seizing Wollo and putting Mohammed Ali as Governor while Yohannes fought Foreign powers.
Emperor Yohannes was determined to solve the problems Ethiopia faced on all fronts. Yohannes defeated the Egyptians at Battle of Gundet and Gura in 1875/6. He contacted Menelik to try to resolve and settled diplomatically their differences and signed an agreement called the Lache agreement of 1878, recognising Yohannes as Emperor and Menelik as Prince of Shewa.
Yohannes then turned his attention to negotiating with the British and Egyptians to recognise Ethiopia as a sovereign state and independent country. Yohannes ambitions were helped when the Mahdist war broke out in Sudan in 1882. Britain had troops stationed there and Britain needed Ethiopia's assistance to rescue its troops. In 1884 the Treaty of Adwa was signed between Ethiopia and Britain, which fulfilled Yohannes demands such as the return of Bogos which was occupied by the Egyptians and the right to import weapons and goods. In return Britain would control the Port of Massawa. After a year, Britain tore up the treaty and handed the Port of Massawa to Italy, which became a major threat to Ethiopian sovereignty.
In 1887, Italy occupied Saati and Dogali. Yohannes fought the Italians at Dogali won the battle and then went on to liberate Saati. During that time, Yohannes received news of the Mahdist invasions of Metema and Gonder and the rise of Menelik against Yohannes. This forced him to prioritise the danger facing Ethiopia and deciding to leave the Italian occupation of Saati. Yohannes marched on Shewa to fight Menelik. Menelik heard of Yohannes's intention and sent a messenger disguised as a monk to meet Yohannes before he reached Shewa. The messenger told Yohannes about his dream not to attack Menelik and instead guided him to fight the Mahdist. Yohannes was a deeply religious man and believed the messenger, which worked well for Menelik. Yohannes and his troops went to defend the threat posed by the Mahdist and headed to Metema, where the Mahdist troops were stationed. In March 1889, Yohannes defeated the Mahdist at the Battle of Metema but he was fatally wounded and died from his wounds.
The death of Yohannes sent a shock wave among Tigrayans. Yohannes' officials asked Ras Mengesha, the son of Yohannes IV, to claim the throne but the power struggle between the relatives of Emperor Yohannes intensified as they refused to recognise Ras Mengesha as Yohannes's heir.
Ras Mengesha's rival and nephew Debab Araya entered the fray to be heir but some Tigrayan nobles wanted Gugsa Araya to take the throne. However, Ras Alula who was a powerful warrior and known for his loyalty to Emperor Yohannes supported Ras Mengesha's claim to the throne and fought bitterly against Debab's and Gugsa's claim. Even though Ras Alula supported Ras Mengesha's claim to the throne Ras Mengesha did not try to take firm measures to curb the feud against him.
Eventually, Menelik of Shewa took the throne and became Emperor. After this event many Tigrayans never forgave Ras Mengesha for his failure to keep the throne in Tigray and allowing Menelik through the back door to be emperor. This was particularly given the fact that Menelik had played a major role in undermining Yohannes efforts to combat against foreign invaders, reunite and modernise the country.

References

  • Roderick Grierson and Stuart Munro-Hay, The Ark of the Covenant, 2000, published by Phoenix, London, UK, ISBN 0753810107
  • Stuart Munro-Hay, Ethiopia, The Unknown Land a Cultural and Historical Guide, 2002, published by I.B. Tauris and Co. Ltd., London and New York, ISBN 1 86064 7448
  • Jenny Hammond, Fire From The Ashes, A Chronicle of the Revolution in Tigray, Ethiopia, 1975-1991, 1999, published by The Read Sea Press, Inc., ISBN 1 56902 0868
  • Philip Briggs, Ethiopia, The Bradt Travel Guide, Third Edition, 2002, published by Bradt Travel Guides Ltd, England, UK, ISBN 1 84162 0351
  • Binyam Kebede (2002). http://www.ethiopiafirst.com (4ladies.jpg, Afar-lady.jpg, Afar-girl.jpg, lady-artful-lips.jpg, Man-face-art.jpg, Man-face-art2.jpg, Somal-lady.jpg, Debra-Damo.jpg, Buitiful-girls.jpg, lady-face-art.jpg, man-hair-style.jpg, yeha.jpg, harar.jpg,). Many thanks to Binyam Kebede for his permission to copy and use these pictures from his website.
  • Federal Democratic Republic of Ethiopia, Office of Population and Housing Census Commission Central Statistical Authority, November 1998, Addis Ababa
  • Edward Ullendorff, Ethiopia and The Bible, The Schweich Lectures, The British Academy, Published by The Oxford University Press, first published 1968, Reprinted 1989, 1992, 1997, Oxford University Press, Great Clarendon Street, Oxford OX2 6DP, United Kingdom, ISBN 0-19-726076-4
  • Mr. Solomon Kibriye (2003). Imperial Ethiopia Homepage, http://www.angelfire.com/ny/ethiocrown. Many thanks to Mr. Solomon Kibriye for the contribution and comments he has made to this website.

ክረምት አልፎ በጋ መስከረም ሲጠባ…

እንዴት ሰነበታችሁሳ!
እንኳን ለአዲስ ዓመት ዋዜማ አደረሳችሁማ!
ፊታችን ሳይጨፈግግ፣ ልባችን በስጋት ሳይነጥር፣ ስሜታችን የነሀሴ ሰማይ ሳይመስል… እንድንቀበለው ያድርግልንማ!
ስሙኝማ…እንግዲህ ጨዋታም አይደል፣ አንዳንዴ ግራ የሚገባችሁ ነገር አለ፡፡ ‘እንደ ሌላው ዓለም ለመሆን’ እንደ ገናና አዲስ ዓመት የመሳሰሉ በዓላትን “ለምን ወደ እነሱ አቆጣጠር አንለውጥም!” የሚሉ ‘ስልጣኔ እግር ተወርች የጠፈራቸው’ ሰዎች ገጥመዋችሁ አያውቁም! ይሄ የፈረደበት ገና ጭራውን ከቀንዱ ለይተን ማየት ያቃተን ግሎባላይዜሽን የሚሉት ነገር… አለ አይደል… ብዙዎቻችንን የሆንን ‘በቀደዱልን ቦይ እንድንፈስ’ እያደረጉን ነው፡፡
በአምባሰል ምት ላይ ቅልጥ ያለ ራፕ ተጨምሮ “ጊዜው የግሎባላይዜሽን ነው…” የሚባል ‘ብሮፌሰሮች’ እንኳን ያልደረሱባት ‘እውቀት’ አለችላችሁ፡፡ የ‘ፈረንጅን ጆሮ’ ይድፈንልንማ! ልጄ… ግሎባላይዜሽን የሚሉት ነገር እንዲሁ “ጊዜው የግሎባላይዜሽን ነው…” እየተባለ የሚታለፍ አይደለም፡፡
ስሙኝማ…እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ… ምን ያህል ‘ከጨዋታ ውጪ’ እንደሆንን እኮ በየቀኑ በዜናዎች ላይ እንሰማለን፡፡ አንድ የሆነ ‘እነሱ የማይመቻቸው’ ነገር ሲፈጠር ሲኤንኤን ቢቢሲ ምናምን ነገሩ “ዓለም አቀፉን ህብረተሰብ…” (International community) እንዳስቆጣ ይናገራሉ፡፡ ‘የተቆጡት’ እኮ የሁለት ወይም የሦስት ጡንቸኛ አገሮች መሪዎች ናቸው! እናላችሁ…ግሎባላይዜሽን ምናምንም እንደዛው ነው!
እኔ የምለው…እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ…ቀደም ባለው ጊዜ አዲስ ዓመት ሲመጣ ቃል የምንገባቸው መአት ነገሮች ነበሩ፡፡ “ማጨስ አቆማለሁ…”  “መጠጥ አቆማለሁ…” “ውጪ ማምሸት አቆማለሁ...” ምናምን ይባል ነበር፡፡
ደግሞላችሁ…“ትምህርቴን እገፋለሁ…” “መሥሪያ ቤት እቀይራለሁ…” “የግል ሥራ እጀምራለሁ…” ምናምን የሚባሉ ነገሮች ነበሩ፡፡ ዘንድሮ ብዙ ሰው እንዲህ ሲል አትሰሙም፡፡ የምር ጊዜ ተለውጧል፡፡ ልጄ…የሰፈረብን ዛር እንዲህ በቀላሉ የሚለቀን አይመስልም፡፡
የምር ግን… በዚህ በአዲስ ዓመት ዋዜማ…አለ አይደል… ነገሮችን ሳንቀባባ፣ በ‘ትክክለኛ ቀለማቸው’ አይተን ለመገንዘብ ፈቃደኛ ካልሆንን “የሚወጣው አሮጌ ዓመት እንዴት ነበር?” ሲባል ያቺ የለመድናትን “ከሚቀጥለው ይሻላል…” ምላሽ እየሰጠን እንዲሁ የቀን መቁጠሪያ ዲዛይን ስንለውጥ ልንኖር ነው፡፡
ስሙኝማ…ይሄን ሰሞን ያው ‘ዳያስፖራዎች’ ከተማችንን ‘በቁጥጥር ስር እንድሚያውሏት’ (‘እንደሚያሳድሯት’ ልል ፈልጌ ይሉኝታ ይዞኝ መሆን አለበት! ቂ…ቂ…ቂ…) እንኳንስ ደህና መጣችሁ!
እኔ የምለው…እንግዲህ ጨዋታም አይደል…ብዙ ጊዜ በተለይ በውጪ ሀገራት ጥቂት ዓመታት ከረም ብለው የመጡ አንዳንድ ሰዎች…አለ አይደል… “ክትፎ ቤቱ ግፊያ ነው፣ ውስኪ ቤቱ ግፊያ ነው፣ ሬስቱራንቱ ሁሉ ግፊያ ነው…ሰዉ ተቸግሯል የምትሉት ምንድነው?” ምናምን አይነት ነገር ይላሉ፡፡ ወዳጆቼ…የኢትዮዽያ ህዝብ ጥቂት አሥር ሺዎች አለመሆኑን ልብ ይባልልንማ! የመጠጥ ቤቶች መሙላት ‘የምቾት ምልክት’ ከመሰላችሁ… በየቀኑ ጢም ብለው የሚሞሉትን የየመንደሮቹ ጠላና ጠጅ ቤቶችንም በእኛ ወጪ ለማሳየት ፈቃደኛ ነን፡፡ (እንትና…ያ ‘ኤክስፐርመንት’ እንዴት ሆነ? ጠጃችን በቮድካ ተበለጠ እንዴ!)
‘ሚዛኑን’ አታበላሹብንማ!
ስሙኝማ…እንግዲህ አዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ አይደለን! የወጣቱ ትውልድ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አያሳስባችሁም! ምንም እንኳን ‘በትክክለኛው ሀዲድ’ ላይ ያሉ በርካታ ወጣቶች ቢኖሩም፣ ደግሞላችሁ… ከእነሱ በብዙ ቁጥር የላቁ ከሀዲዱ ሲወጡ ስታዩ የምርም… “ወዴት እየሄድን…” እንደሆነ ግራ ይገባችኋል፡፡ በአንድ በኩል በርካታ መሥሪያ ቤቶች በወጣቶች ተሞልተው ስታዩ (ስለ ‘አገልግሎት ጥራት’ እያወራን አይደለም!) የሆነ ተስፋ ነገር ይታያችኋል፡፡ በተለይም የተለያዩት የስነ ጥበብና የኪነ ጥበብ ዘርፎች በወጣቶች ፊት አውራሪነት ሲካሄዱ ስታዩ ተስፋ ነገር ይታያችኋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች መአት ናቸው፡፡ ወጣቶች ራሳቸውን መሆን ትተው ሌላ ‘ማንነት’ ለመያዝ ሲሞክሩ ስታዩና ከማንነት ‘ግራ መጋባት’ ጋር የተያያዙ ቀውሶች ውሎ አድሮ የሚያስከትሏቸውን የቀጥታም ይሁን የጎንዮሸ አበሳዎች ስታስቡ… እንደ ተስፋ መቁረጥ ይቃታችኋል፡፡ እነኚህ ወጣቶች ነገ በግድ የራሳችን ካላደረግነው ያሉት ‘ማንነት’ “ለአሁኑ አልተሳካላችሁም…” አይነት ነገር ሲገጥማቸው፣ ያኔ ሉሲፈር ሙሉ ለሙሉ የሚሰፈርበት ‘ነጻ ሰው’ አገኘ ማለት ነው! እናማ…የአገሪቱን ‘ማስተር ኪይ’ ይቀበላል የምንለው ወጣት፤ “እውን ያንን ኃላፊነት የመቀበል አቅም ይኖረው ይሆን!” ብላችሁ ስጋትና ተስፋ መቁረጥ ቢጤ ይቃጣችኋል፡፡
እናላችሁ… እያሳሳቀ እንደሚወስደው ወንዝ፣ ወጣቱን ትውልድ ‘እያሳሳቁ የሚወስዱት’ ነገሮች በዝተዋል፡፡ ስሙኝማ…ይሄ ወጣቱን ትውልድ የማዳን ነገር ብዙ ጊዜ በየሚዲያው እየተነሳ ምንም ተጨባጭ ነገር ሲደረግ አለማየታችን አይገርማችሁም! ኮሚክ እኮ ነው…የሚመለከተን ሁሉ…አለ አይደል…“የራሳቸው ጉዳይ፣ እኛ በአንቀልባ ልናዝንላቸው ነበር!” አይነት ነገር የምንል ይመስላል፡፡
ምን ግርም ይልሀል አትሉኝም…በየቦታው ያሉት ወጣት ማዕከላት በጠረጴዛ ኳስና በ‘ጆተኒ’ ተሞልተው ስታዩዋቸው “እውን በዚህ ብቻ ነው የወጣቱ አእምሮ የሚጐለምሰው!” ብላችሁ ስጋት ቢጤ ይቃጣችኋል፡፡
መጪው ዓመት ወጣቱን ትውልድ ‘ከሀዲዱ የሚያወጡ’ ነገሮችን ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የሚጠፉበት አለበለዛ በእጅጉ የሚቀንሱበት ይሁንልንማ!
መጪው ዓመት… አለ አይደል… “እንደው አምላኬ ምን ታደርገን ይሆን?” የምንለው አሁን፣ አሁን እየባሰ የመጣ ስጋታችን ተቀርፎ… አለ አይደል…ደግ፣ ደግ ነገሮችን የምናወራበት፣ በሥራችንም፣ በኑሯችንም “እንኳን ደስ ያለህ!” የምንባባልባቸው ነገሮች የሚበዙበት ዓመት ይሁንልንማ!
አንዱ ‘የፈረንጅ ስታንድ አፕ ኮሜዲያን’ ምን አለ መሰላችሁ…“ልጅ ማሳደግ በከፊል ደስታ፣ በከፊል ደፈጣ ውጊያ ነው፡፡” አሪፍ አባባል አይደል! መጪው ዓመት ለሀገራችን ወላጆች ልጅ ማሳደግ ደፈጣ ውጊያ ሳይሆን ደስታ የሚሆንበት ዓመት ይሁንልንማ!
እብሪት ከእነ ጦስ ጥንቡሳሱ ውልቅ ብሎ ይጥፋልንማ!
ኮሚክ ነገር እኮ ነው…ብዙዎቻችን በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ‘ወፍረን’… አለ አይደል… “መንገዱን ልቀቁልኝ!” አይነት ነገር ይሞክረናል፡፡ ወይ በስልጣን፣ ወይ በወንበር፣ ወይ ‘በኔትወርክ’  (ቂ…ቂ…ቂ…) ‘እንወፍር’ና “ነጋሪት ጎስሙልኝ!” ለማለት ይቃጣናል፡፡
አባቶቻቸን ‘አሞሌ ሲወፍር ወንዝ አውርዳችሁ እጠቡኝ ይላል…’ የሚሏት አባባል አለቻቸው፡፡ እናማ…ምን መሰላችሁ… ‘እንደ ወፈረ’ አሞሌ… “ወንዝ አውርዳችሁ እጠቡኝ…” የምንል በዝተናል፡፡ ‘እብሪታችን’ እይታችንን ጋርዶናል፡፡ ገንዘብና ስልጣን የሁሉ ነገር ‘የበርሊን ግንባችን’ የሚመስለን በዝተናል፡፡
መጪው አዲስ ዓመት… “ወንዝ አውርዳችሁ እጠቡኝ!” ማለትን የምንቀንስበትና አሞሌ ሆዬ፤ “ወንዝ አውርዳችሁ እጠቡኝ!” ያለ ቀን የሁሉም ነገር ‘አርማጌዶን’ እንደሚሆን የምንገነዘብበት ዓመት ይሁንልንማ!
ከልባችን…
ክረምት አልፎ በጋ መስከረም ሲጠባ
አሮጌ ዓመት አልፎ አዲሱ ሲገባ
በአበቦች መአዛ ረክቷል ልባችሁ
ህዝቦች ሁሉ በጣም እንኳን ደስ አላችሁ፤
ብለን በጋራ የምንዘምርበትን ጊዜ ያቅርበውማ!
መልካም የዋዜማ ቀናት፣ መልካም የአዲስ ዓመት መግቢያ ይሁንልንማ!
ደህና ሰንበቱልኝማ!

“ህይወት በመንግስቱ ቤተ-መንግስት ቁጥር 2” ለንባብ በቃ

በወታደር እሸቱ ወንድሙ የተፃፈው “ህይወት በመንግስቱ ቤተ መንግስት ቁጥር 2” መፅሃፍ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ የመፅሃፉ ደራሲ ቀድሞ የልዩ ሃይል አባል የነበረ መሆኑን በመፅሃፉ ሽፋን ላይ የገለፀ ሲሆን መፅሃፉም የጓድ መንግስቱ ኃይለማርያምና የአስተዳደራቸውን ምስጢራት ይበረብራል ተብሏል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም በሳተመው “ቁጥር 1” መፅሃፉ ውስጥ የተለያዩ ግለሰቦችን ስም መጥቀሱ ለዛቻና ማስፈራሪያ እንደዳረገው ጠቁሞ በሁለተኛው መፅሃፉ የግለሰቦችን ስም ከመጥቀስ መቆጠቡን አስታውቋል፡፡
መፅሃፉ በ220 ገፆች የተቀነበበ  ሲሆን በ50.66 ብር ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ ደራሲው ወታደር እሸቱ ወንድሙ፤ “ህይወት በመንግስቱ ቤተ መንግስት ቁጥር 1” መፅሃፍን ጨምሮ “የሌ/ኮ መንግስቱ ያልተነገሩ ሚስጥሮች” የተሰኙ መፅሃፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ከአፍሪካ አነስተኛ ሙስና የተሰራባት አገር ናት ተባለ

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው አለማቀፍ ተቋም እ.ኤ.አ በ2013 በአለም ዙሪያ በሚገኙ 95 አገራት በሰራው ጥናት፣ ባለፈው አመት ከአፍሪካ አህጉር አነስተኛ ሙስና የተሰራባት አገር ኢትዮጵያ እንደሆነች ማስታወቁን የኬንያው ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ አልጀዚራ በበኩሉ ትናንት ባወጣው ዘገባ፣ በኢትዮጵያ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት ቅንጦት ነው ብሏል፡፡
የአገራትን ዜጎች አስተያየትና ሌሎች መስፈርቶችን በመጠቀም ባወጣቸው የሙስና መለኪያዎች በ6 በመቶ ነጥብ ያገኘችው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት አነስተኛ ሙስና ያለባት አገር እንደሆነች የገለጸው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል፣ ዴንማርክ፣ ፊላንድ፣ ጃፓንና አውስትራሊያም በተመሳሳይ ሁኔታ 1 በመቶ ነጥብ ይዘው በአለማችን አነስተኛ ሙስና ያለባቸው አገሮች መሆናቸውን በጥናቱ ማረጋገጡን ይፋ አድርጓል፡፡
በሙስና መለኪያዎች 84 በመቶ ውጤት ያገኘችው ሴራሊዮን በአለማችን ከፍተኛ ሙስና የሚፈጸምባት አገር እንደሆነች የገለጸው ተቋሙ፣ ላይቤሪያ፣ የመንና ኬንያ እንደሚከተሏት አስታውቋል፡፡
ከአፍሪካ ሁለተኛዋ አነስተኛ ሙስና ያለባት አገር ሩዋንዳ መሆኗን የገለጸው ተቋሙ፣ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አገራት መካከልም ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያና ሱዳን በቅደም ተከተል ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ደረጃ ይዘው እንደሚገኙ ተናግሯል፡፡
አልጀዚራ በበኩሉ ትናንት ለንባብ ባበቃው ዘገባው በኢትዮጵያ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት ቅንጦት እንደሆነ ገልጾ፣ ምንም እንኳን 52 በመቶ የአገሪቱ ህዝብ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የተሟላለት ቢሆንም፣ የውሃ መስመር ቤታቸው ድረስ የተዘረጋላቸው የአገሪቱ ዜጎች 10 በመቶ ያህሉ ብቻ እንደሆኑ አስረድቷል፡፡በአገሪቱ የገጠር አካባቢዎች ከሚኖሩት ዜጎች የንጹህ የመጠጥ ውሃ ቧንቧ መስመር የተዘረጋላቸው አንድ በመቶ ያህሉ ብቻ እንደሆኑም ገልጧል፡፡የአገሪቱ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ቢሆንም፣ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት አሁንም ድረስ በበቂ ሁኔታ አለመሟላቱንና ከፍተና ስራ መስራት እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

Egypt: Irrigation Minister Receives Invitation to Visit Ethiopian Dam

Water Resources and Irrigation Minister Hossam Moghazi said that he has received an official invitation from his Ethiopian counterpart Hailemariam Desalegn to visit Addis Ababa and the Renaissance Dam construction site by the mid of September.
He said that the visit comes within the framework of building confidence as agreed in the joint statement of the ministers of water affairs of Egypt, Ethiopia and Sudan at the 4th Tripartite Ministerial Meeting, which was held in Khartoum last week, comprising representatives from the three countries.
He said that the Ethiopian embassy in Cairo sent the invitation which carries a message of friendship and welcome.
He noted that the visit was scheduled for last week but has been post
poned to mid September.

Egypt: Foreign Ministry - President to Meet Ethiopian PM At UN Meeting

President Abdul Fattah Al-Sisi is due to meet with Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn on the sidelines of the United Nations meetings after two weeks, said Spokesman for the Foreign Ministry Ambassador Badr Abdul Atti said in a televised statement.
He said that Foreign Minister Sameh Shoukry discussed with the Ethiopian premier the Renaissance Dam crisis as well as the ties binding the two countries during his recent visit to Addis Ababa.
He added that Shoukry carried a message from President Al-Sisi to the Ethiopian top official urging him to press ahead with the joint cooperation and work in a way that maintains the interests of both sides in all fields including the Renaissance Dam.
He went on to say that the joint ministerial committee chaired by the foreign ministers of both countries will be activated soon.

Monday, September 8, 2014

በአዳዲስ የሙዚቃ አልበሞች የታጀበው አዲሱ አመት

ላለፉት ዓመታት የቅጂና ተዛማች መብቶች ጥሰት በፈጠረው ስጋት ተቀዛቅዞ የከረመው የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ዘንድሮ የተነቃቃ ይመስላል፡
ታዋቂ ድምፃውያን ለአዲሱ አመት አዳዲስ ነጠላ ዜማቸውንና አልበማቸውን አበርክተዋል፡፡ ይሄም ለሰሞኑ የአውዳመት ድባብ ተጨማሪ ድምቀት ሰጥቶታል፡፡
የአብነት አጎናፍር “አስታራቂ፣ የታምራት ደስታ “ከዛ ሰፈር”፣ የዮሴፍ ገብሬ “መቼ ነው” የሰለሞን ሃይለ “ውህብቶ”፣ የቤተልሔም ዳኛቸው “ሰው በአገሩ” እና የተስፋፅዮን ገ/መስቀል “ጀመረኒ” እንዲሁም የቴዎድሮ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) “ሰባ ደረጃ” ነጠላ ዜማም ለአዲስ ዓመት ከተበረከቱ የሙዚቃ ስራዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡
“ሙዚቃ እንደ በረዶ በቀዘቀዘበት ዘመን ደፍረውና መስዋዕትነት ከፍለው አዲስ ነገር ይዘው ስለመጡ አድናቆት ይገባቸዋል” ብለዋል በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የስራ ኃላፊ የሆኑና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የሙዚቃ ባለሙያ፡፡
በዚህ አመት ለአድማጭ ይበቃሉ ከተባሉት የሙዚቃ አልበሞች መካከል፣ የኤፍሬም ታምሩ አልበም የሚጠቀስ ሊሆን፣ የድምፃዊው ወላጅ እናት በሳምንቱ መጀመሪያ ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት አልበሙ ሳይለቀቅ ቀርቷል፡
የአብነት አጎናፍር “አስታራቂ”
ከሁለት ሳምንት በፊት ገበያ ላይ የዋለው አብነት አጎናፍር “አስታራቂ” አልበም 14 ዘፈኖች የተካተቱበት ሲሆን ካሙዙ ካሳ፣ ሚካኤል ሀይሉና አቤል ጳውሎስ አቀናብረውታል፡፡ ድምፃዊው ሶስተኛ ስራው በሆነው በዚህ አልበም አገራዊ፣ ማህበራዊ እና የፍቅር ጉዳዮችን የዳሰሳ ሲሆን ከአድማጮች በተገኘ አስተያየት፣ ከአብነት ስራዎች ውስጥ ስለአገር የዘፈናቸው “አያውቁንም”፣ “ለማን ብዬ”፣ “አስታራቂ” እና “የኔ ውዳሴ” የተሰኙት ይበልጥ ተወደዋል፡፡ በAB ሙዚቃና ፊልም ፕሮዳክሽን የታተመው “አስታራቂ” አልበም፤ በአርዲ ኢንተርቴይመንት እየተከፋፈለ ሲሆን የአዲሱ ዓመት አንዱ ገጸ በረከት ነው፡፡ አብነት ከአማርኛ ሙዚቃ በተጨማሪ ሱዳንኛ እንደሚጫወት የሚታወቅ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ “አያሌሌ” የተሰኘ የጉራጊኛ ዘፈን አካትቷል፡፡ ድምፃዊው በአብዛኛው ዘፈኖቹ ላይ በግጥምና በዜማ ድርሰት ተሳትፏል፡፡
የታምራት ደስታ “ከዛ ሰፈር”
ለአዲሱ ዓመት በገፀ-በረከትነት ከቀረቡት አልበሞች ውስጥ የታምራት ደስታ አራተኛ ስራ የሆነው “ከዛ ሰፈር” አንዱ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ለአድማጭ ጆሮ የደረሰው ይሄው አልበም፤ 14 ዘፈኖችን አካትቷል፡፡ ካሙዙ ካሳ፣ ሚካኤል ሃይሉ፣ ሚካኤል መለሰና ኪሩቤል ተስፋዬ በቅንብር የተሳተፉበት ይሄ ስራ፤ በግጥም እና ዜማ ጌትሽ ማሞ አማኑኤል ይልማ፣ መሰለ ጌታሁንና ኢዩኤል ብርሃኔን አሳትፏል፡፡ በናሆም ሪከርድስ አሳታሚና አከፋፋይነት ገበያ ላይ የዋለው የታምራት አልበም፤ በስፋት እየተደመጠ ሲሆን በተለይም “ሊጀማምረኝ ነው” “አዲስ አበባ”፣ “ማማዬ” እና የአልበሙ መጠሪያ የሆነው “ከዚያ ሰፈር” የተሰኙ ዘፈኖች የበለጠ እየተሰሙ እንደሚገኙ ከአድማጮች አስተያየት ለመረዳት ተችሏል፡፡
የቴዲ አፍሮ “ሰባ ደረጃ”
ከበደሌ ጋር አመቱን ሙሉ በሚዘልቅና “ወደ ፍቅር ጉዞ” በተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት ከአድናቂዎቹ ጋር ለመገናኘት የጀመረው ስራ የተሰናከለበት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፤ ከሁለት ሳምንታት በፊት የለቀቀው “ሰባ ደረጃ” የተሰኘ ነጠላ ዜማው በስፋት እየተደመጠ ሲሆን ማህበራዊ ድረ - ገፆችን በተለይም ፌስ ቡክን ተቆጣሮጥት ሰንብቷል፡፡ የቴዲ “ሰባ ደረጃ” ፒያሳ፣ ዶሮ ማነቂያ፣ ሰራተኛ ሰፈር፣ አራት ኪሎን፣ ታሪካዊ ክስተቶችንና አለባበሶችን ከፍቅር ጋር እያሰናሰለ ያነሳሳል፡፡ የቴዲ አፍሮ “ሰባ ደረጃ” ነጠላ ዜማ ሙሉ አልበምን የመወከል ያህል ተቀባይነት አግኝቶ በየምሽት ቤቱ፣ በየሆቴሉና በየሬስቶራንቱ በስፋት እየተደመጠ ያለ የአዲስ አመት የበዓል ድምቀት ሆኖ ቀጥሏል፡፡
የሰለሞን ሃይለ “ውህብቶ”
“ቆሪብኪለኩ” (ቆረብኩልሽ) በሚለው የመጀመሪያ አልበሙ በተለይም “ንኢባባ” በተሰኘው ዘፈኑ የሚታወቀው ወጣቱ የትግርይኛ ዘፋኝ ሰለሞን ሃይለም ከሳምንታት በፊት “ውህበቶ” የተሰኘ አልበም ለአድማጭ አቅርቧል፡፡ አልበሙ 12 ዘፈኖችን ያካተተ ሲሆን፣ ስለ ሃገር፣ ስለ ፍቅር ስለማህበራዊ ጉዳዮች ተነስተውበታል፡፡ ሙሉ ግጥምና ዜማው በራሱ በድምፃዊው የተሰራ ሲሆን፣ በቅንብሩ አብዛኛውን ዘፈኖች ተወልደ ገ/መድህን ሲሰራ፣ ሁለት ዘፈኖችን ዮናስ መሃሪ እና ደነቀው ኪሮስ፣ አንዱን ዘፈን ዘመን አለምሰገድ አቀናብረውታል፡፡ በስፋት እየተደመጠም ይገኛል፡፡
የዮሴፍ ገብሬ “መቼ ነው”
ድምፃዊና ጋዜጠኛ ዮሴፍ ገብሬም አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ “መቼ ነው” የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበሙን ከ10 ቀናት በፊት በገበያ ላይ አውሏል፡፡ ለዝግጅት 6 አመታትን የፈጀው ይሄው አልበም፤ በአገር፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በመተሳሰብ ላይ የሚያተኩር ሲሆን 7 አቀናባሪዎችና የተለያዩ የግጥምና ዜማ ደራሲዎች ተሳትፈውበታል፡፡ “መቼ ነው” የተሰኘው የአልበሙ መጠሪያ፣ “ክፉ አይንካብኝ” ሲል ስለ አገር የዘፈነው፣ “ፍቅር ነው ያገናኘኝ” እንዲሁም ስለአንድነትና መተባበር (በጉራጊኛ) የዘፈናቸው ይበልጥ ተወዳጅ እንደሆኑለት ከአድማጮች ያገኘነው አስተያየት ይጠቁማል፡፡ አልበሙ በተለያዩ የመዝናኛ ስፍራዎች በስፋት እየተደመጠ ይገኛል፡፡
የቤተልሔም “ሰው በአገሩ”
በ1996 ዓ.ም ለአድማጭ ባቀረበችው “ቅዳሜ ገበያ” የተሰኘ ባህላዊ ዜማዋ የምትታወቀው ድምፃዊት ቤተልሔም ዳኛቸው፣ ሰሞኑን “ሰው በአገሩ” የተሰኘ አዲስ አልበሟን ለአድማጭ አቅርባለች፡፡
ነዋሪነቷ በስዊዘርላንድ የሆነው ድምፃዊት ቤተልሔም ያቀረበችው አዲስ አልበም፤ 13 ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃዎች የተካተቱበት ነው፡፡ ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪና የድምፃዊቷ ባለቤት ዳዊት ጥላሁን ባቀናበረው በዚህ አልበም ውስጥ ራሱ ዳዊትና ቤተልሔም ጥላሁን በዜማና ግጥም ደራሲነት ተሳትፈዋል፡፡
የተስፋፅዮን “ጀመረኒ”
በባህላዊ የማሲንቆ አጨዋወቱ አድናቆት የተቸረው ድምጻዊ ተስፋፅዮን ገ/መስቀል ከሰሞኑ “ጀመረኒ” የተሰኘውንና ራሱን በማሲንቆ ያጀበበትን የትግርኛ ሙዚቃዎች ለአድማጭ አብቅቷል፡፡ ከዚህ ቀደም “ቆልዑ ገዛና” የተሰኘ አልበም አውጥቶ ተቀባይነትን ያገኘው ድምፃዊው፤ በ“ጀመረኒ” አልበሙ የሰርግን ጨምሮ በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 13 ሙዚቃዎችን አካትቷል፡፡ አልበሙን ዳአማት መልቲ ሚዲያ አሳትሞ እያከፋፈለው ሲሆን፣ ለአዲሱ ዓመት በተለይ በትግርኛ ዘፈን አድማጮች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
“አራዳ” ቪሲዲ ኮሌክሽን
በመስፍን ታምሬ ፕሮዲዩሰርነት የታተመውና 14 እውቅ ድምፃዊያን የተሳተፉበት “አራዳ” ባህላዊ እና ዘመናዊ ዘፈኖች በምስል (በቪዲዮ) የቀረቡበት ነው፡፡ የዚህ ቪሲዲ አዘጋጅ “ኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽን” ሲሆን “ፒያሳ ዘ አራዳ ኢንተርቴይመንት” አሳትሞ ከትናንት ጀምሮ እያከፋፈለው ይገኛል፡፡ በ“አራዳ” ኮሌክሽን ቪሲዲ ላይ ሸዋንዳኝ ሃይሉ፣ ብዙአየሁ ደምሴ፣ እመቤት ነጋሱሲ (ሰንዳበል)፣ ጃኪ ጎሲ፣ የኦሮምኛ ዘፋኙ አበበ ከፍኔና ቤተልሄም ዳኛቸውን ጨምሮ 14 ያህል ታዋቂ ድምፃዊያን ተሳትፈውበታል፡፡
“አራዳ” ብቸኛው ለአዲስ ዓመት የተዘጋጀ ቪሲዲ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የእንቁጣጣሽ ስጦታ! “ክላሲካል ሙዚቃን በልምድ መጫወት አይቻልም”

የኒውዮርክ ታይምስ መጽሔት “From Chopin to Ethiopia and Part way Back Again (“ከቾፐን እስከ ኢትዮጵያ እና ደርሶ መልስ”) በሚል ባስነበበው የሙዚቃ ቅኝት ስቲቭ ስሚዝ ስለግርማ ይፍራሸዋ ያሰፈረው በከፊል ይሄን ይመስላል፡-
“…በተነፃፃሪ ሲታይ፤ ስለክላሲካል ሙዚቃ በአፍሪካ፤ የሚያመላክቱ ጥቂት ማረጋገጫዎች ብቻ ይኑሩ እንጂ የምዕራቡ ክላሲካል ባህል በሌላው ዓለም ማለትም ከቬኔዝዌላ እስከ ቻይና እንደተንሰራፋው ሁሉ የአፍሪካንም ዙሪያ መለስ ማዳረሱ ገሀድ ነው፡፡ ለዚህ አስረጅ የሚሆነን የ45 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ፒያኒስትና ቀማሪ ግርማ ይፍራሸዋ በብሩክሉን “ኢሹ ፕሮጀክት ሩም” ቅዳሜ ምሽት ያቀረበው ምርጥ የፒያኖ ሥራ፤ እጅግ ብርቅ፣ ሥነ ውበታዊና ተምሳሌታዊ የክላሲካል ሙዚቃ መናኸሪያ መሆኑን የሚያሳይ ነው!
…. ግርማ “የኢትዮጵያዊያን በገና” ሊባል በሚችለው በክራር ነው የሙዚቃ ልጅነቱን የጀመረው፡፡ አዲስ አበባ ሙዚቃ ት/ቤት ሲገባ ከፒያኖ ጋር ተገናኘ፡፡ ከዚያ ነው በነቃ አዕምሮው በቡልጋሪያ የሶፊያ ስቴት ኮንሰርቫቶሪ መደበኛ ትምህርቱን ገፍቶ የተካነው…
“… ወደ ኢትዮጵያ በ1995 እ.ኤ.አ ከተመለሰ በኋላ ግርማ ደረጃውን የጠበቀ ክላሲካል ትርዒት ምን እንደሚመስል ደርዝ ያለው ግንዛቤ ማስጨበጥን ሥራዬ ብሎ ከመያያዙ ሌላ፤ አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎችን ፅፏል፡፡ ለነዚህ አዳዲስ የጥበብ ስራዎች መቀመሪያ ይሆነው ዘንድ የአውሮፓን የጥበብ መላ ከኢትዮጵያ ሙዚቃና ሥነ-ትውፊታዊ ዕሴት ጋር በማጋባት ተጠቅሟል፡፡....››

ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበው አዲሱ አልበሙ በአሜሪካ በቢልቦርድ ሰንጠረዥ 23ኛ ደረጃ አግኝቷል ታዋቂው ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ በቅርቡ በአሜሪካ ያስመረቀው “Love and peace” የተሰኘ አዲስ አልበሙ፤ በቢልቦርድ ሰንጠረዥ 23ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠለት ይናገራል፡፡ በአሜሪካ ያቀረበው ኮንሰርት እንደተወደደለት የገለፀው ፒያኒስቱ፤ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በአድናቆት የተሞላ ጽሑፍ እንዳወጣለት ጠቁሟል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤት ዕቁባይ ከግርማ ይፍራሸዋ ጋር ያደረገችው ቃለምልልስ እንዲህ ቀርቧል፡፡ ወደ ሙዚቃ እንዴት እንደገባ በመናገር ይጀምራል፡-

ሙዚቃ የጀመርኩት በልጅነቴ ክራር በመጫወት ነው፡፡ ክራር ስጫወት ነው ያደግሁት፡፡ ፡፡ሙዚቃን በሳይንሳዊ መንገድ ለማጥናት ደግሞ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በመግባት፤ ከባህል ክራር፣ ከዘመናዊ ደግሞ ፒያኖን ለአራት አመት ተማርኩ፡፡ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ትምህርቴን እንዳጠናቀቅሁ፣ በ1980 ስኮላርሺፕ አግኝቼ ወደ ቡልጋሪያ አቀናሁ፡፡
እዚያ ከሄድክ በኋላ ግን ችግር ገጠመህ…
ፒያኖ ለመማር አልሜ ቡልጋሪያ በሚገኝ የሙዚቃ አካዳሚ ለሁለት አመት ከተማርኩ በኋላ በወቅቱ በተፈጠረው የሶሻሊስት ካምፕ መፍረክረክና መፍረስ ሳቢያ የእኔና በሙዚቃ ትምህርት ቤቱ የነበሩ ሌሎች ተማሪዎቸ እጣ ፈንታ ስደት ሆነ፡፡ ሁሉም በየፊናው ሲበተን እኔ ጣሊያን ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ገባሁ፡፡ ለስድስት ወራት ያህል “ክርስቲያን ብራዘርስ” የተባሉ በጎ አድራጊዎች እየረዱኝ በካምፑ ተቀመጥኩ፡፡ ካምፑ ውስጥ ያሉ የተለያዩ አገር ስደተኞች በሞሉት ፎርም ላይ አሜሪካ ወይም ካናዳ መሄድ እንደሚፈልጉ ሲያሰፍሩ፣ እኔ ግን ትምህርቴ ለምን እንደተቋረጠ በመግለፅ የፒያኖ ትምህርቴን ቡልጋሪያ ሄጄ መቀጠል እንደምፈልግ ገለፅኩ፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቱም የኔን ጥያቄ ከሌሎች በመለየት ነገሮች ሲረጋጉ የትምህርት ክፍያውን እየከፈሉ ትምህርቴን እንድጨርስ ቡልጋሪያ መልሰው ላኩኝ፡፡ በአጠቃላይ ሰባት አመት የፈጀውን የፒያኖ ትምህርቴን አጠናቅቄ ማስተርሴን ካገኘሁ በኋላ ተመልሼ ጣሊያን ሄድኩ፡፡
ትምህርቴን እንድጨርስ የረዳኝ ድርጅት አሮጌ ፒያኖ ቢሰጠኝ እያልኩ እመኝ ነበር፡፡ ጣሊያን አገር በቆየሁበት ጊዜ ኮንሰርት ሰርቼ ስለነበር እሱን ተከትሎ ድርጅቱ አዲስ ፒያኖ በሽልማት ሰጠኝ፡፡ አሮጌ ቢሰጡኝ እያልኩ ስመኝ ፋብሪካ ድረስ ሄጄ መርጬ ባለፒያኖ ሆንኩ፡፡ ያ ለኔ ትልቅ ደስታ ነበር የፈጠረልኝ፡፡
ፒያኖዋ ግን ሌላ ስጋት ይዛ መጣች…
አዎ ፒያኖዋ በአውሮፕላን ከኔ ቀደም ብላ ነበር አዲስ አበባ የገባችው፡፡ እኔ ከመጣሁ በኋላ ፒያኖዋን ለመውሰድ ስጠይቅ፣ የቅንጦት እቃ ስለሆነ ታክስ መክፈል አለብህ በሚል ሁለት ወር ተያዘች፡፡ ሁለት ወር ሙሉ በየቀኑ አየር መንገድ እመላለስ ነበር፤ ምክንያቱም ፒያኖዋ የተቀመጠችው ደጅ ላይ ስለሆነ ፀሀይና ዝናብ እንዳያበላሻት በየቀኑ እየሄድኩ የምትሸፈንበትን ላስቲክ አስተካክላለሁ፣ እቀይራለሁ፡፡ እዚያ አካባቢ ያሉ ሰዎች እንዲንከባከቡልኝም አደራ እላለሁ፡፡ በመጨረሻ የጣሊያንና የቫቲካን ኤምባሲዎች ጣልቃ ገብተው በስጦታ እንደተሰጠኝ ለኢትዮጵያ መንግስት በደብዳቤ አሳውቀውልኝ እጄ ገባች፡፡ ፒያኖዋን ስረከብ ገልጬ ሳያት ከወገቧ በታች ዝናብ ገብቶባታል፡፡ በጣም አዘንኩና አለቀስኩ፡፡ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ለምን እንደማለቅስ ግራ ገባቸው፤ አንዳንዶች ደግሞ ለእንጨት ያለቅሳል እንዴ ብለውኛል፡፡ በነገርሽ ላይ ይህ ታሪክ የእንግሊዝ መንግስትና አዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ ለኢትዮጵያ ሚሊኒዬም በጋራ ባወጡት ትልቅ መፅሀፍ ውስጥ ከተካተቱ ታሪኮች አንዱ ነው፡፡
ክላሲካል ሙዚቃ ምን አይነት ሙዚቃ ነው? እኛ አገር በመሳሪያ ብቻ ከተቀነባበረ ሙዚቃ ጋር የመቀላቀል ነገር ይስተዋላል…
የክላሲካል ሙዚቃ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ የሙዚቃ ስልት ሲሆን በረጅም ጊዜ የትምህርት ሂደት የሚገኝ የሙዚቃ ክህሎት ነው፡፡ ክላሲካል ሙዚቃን በልምድ መጫወት አይቻልም፡፡ የክላሲካል ሙዚቃ ተብሎ ሲነሳ እነ ሞዛርት፣ ሀይደን፣ ቤትሆቨን የመሳሰሉት የሰሯቸው ስራዎች ይጠቀሳሉ፡፡
እኛ አገር ያለው የክላሲካል ሙዚቃ ተቀባይነት ምን ይመስላል?
አድማጭ አለው፤ አቅርቦት ግን የለም፡፡ ፒያኖ ማግኘት እጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡ በዚህ የሙዚቃ ዘርፍ መውጣት የሚፈልጉ ብዙ ልጆች አሉ፤ ግን የክትትል ችግር አለ፡፡ ቅድም እንዳልኩሽ የረጅም ጊዜ ስልጠና ይፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ተሰጥኦ ያላቸው ልጆች አሉ፡፡ እነሱን የሚፈልጉበት ለማድረስ ግን ብዙ ክትትል እና ድጋፍ ይፈልጋል፡፡
ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ማስተማሩን ለምን ተውከው?
እንዳልኩሽ ማስተማሩ በጣም ጊዜ ይጠይቃል፡፡ እኔ ደግሞ አጫጭር ኮርሶችን ስከታተልና ኮንሰርቶች ማሳየት ስጀምር፣ ቁጭ ብሎ የማስተማሩን ስራ እንዳያስተጓጉል በማለት ነው የተውኩት፡፡
ቡልጋሪያ አስተማሪህ የነበሩትን ፕሮፌሰር አንተ በምታስተምርበት ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ኮንሰርት እንዲያሳዩ አድርገህ ነበር፡፡ እስቲ ስለሱ ንገረኝ…
ለእኔ እዚህ መድረስ የቡልጋሪያ አስተማሪዬ ፕሮፌሰር ኢታናስ ኮርቴሽ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ እንደመምህሬ ሳይሆን እንደ ወላጄ ነው የማየው፡፡ እሱን ኢትዮጵያ አምጥቶ ኮንሰርት እንዲያሳይ ማድረግ ደግሞ የረጅም ጊዜ ህልሜ ነበር፡፡ በ2011 የሀንጋሪያዊው አቀናባሪ የፍራንስ ሊስታ 200ኛ አመት በአለም አቀፍ ፌስቲቫሎች ይከበር ስለነበር፣ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ፣ እዚህ አገር ያሉትን የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አግባብቼ ፕሮፌሰሩ አዲስ አበባ መጥቶ ኮንሰርት እንዲያቀርብ ጠየቅሁና ተሳካ፡፡ ኮንሰርቱም ተሰራ፡
አንተም ባለፈው ጥር ቡልጋሪያ በተማርክበት አካዳሚ ኮንሰርት አቅርበሃል…
አዎ፡፡ ከዚያም በተጨማሪ በቫዮሊን፣ በቼሎ እና በሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች አዲስ ስራ ሰርቻለሁ፡፡ ቡልጋሪያ የሄደኩት እሱን ለማስቀረፅ ነበር፡፡ የተማርኩበት አካዳሚ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ተቀረፀ፡፡ ከዚያ እዚህ ያደረሰችኝን ቡልጋሪያን ኮንሰርት ሰርቼ ላመስግናት አልኳቸው፡፡ በጣም ደስ አላቸውና ኮንሰርቱን ሰራሁ፡፡ እነሱ የኔን የሙዚቃ እድገት እያንዳንዷን ደረጃ ይከታተሉ ነበር፡፡ ከኮንሰርቱ በኋላ “ቡልጋሪያን በተለያዩ የአለም መድረኮች እያስጠራህ ነው” ብለው ትልቅ ሙያተኛና አስተዋፅኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን ከፍተኛ ሜዳሊያ ሸለሙኝ፡፡ በአሜሪካን በ2010 ዓ.ም ላይ ትልቅ ኮንሰርት ተደርጎ ተሳትፌ ነበር፡፡ ሁለት የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በሙዚቃ ዲፕሎማሲ የክብር እውቅና ሰጥተውኛል፡፡
የአሜሪካኑ የአልበም ማስመረቅ ፕሮግራም እንዴት ነበር?
የአሜሪካኑ ፕሮግራም በጣም ውጤታማ ነበር፤ እንደምታይው ደስታው እስከአሁን ከፊቴ ላይ አልጠፋም፡፡ ሂደቱ ከተጀመረ ቆይቷል፡፡ “ኤምሲል ዎርልድ ሪከርድስ ሌብል” በሚል የተባለ ኩባንያ ነው፡፡ ጥሩ ስራ የሰሩ ታዋቂ ሰዎችን ማስተዋወቅ ሲሆን ትልቁ ስራቸው ግን ያልታወቁ ሰዎችን መፈለግና ማስተዋወቅ ነው፡፡ “ስራህን በኢንተርኔት ላይ አይተነዋል፤ ጥሩ ነው እናስተዋውቅህ” ቢሉኝም ብዙዎች እንደዚያ እያሉ ተግባራዊ ስለማያደርጉት አላመንኳቸውም ነበር፡፡ በኋላ ግን ስራዎቼን በአዲስ እንድቀርፅና ኮንሰርት እንዳደርግ የሚያስችል የስራ ፈቃድ እና ቪዛ ላኩልኝ፡፡ በ2013 ሄጄ ኮንሰርት አቀረብኩ፤ ስራዬንም ቀረፅኩ፡፡ በወቅቱ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በአድናቆት የተሞላ ፅሁፍ አወጣ፡፡ ሞራሌን በጣም ከፍ አደረገው፡፡ ከአንድ አመት በኋላ፣ ሰሞኑን ማለት ነው ሲዲዬን ለቀቅኩ፡፡ የአልበሙ መጠሪያ “ላቭ ኤንድ ፒስ” ነው፡፡ አልበሙ ከፍተኛ ሽያጭ ነው ያስመዘገበው፡፡ በአሜሪካ የሙዚቃ ደረጃ በሚያወጣው የቢልቦርድ ሰንጠረዥም 23 ደረጃ ላይ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ከአርቲስት ሚካኤል በላይነህ ጋር የሰራሁት “መለያ ቀለሜ” የሚለው አልበምም በቢልቦርድ ሰንጠረዥ የገባ ሲሆን ለብቻዬ ከሰራኋቸው ውስጥ ግን የአሁኑ የመጀመሪያዬ ነው፡፡
የአሜሪካው ኮንሰርት ብዙ ኢትዮጵያውያን ታድመውት ነበር?
ብዙ ባይሆኑም ነበሩ፡፡ እንዲያውም ከኮንሰርቱ በኋላ እራት ጋብዘውኝ እንዴት አናውቅህም አሉኝ፡፡ ከጋባዦቼ አንዱ ደግሞ “አንተን የሙዚቃ ግርማ ሞገስ ብዬሀለሁ” አሉኝ፡፡ ይህ አባባል ለኔ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ አባቴ አስራ ሁለተኛ ክፍል ጨርሼ ዩኒቨርሲቲ ከተማርኩ በኋላ ወደ ስራ እንድገባ ነበር የሚፈልገው፡፡ የሙዚቃ ጉዞውን እንዳታደናቅፉት ብለው ብዙ እገዛ አድርገው ለዛሬ እኔነቴ የለፉት አጎቴ ናቸው፤ ስማቸው ደግሞ ሞገስ ነው፡፡ ግርማ ሞገስ ሲሉኝ በጣም ደስ አለኝ፡፡
ልጆችህን ፒያኖ እያስተማርክ ነው?
አዎ! የትምህርት ጊዜያቸውን ሳልሻማ በትርፍ ሰአት አስተምራቸዋለሁ፡፡
በሚቀጥለው ሐሙስ አዲስ አመት ነው፡፡ መጪውን አመት እንዴት ትቀበለዋለህ?
እንግዲህ እድሜ አግኝቶ አዲስ አመትን መቀበል ትልቅ ነገር ነው፡፡ በተቻለ መጠን አዳዲስ ስራዎቼን እንዲሁም ተሰርተው የተቀመጡትን የማስተዋውቅበት አመት ይሆናል፣ ሌሎች ብዙ በሮችም ይከፈታሉ ብዬ በተስፋ እቀበለዋለሁ፡፡
Photo: የእንቁጣጣሽ ስጦታ! “ክላሲካል ሙዚቃን በልምድ መጫወት አይቻልም”

የዓመቱ አነጋጋሪና አወዛጋቢ ክስተቶች

Photo: የዓመቱ አነጋጋሪና አወዛጋቢ ክስተቶች
በዓመቱ መጀመሪያ በመስከረም ወር 2006 ዓ.ም ለ12 ዓመታት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፤ ከስልጣናቸው የወረዱ ሲሆን በቦታቸውም ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተተክተዋል፡፡ በአምባሳደርነት ዘመናቸው የውጭ አገር ኢንቨስተሮችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣትና አገር ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በማግባባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው የሚነገርላቸው ዶ/ር ሙላቱ፤ የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸውን ከተረከቡ በኋላም ሥራቸው በቤተመንግስት አካባቢ የተገደበ አልሆነም፡፡ በተለያዩ አገራት እየዞሩ የውጭ ኢንቨስተሮችን የማግባባት ሥራቸውን ቀጥለውበታል፡፡
በዓመቱ ከተከናወኑ አነጋጋሪ ጉዳዮች መካከል አንድነት ፓርቲ ከሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተገናኘ የመብት ጥሰትና መጉላላት ተፈጽሞብኛል በማለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባንና የከተማዋን ፖሊስ ኮሚሽን በፍ/ቤት መክሰሱ ተጠቃሽ ነው፡፡
ፍ/ቤቱም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ “ክሱ ለክስ የሚያበቃ ምክንያት የለውም፣ አስተዳደራዊ ውሣኔ ያገኝ የሚል ውሣኔ የሰጠ ሲሆን ፓርቲውም በጊዜው ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልፆ ይግባኝ ለመጠየቅ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡  
የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ እንዲሁም የኢዴፓ መስራችና ሊ/መንበር የነበሩት አቶ ሙሼ ሰሙ ራሳቸውን ከፖለቲካ ፓርቲ ያገለሉት በዚሁ ባሳለፍነው ዓመት ነው፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ከጤና ጋር በተያያዘ፣ አቶ ሙሼ ደግሞ “የጥሞና ጊዜ እፈልጋለሁ” በሚል የፓርቲ ፖለቲካ በቃን ብለዋል፡
ሹመትና ህልፈት
የአማራ ክልልን ለ8 ዓመታት በርዕሰ መስተዳደርነት የመሩት አቶ አያሌው ጎበዜ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአምባሳደርነትና በትምህርት ሚኒስትርነት የተመደቡት ባሳለፍነው ዓመት ሲሆን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ባደረባቸው ህመም ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የህዝብ ተሳትፎና ንቅናቄ ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ሙክታር ከድርም የክልሉ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙ ሲሆን  በሳቸው ቦታ ወ/ሮ አስቴር ማሞ ተተክተዋል፡፡
የሳኡዲ ስደተኞችን ማባረር
የሳኡዲ አረቢያ መንግስት የመኖሪያ ህጋዊ ፍቃድ የላቸውም በሚል ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የበርካታ ሃገር ዜጎችን ከሃገሩ በኃይል ማስወጣት የጀመረው ባሳለፍነው ዓመት ጥቅምት ወር  መጨረሻ ገደማ ነበር፡፡ የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ ስደተኞች ባላቸው ላይ በወሰደው የማባረር እርምጃ ከ150ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት በሳበው በዚህ ክስተት፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳኡዲ ኤምባሲዎች በር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ለተመሳሳይ ዓላማ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ግን በፖሊስ በመበተኑ ሳይደረግ ቀርቷል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በየአረብ ሃገራቱ ለስራ የሚጓዙ ዜጎች ጉዳይ አሳስቦኛል በማለት ወደ የትኛውም የአረብ ሃገራት ለጉልበት ስራ የሚደረግን ጉዞ ለ6 ወር ያህል ማገዱ የሚታወስ ሲሆን እገዳው 9ኛ ወሩን ቢይዝም እስካሁን አልተነሳም፡፡
“የረዳት አብራሪው የአውሮፕላን ጠለፋ”
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ5 ዓመታት በረዳት አብራሪነት ያገለገለው ሃይለመድህን አበራ፤ በጥር ወር አጋማሽ ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ጣሊያን ሲበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን  ጠልፎ ስዊዘርላንድ ማሳረፉ ከዓመቱ አነጋጋሪና ትኩረት ሳቢ ጉዳዮች አንዱ ነበር፡፡
ረዳት አብራሪው አውሮፕላኑን ለምን እንደጠለፈ እስካሁንም ይሄ ነው የሚባል አሳማኝ ምክንያት አልተገኘለትም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ጠላፊው ተላልፎ እንዲሰጠው የጠየቀ ቢሆንም አዎንታዊ ምላሽ አላገኘም፡፡ ጠላፊው የስዊዘርላንድን መንግስት ጥገኝነት ጠይቆ እንደተፈቀደለትና አሁን እዚያው በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ፍትህ ሚኒስቴር በበኩሉ፤ በጠላፊው ላይ  ክስ መስርቶ ፍ/ቤት የአቃቤ ህጎችን ምስክርነት በመስማት  ላይ ይገኛል፡፡
መፍትሔ ያልተበጀለት “የሙስሊሞች ጉዳይ”
“ከሁለት ዓመት በፊት የታሰሩት ሙስሊም መሪዎቻችን ይፈቱ፣ ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ ንቅናቄዎች እየተካሄዱ ነው ዓመቱ ያለፈው፡፡ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም አርብ በታላቁ አንዋር መስጊድ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ  ተከትሎ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ በሰዎች ላይ ድብደባና ጉዳት መድረሱ ይታወሳል፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ታስረው የነበረ ሲሆን በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ በዋስ ተለቀዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የቀድሞው “አዲስ ጉዳይ” መፅሄት የፎቶግራፍ ባለሙያ አዚዛ አህመድ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል ወይንሸት ሞላ ይገኙበታል፡፡
የታሰሩት ሙስሊሞች ጉዳይ በፍ/ቤት መታየቱን የቀጠለ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን በማሰማት ሂደት ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
አዲሱ ማስተር ፕላን የቀሰቀሰው ተቃውሞ
ሌላው የዓመቱ አብይ ክስተት የአዲስ አበባና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ስር የሚተዳደሩ ከተሞች የጋራ ማስተር ፕላን የተነሳ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና ረብሻ ሲሆን የሰው ህይወትን ጨምሮ በርካታ ጉዳትና ውድመት ደርሷል፡፡
በአገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የኦሮሚያ ተወላጅ ተማሪዎች በሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ ባስነሱት ተቃውሞ ሳቢያ ከፖሊስ ጋር ግጭት መፈጠሩ ይታወሳል፡፡
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በአምቦ ከተማ በተፈጠረው ግጭት 30 የሚደርሱ ሰዎች መሞታቸውን ሲዘግቡ፣ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው፤ በአጠቃላይ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን ዘግበዋል፡፡
ተቃውሞውን ለማስቆም በፀጥታ ሃይሎች ከተወሰደው እርምጃ ባሻገር ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ውዝግብ ባስነሳው የጋራ ማስተር ፕላን ዙሪያ ከተማሪዎችና ከህብረተሰቡ ጋር ለበርካታ ሳምንታት ውይይት እንዳደረጉም አይዘነጋም፡፡
“አስደንጋጩ” የጋዜጠኞችና ጦማሪያን እስር
መንግስት በሽብርተኝነት ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለት  3 ጋዜጠኞችና 6 ጦማሪያን ማሰሩ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት የሳበ ሌላው የዓመቱ ጉልህ ክስተት ነበር፡፡ አብዛኞቹ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማትም እስሩን ከመጪው አገራዊ ምርጫ ጋር በማያያዝ የመንግስት ፍርሃት የፈጠረው ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ እንዲሁም “ዞን 9” በተሰኘ ድረገጽ ፀሐፊነታቸው የሚታወቁት አጥናፉ ብርሃኔ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ በፈቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ ተይዘው መታሰራቸው የሚታወስ ነው፡
መንግስት በተጠርጣሪዎቹ ላይ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በመተሳሰር እንደሚሰሩ ደርሼበታለሁ በሚል ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን ጉዳያቸው በፍ/ቤት በመታየት ላይ ይገኛል፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው መያዝና የተቃዋሚ አመራሮች እስር
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት ከተፈረጁት አምስት የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የ“ግንቦት 7” ዋና ፀሐፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በየመን መያዝና ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠት የተጠናቀቀው አመት ያልተጠበቀ ክስተት ነበር፡፡ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው አቶ አንዳርጋቸው፤ ቀደም ሲል በሌሉበት በተመሰረተባቸው የአሸባሪነት ክስ የሞት ፍርድ እንደተወሰነባቸው ይታወሳል፡፡
እኚህ የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር በኢትዮጵያ መታሰራቸውን ተከትሎ በተለያዩ የአሜሪካና አውሮፓ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በእንግሊዝ ኢምባሲዎች ደጃፍ ላይ በመሰባሰብ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል - እንግሊዝ ዜግነት ለሰጠችው ሰው ተገቢውን ጥበቃና ከለላ አልሰጠችም በሚል፡፡
አንዳንዶች እንደሚሉት፤ የአቶ አንዳርጋቸው ጦስ ለአገር ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ተርፏቸዋል፡፡ እሳቸው በታሰሩ ማግስት በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌውና የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ም/ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ም/ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንዲሁም የአረና ፓርቲ አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ በሽብር ተጠርጥረው የታሰሩ ሲሆን ጉዳያቸውም በፍ/ቤት እየታየ ነው፡፡
የግል የሚዲያ ተቋማት ክስ፤ የአሳታሚዎችና ጋዜጠኞች ስደት
መንግስት በ“ፋክት” ፣ “ሎሚ” ፣ “አዲስ ጉዳይ”፣ “እንቁ”፣ “ጃኖ” መፅሄት እና “አፍሮ ታይምስ” ጋዜጣ አሳታሚዎችና ባለቤቶች ላይ የወንጀል ክስ መመስረቱን በቴሌቪዥን የገለፀው  በሐምሌ ወር መጨረሻ ነበር፡፡ ከመግለጫው ጥቂት ሳምንት በኋላ ለፍ/ቤት የቀረበው የአሳታሚዎችና የስራ አስኪያጆቹ ክስ ጠቅለል ብሎ ሲታይ በተለያዩ የህትመት ውጤቶቻቸው በፃፏቸው ፅሁፎች በህገ-መንግስታዊ ስርአቱ ላይ አመፅ ቀስቅሰዋል፣ በሃሰት ወሬ ህዝብን በመንግስት ላይ የሚያነሳሱ ፅሁፎችን አትመዋል የሚል ሲሆን የፍ/ቤት ሂደቱም ቀጥሏል፡፡
የመንግስትን ክስ ተከትሎ ከ “ፋክት” መፅሄት አሳታሚ በስተቀር የሁሉም ተከሳሽ የሚዲያ ተቋማት ባለቤቶች ሃገር ለቀው የወጡ ሲሆን በአጠቃላይ 16 ያህል የግል ፕሬሱ አባላት አገር ለቀው ተሰደዋል፡፡ መንግስት በበኩሉ፤ በጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተ ክስ ስለሌለ የተሰደደ አንድም ጋዜጠኛ የለም ብሏል፤ ጋዜጠኞቹ ለተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከአገር መውጣታቸውን በመጠቆም፡፡
“ብዙ የተባለለት የደሞዝ ጭማሪ”
ብዙ የተነገረለትና በጉጉት የተጠበቀው የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪም የተደረገው በዚህ ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ ነው፡፡ ጭማሪው ከፍተኛ ይሆናል በሚል ግምት ከፍተኛ የመነጋገሪ አጀንዳ ሆኖ የቆየው የደሞዝ ጭማሪው ብዙዎች እንደጠበቁት ግን አልሆነም፡፡ ጭማሪው ከ33 እስከ 46 በመቶ ብቻ ነበር፡፡ ጭማሪውን ተከትሎም ነጋዴው በመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዳያደርግ መንግስት ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ቆይቷል፤ ማስጠንቀቂያውን የጣሱ “ህገወጥ” ነጋዴዎች ላይም እርምጃ መወሰዱን መንግስት አስታውቋል፡፡
“ዓለምን ያስደነገጠው ኢቦላ”
በምዕራብ አፍሪካ አገራት ተከስቶ ወደሌሎች የአፍሪካ አገራት የተስፋፋው ኢቦላ፤ መላውን ዓለም ድንጋጤ ውስጥ የከተተው በዚሁ ዓመት ላይ መገባደጃ ላይ ሲሆን አሁንም ስጋት እንደሆነ ቀጥሏል፡፡  
ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት (WHO) ከትላንት በስቲያ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ቫይረሱ በተከሰተባቸው የአፍሪካ አገራት 2ሺ ገደማ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን አስታውቋል፡፡
 ኢትዮጵያም የዚህ ቫይረስ ተጠቂ እንዳትሆን ከወዲሁ ለመከላከል የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን መንግስት አስታውቋል፡፡ ቦሌ አየር መንገድን ጨምሮ በተለያዩ የድንበር አካባቢዎች ጊዜያዊ የምርመራ ጣቢያዎች የተቋቋሙ ሲሆን በአዲስ አበባም 50 አልጋዎች ያሉት ልዩ ሆስፒታል መዘጋጀቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከመሳሳም በስተጀርባ ያለው ሳይንስ

መሳሳም የሁለት ሰዎች ፍቅር መገለጫ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሁለት ፍቅረኛሞችን የበለጠ ያጣምራል፡፡ መሳሳም ጥልቅ ፍቅራዊ፣ ሀይል ያለው፣ ወይም የሰላምታ መግለጫ ሊሆን ይችላል፡፡ በአማካይ አንድ ሰው በህይወቱ 20,000 ደቂቃዎችን በመሳሳም ያሳልፋል፡፡ ይህ ማለት ወደ ሁለት ሳምንት ይጠጋል፡፡ ይህን ያህል ሰዓት በመሳሳም ለማሳለፍ የሆነ ምክንያት መኖር አለበት፡፡ እርግጥ ነው፤ ከመሳሳም በስተጀርባ ያለ ሳይንሳዊ ምክንያት አለ፡፡ ይህ ከመሳሳም ጀርባ ያለው ሳይንስ በፍቅር ወቅት ብዙ ጊዜ ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡ ነገር ግን ይበልጥ እንድንሳሳም የሚያደርገን ይህ ሳይንስ ነው፡፡

የመሳሳም ሳይንሳዊ ጥናት Philematology በመባል ይታወቃል፡፡ የማንኛውም ሰው ከንፈርና ምላስ በነርቮች የተሞሉ ስለሆኑ በመሳሳም ወቅት አዕምሮአችን የተለየ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም በምንሳሳምበት ጊዜ ሰላሳ አራት የፊት ጡንቻዎችን እንጠቀማለን፡፡

ለምን እንሳሳማለን? (Why do we kiss?)

እኛ ለመሳሳማችን የማህበረሰብና የዝግመተ- ለውጥ (evolution) አስተዋጾ ከፍተኛ ነው፡፡ የእኛ የመሳሳም ፍላጎት ከማህበረሰቡ ሊመነጭ የቻለው በሰዎች መካከል በሚፈጠር መቀራረብ ነው፡፡ ከማህበረሰብ ብዙ የምንማራቸው ነገሮች እንዳሉ ሁሉ በተለያዩ ማህበረሰቦች መሳሳም የፍቅር መግለጫ ሆኖ ስለሚታይ ይህንን ከአካባቢያችን እንማራለን፡፡ ይህ በሌሎች ማህበረሰባዊ አጥቢ እንስሳቶች ላይም ይታያል፡፡ ለመቀራረብ የምናሳየው ፍላጎት እናትና ልጅን እንደሚያገናኘው የሆርሞንና የኒውሮን የጥምረት መሠረት የተገነባ ነው፡፡

በዝግመተ-ለውጥ በኩል ስንመጣ ደግሞ ጦጣና የጦጣ ዘሮች ለምሳሌ ልጆቻቸውን በመሳም ምግብ በአፋቸው ያቀብሏቸዋል፡፡ ይህ ድርጊት ከዘመን ዘመን እንደፍቅር መግለጫ ተስፋፍቶ በሰዎች ላይ ተፅእኖ ያሳደረ ነው፡፡

ዋነኛውና ቀላሉ ምክንያት ደግሞ በመሳሳም ወቅት የሚፈጠረው ጥሩ ስሜት ነው፡፡ በምንሳሳምበት ወቅት ከአስራ ሁለቱ የአዕምሮ ነርቮች አምስቱ ተሳታፊ ናቸው፡፡ ይህ ስሜት በኑሮአችን እርካታን ስለሚፈጥርልን ይበልጥ እንድንሳሳም ያደርገናል፡፡

ሌላው የመሳሳም ምክንያት ሊሆን የሚችለው ደግሞ የተቃራኒ ፆታን የበሽታ መከላከያ አቅም (Immune system) መገምገም ስለሚያስችላቸው ነው፡፡ የሚያፈሩት ልጆች ጠንካራ እንዲሆኑ የበለጠ ጠንካራ የበሽታ መከላከያ አቅም ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ሴቶች ሳያውቁት የጓደኛቸውን የአቅም ተስማሚነት የመገምገም ችሎታ አላቸው፡፡

በመሳሳም ወቅት፡
  • የልብ ትርታ እና የደም ግፊት ይጨምራል
  • ትንፋሽ ይጨምራል
  • ጉንጫችን እና ፊታችን ይቀላል
  • የአይን ቀዳዳ ይለጠጣል
  • አዕምሮ ዘና ይላል

መሳሳምና ጥቅሙ (Benefits of Kissing)

መሳሳም የደስታ ምንጭ የሚሆኑ ኬሚካሎችን ያመነጫል፡፡ Dopamine (ዶፓሚን) አንዱ ኬሚካል ነው፡፡ ይህ ኬሚካል አዕምሮ ውስጥ የሚመነጭ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ ከመሳሳም ሌላ በአደንዛዥ ዕፆችና በመብላት ይህ ኬሚካል ሊመነጭ ይችላል፡፡ በዚህ ደስታ ምክንያት ሰዎች መሳሳምን ያዘወትራሉ፡፡

መሳሳም በትዳርም ሆነ በጓደኝነት ወቅት አስፈላጊ ነው፡፡ ሰዎችን የበለጠ ያቀራርባል፡፡ ኢንዶርፊን (endorphin) የተባለውን ሆርሞን በማመንጨት በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ደስተኛ እንድንሆን ይረዳል፡፡ የሰውነታችንን ቀመር ወዲያውኑ ይቀይረዋል፡፡ ሁለቱም አጋሮች በዚህ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ከሆኑ ሰውነታችን ኢንዶርፊን (endorphin) እያመነጨ የበለጠ ደስተኛና የበለጠ እንዲቀራረቡ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም መሳሳም ኦክሲቶሲን (Oxytocin) የተባለውን ሆርሞን በማመንጨት ይታወቃል፡፡ ይህ ሆርሞን ‹‹የፍቅር ሆርሞን›› እየተባለ በተለምዶ ይጠራል፡፡ በፍቅረኛሞች መካከል ፍቅርን እያጧጧፈ አብረው እንዲቆዩ ያግዛቸዋል፡፡

በ2009 የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው መሳሳም ለሴቶች Cytomegalovirus ከተባለው ቫይረስ የመከላከያ አቅም ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ በሰው ልጅ ምራቅ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ቫይረሱ ጎጂ ባይሆንም በእርግዝና ወቅት ግን ያልተወለዱ ህፃናትን ሊገድልና የተለያዩ የአዕምሮ ችግሮችን ሊያስከትልባቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ቫይረስ ከበፊቱ ከሴቷ ጋር ከተዋወቀ የመከላከያ አቅም ስለምታዳብር ምንም አይነት ችግር በፅንሱ ላይ አይደርስበትም፡፡

መሳሳም በደቂቃ እስከ 6 ካሎሪ ያቃጥላል፡፡ ይህም ማለት በአንድ ሰዓት ቢሰላ ከአንድ ሰዓት ሩጫ የምናጠፋው የበለጠ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

የበሽታ መከላከያ አቅም በመሳሳም ልናዳብር እንችላለን፡፡ እርግጥ ነው በአፍ ውስጥ የተለያዩ ባክቴሪያዎች ይገኛሉ፡፡ በዚህም በሽታ ልናመጣ እንችላለን፡፡ ነገር ግን ከመሳሳም ይልቅ እጅ በመጨባበጥ የበለጠ በሽታ ልናተርፍ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ተገቢውን የአፍ ፅዳት አድርገን ከተሳሳምን ምንም አይነት ችግር አይመጣም፡፡

የመሳሳምና ባህል (Kissing and Culture)

አንድ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ቢኖር መሳሳም በሁሉም ባህል አንድ አይነት እንዳልሆነ ነው፡፡ እንዲያውም መሳሳምን የማይፈቅዱና የማይተገብሩ ብዙ ባህሎች አሉ፡፡ ይህም ማለት መሳሳም በማህበረሰቡ ተፅእኖ ሊያድርበት የሚችልና በትምህርት ልናገኘው የምንችለው ነገር መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ምንም እንኳን ተፈጥሮአዊ የመሳሳም ፍላጎት ቢኖረንም ባህሉ ካልፈቀደ አንተገብረውም፡፡

በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም በብዙ አጥኚዎች እንደሚገመተው መሳሳም ከህንድ የመጣ ነው፡፡ አንዳንድ እንደ ሀውልቶችና ቅርፃ ቅርፆች ያሉ መረጃዎች የመሳሳም ስዕልን ይዘው ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህች ሀገር ተገኝተዋል፡፡  

Source : http://www.wanawtenanew.com/ 

‹‹በኢትዮጵያ ያለው የነዳጅ ጥራት ችግር ነዳጅ ቆጣቢና ዘመናዊ መኪኖችን እንዳናቀርብ አድርጐናል››

ጄፍሪ ኒሜዝ፣ ከሰሐራ በታች ለሚገኙ የአፍሪካ አገሮች
የፎርድ ኩባንያ ፕሬዚዳንት
ለደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የፎርድ ሞተር ኩባንያ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት ከአራት ዓመታት በፊት ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከ2013 ጀምሮም ከሰሐራ በታች ለሚገኙ የአፍሪካ አገሮችም ይህንኑ ኃላፊነት ይዘው በመሥራት ላይ እንደሚገኙ ከኩባንያው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ዋና ማምረቻ ፋብሪካዎቹን በደቡብ አፍሪካ ከተከለ 91 ዓመታትን ያስቆጠረው ፎርድ ኩባንያ፣ በታዋቂው ሔንሪ ፎርድ እ.ኤ.አ. በ1903 ነበር የተመሠረተው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ የተገኙት ጄፍሪ ኒሜዝ፣ በኢትዮጵያ ፎርድ ኩባንያ አቅርቦቱን ለማስፋፋት እንደሚፈልግ፣ እግረ መንገዱንም እንደ የውጭ ምንዛሪና በነዳጅ ጥራት ላይ ከመንግሥት ጋር ለመምከር መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ፎርድ ሞተር፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ ለመካከለኛው ምሥራቅና ከሰሐራ በታች ለሚገኙ የአፍሪካ አገሮች 25 አዳዲስ ምርቶችን ለማቅረብ ከማቀዱ ጋር በተያያዘ፣ በኢትዮጵያ የፎርድ ወኪል ከሆነው ሬስ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ጋር ለመነጋጋር መምጣታቸውም ታውቋል፡፡ ሬስ ኢንጂነሪግ ከ80 በመቶ በላይ የገበያ ድርሻው የኮንስትራክሽን ማሽነሪ የሆኑትን የካተር ፒላር ኩባንያ ምርቶችን በማስመጣት፣ ለመንግሥትና ለግል ፕሮጀክቶች እያቀረበ የሚገኝ አንጋፋ ኩባንያ ነው፡፡ ከሁለቱ የአሜሪካ ኩባንያዎች በተጨማሪ የሜሲ ፈርጉሰን ኩባንያ ሥሪት የሆኑ የግብርና ማሽነሪዎችንና የሌሎች ኩባንያዎችን ማሽኖች፣ የኃይል አቅርቦት መቆጣጠሪያ መሣሪዎችንና ሌሎችንም ያስመጣል፡፡ ከሬስ ኢንጂነሪንግ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ጄፍሪ ኒሜዝ ከሪፖርተርና ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ ይህንን ቃለ ምልልስ ብርሃኑ ፈቃደ አጠናቅሮታል፡፡
ጥያቄ፡- ፎርድ ኩባንያ ከሰሐራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ እ.ኤ.አ. እስከ 2020 ድረስ የ40 በመቶ የመኪና ሽያጭ ሊኖረው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ድርሻ ምን ያህል እንደሆነ ተመልክቷል? ስለኢትዮጵያ የተሠሩ አኃዞች ካሉ ቢገለጹልን?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- ኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሆነ የዕድገት አቅም ላይ እንደምትገኝ እናምናለን፡፡ በቀጣናችን 67 ገበያዎች አሉን፡፡ ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እንዳላት እናምናለን፡፡ ጠንካራ መንግሥት አለ፡፡ የሕግ የበላይነት፣ ፈጣን ዕድገት ያለው ኢኮኖሚ፣ ጥሩ ሥርዓተ ትምህርት በመኖሩ ኢትዮጵያ ከአማካይ በላይ አቅም እንዳላት እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን አኃዞችን ነጣጥለን ለኢትዮጵያ ምን ያህል ነው ብለን አላወጣንም፡፡ የ40 በመቶው ዕድገት ለእያንዳንዱ የተናጠል ገበያም የተከፋፈለ አይደለም፡፡
ጥያቄ፡- እንደ ቶዮታ፣ ኒሳንና ኪያ የመሳሰሉ ተቀናቃኞችን እንዴት ትመከታላችሁ? እያንዳንዱ ሰው ሊገዛ በሚችለው አቅም መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ ወይም በምሥራቅ አፍሪካ ገበያ ለማቅረብ አማራጭ ሐሳብ አላችሁ?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ በዓለም ላይ ፉክክር ከሚበዛባቸው ኢንዱስትሪዎች አንዱ ነው፡፡ በጣም ቀላልና በተመጣጣኝ ዋጋ ሊቀርቡ የሚችሉ መኪኖችን የሚሠሩ አምራቾች አሉ፡፡ ውድ ተሽከርካሪዎችንም የሚያመርቱ አሉ፡፡ እዚህ ባለው ገበያ የእኛ ዓላማ ለበርካታ ደንበኞች የሚስማሙ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ ነው፡፡ ለዚህም ነው አነስተኛ፣ መካከለኛና ትልልቅ ተሽከርካሪዎችን ለማቅረብ የምንጥረው፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን ጥሩ ዋጋ ያላቸውን ነው የምናመጣው፡፡ በፎርድ ኮርፖሬሽን እንደ መመርያ የምንጠቀምባቸው ሦስት የኮርፖሬት ምሰሶዎች አሉን፡፡ አንዱ ጠንካራ ቢዝነስ ነው፡፡ ሁለተኛው ጥሩ ምርት ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ ሕግ ነው፡፡ ለደንበኞች በሚሆኑ ምርቶች ላይ አራት መርሆዎችን እንከተላለን፡፡ ጥራት፣ አረንጓዴነት፣ ደኅንነትና ብልኃት የሚባሉ መለያዎች አሉን፡፡ በእነዚህ መርሆዎች እየታገዝን ኢንዱስትሪውን እንመራለን፡፡ ስለዚህ በአረንጓዴያማነት መርህ መሠረት ነዳጅ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎችን እያመረትን ነው፡፡ በእያንዳንዱ ተናጠል ምርታችን ላይ ነዳጅ ቆጣቢነትን መተግበር እንፈልጋለን፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ ይኼ ምናልባት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ይኼውም ከነዳጅ ጥራት ጋር በተያያዘ ነው፡፡ የነዳጁ ጥራት ችግር ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ ሞተሮችን ማምጣት አላስቻለንም፡፡ መንግሥት ተፈላጊውን የነዳጅ ጥራት ለማምጣት እንደሚሠራ እምነት አለን፡፡ ሆኖም አሁን ከመንግሥት ጋር በዕቅዶቻቸው ዙሪያ እየተነጋገርን ነው፡፡ ከፍተኛ ጥራት ያለው ነዳጅ ቢመጣ፣ ውስብስብና ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ሞተሮች የተገጠሙላቸው ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እንችል ነበር፡፡ የምንጠቀመው ቴክኖሎጂ በናፍጣ የሚሠሩ ሞተሮችን በመጠቀም አዲሱን ሬንጀር ሞዴል መኪና 2.2. ሊትርና 3.2 ሊትር ናፍጣ ሞተር ያለው ነው፡፡ ይህንን መኪና ለገበያ እያቀረብን ነው፡፡ በፔትሮሊየም የሚሠሩ ሞተሮች የተገጠመላቸው መኪኖችም አሉን፡፡ እነዚህም ነዳጅ በመቆጠብ በጣም የታወቁ ናቸው፡፡ እነዚህን ሁሉ ግን እዚህ ማምጣት አንችልም፡፡ ግን ከመንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው፡፡ ሆኖም ግን እኛ የራሳችን፣ ተቀናቃኞቻችንም የየራሳቸው ቦታ ያላቸው ይመስለኛል፡፡ ደንበኞች የሚፈልጉትን ነገር እያቀረብን ነው፡፡ ትልቅ ጥራት ያለው፣ ጥሩ ምርት፣ ድኅረ ሽያጭ በማከናወን ተወዳዳሪነታችንን እያስጠበቅን ነው፡፡
ጥያቄ፡- በአፍሪካ ትልቁ ገበያችሁ የት ነው? የማምረቻ ፋብሪካችሁ የሚገኘው በደቡብ አፍሪካ ብቻ ነው ማለት ነው?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- ከአፍሪካ ትልቁ ገበያችን ደቡብ አፍሪካ ነው፡፡ ረጅም ጊዜ ሆኖናል፡፡ የመጀመሪያውን ‹‹ሞዴል ቲ›› የተባለ መኪና የሸጥነው እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 1904 ነበር፡፡ ፎርድ ኩባንያ የተመሠረተው ግን እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 1903 ነበር፡፡ የመጀመሪያው ማምረቻ የተገነባው እ.ኤ.አ. በ1923 በመሆኑ፣ ላለፉት 91 ዓመታት በደቡብ አፍሪካ ስናመርት ቆይተናል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ለረጅም ጊዜ ኖረናል፡፡ እዚያ በዓመት እስከ 70,000 መኪኖችን እንሸጣለን፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅና በአፍሪካ በጠቅላላው በዓመት 2,000 እንሸጣለን፡፡ ከመካከለኛው ምሥራቅ ሳዑዲ ዓረቢያ ትልቁ ገበያችን ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ ሁለት የማምረቻ ይዞታዎች አሉን፡፡ አንዱ ሬንጀር መኪና የሚመረትበት ሲሆን፣ ለ148 አገሮች ኤክስፖርት ይደረጋል፡፡ ገበያው ከአፍሪካ እስከ መካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ያካትታል፡፡ እርግጥ ኢራን በአሜሪካ በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት ወደዚያ አንልክም፡፡ ሁሉም የምራብና የምሥራቅ አውሮፓ አገሮች ሬንጀር የተባለውን የፎርድ መኪና ይገዛሉ፡፡ በአርጀንቲና የሬንጀር ፋብሪካ ስላለ የላቲን አሜሪካ ገበያን ይሸፍናል፡፡ በታይላንድም ተመሳሳይ ፋብሪካ ስላለ፣ አዝያን የተባለውን የንግድ ግሩፕን ይሸፍናል፡፡
በፕሪቶሪያ የመኪና መምረቻው ሲገኝ፣ በፖርት ኤሊዛቤት ከተማ ደግሞ የመኪና ሞተሮችን የሚያመርተው ፋብሪካ አለን፡፡ ፑማ የተባለውን የናፍጣ ሞተር ያመርታል፡፡ ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ትልቁ ማምረቻ አለን፡፡ ከሰሐራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ስላለው አቅም እያየን ነው፡፡ ናይጄሪያ ውስጥ ያሉ ተወዳዳሪዎቻችን አዳዲስ ማምረቻዎችን ለመገንባት ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡ በከሰሐራ በታች የአፍሪካ አገሮች ላይ ጥናት ከማድረግ በቀር እውነቱን ለመናገር ምንም የወሰንነው ነገር የለም፡፡ ኢንቨስት ለማድረግ ከመወሰናችን በፊት በደንብ ማጥናት እንፈልጋለን፡፡ ቀድመን ላንመጣ እንችላለን፣ ስንመጣ ግን ከሰፊ መሠረተ ልማት ጋር ነው፡፡ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ከሚሰጣቸው ጥቅሞች አንዱ በተዘዋዋሪ የሚፈጥራቸው የሥራ ዕድሎችና መሠረተ ልማቶች ናቸው፡፡ የአቅርቦት መሠረቱ ዋናው የማምረቻ ፋብሪካ ትልቅ ጠቀሜታ ነው፡፡ መቶ በመቶ የመኪና አካላትን ከውጭ በማስመጣት ላይ የተመሠረታችሁ ከሆነ፣ ማምረቻ ፋብሪካ ሊያመጣ የሚችለውን ጥቅም እያጣችሁ ነው ማለት ነው፡፡ መንግሥት ትክክለኛውን ፖሊሲ በማውጣት ለዘርፉ እንዲያውል እየመከርን ነው፡፡ አቅራቢዎች የተሻለ ዕድል እንዲኖራቸው ለማስቻልም እንሞክራለን፡፡
ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ የመገጣጠሚያ ፋብሪካ የመገንባት ሐሳብ አላችሁ? 
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- እንዳልኩት በኢትዮጵያም ሆነ ከደቡብ አፍሪካ ውጪ በመገጣጠሚያ ዘርፍ  ኢንቨስት ለማድረግ ምንም ዓይነት ዕቅድ የለንም፡፡ በደቡብ አፍሪካ ያለንን ድርሻ ማስፋፋት እንፈልጋለን፡፡
ጥያቄ፡- የፎርድ መምጣት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚጨምረው እሴት ምንድነው?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- ፎርድ ለኢትዮጵያ ምን ያመጣል? ለሚለው የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚዘውሩት መሣሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህን መሣሪያዎች ተጠቅመው ሰዎች ገበያ የሚያወጡ ነገሮችን ያመርታሉ፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች ኤሌክትሪክ፣ መንገዶች፣ ትምህርትና ያለጥርጥር ደግሞ እንቅስቃሴ ናቸው፡፡ ሬስ ኢንጂነሪንግ ለምሳሌ የፎርድ መኪኖችን ብቻ ሳይሆን የካተር ፒላር ምርቶች የሆኑ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን ያቀርባል፡፡ ከእነሱ ጋር መሥራታችን መሠረተ ልማት ላይ ብቻ ሳይሆን የንግድ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ስለሚያስችለን እንደሰታለን፡፡ እዚህ የምንሸጣቸው መኪኖች ለንግድ ዓላማና ምርት ለማከፋፈል ተግባር ሲውሉ እያየን ነው፡፡ እንደ አውቶሞቲቭ አቅራቢ ኩባንያ፣ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ዋናው ጅረት ውስጥ እንገኛለን ብለን እናምናለን፡፡
ጥያቄ፡- አብዛኛው የኢትዮጵያ አውቶሞቲቭ ቢዝነስ ባገለገሉ ተሽከርካሪዎች የተሞላ ነው፡፡ ይህ መሆኑ እንደ ፎርድ ላሉ ኩባንያዎች ምን ማለት ነው? ይኼ በመሆኑ ገበያው ውስጥ ለመግባት ሲታሰብ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ወይም እንደ ፈተና ሊታይ የሚችልበት ምክንያት ምንድነው?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- ምርታችንን ከሸጥንበት ቀን በኋላ መኪናው ያገለገለ መሆኑ ተጨባጭ እውነታ ነው፡፡ ስለዚህ ያገለገሉ መኪኖች የሚበዙበት ኢኮኖሚና ኢንዱስትሪን እንደግፋለን፡፡ በዓለም ላይ ላገለገሉ መኪኖች ማረጋገጫ የምንሰጥባቸው በርካታ ፕሮግራሞች አሉን፡፡ እነዚህን ፕሮግራሞች ወደ ከሰሐራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች የማምጣት ስትራቴጂ አለን፡፡ ሬስ ኢንጂነሪንግ ሁለት የዚህ መሰል ተሸከርካሪዎች የሚስተናገዱበት ማዕከል እየገነባ መሆኑ አስደስቶናል፡፡ የየትኛውም ኩባንያ ሥሪት የሆኑ መኪኖች ቀላል ጥገና የሚያገኙባቸው ናቸው፡፡ ያገለገሉ መኪኖች ኢንዱስትሪ የአጋጅነቱን ያህል ጥሩ የሚባሉ አጋጣሚዎችን የሚፈጥር ነው ማለት ይቻላል፡፡ መንግሥት በኢንዱስትሪ ፖሊሲው አማካይነት አማራጭ መፍትሔ ካገኘና የትኛውን ዓይነት ተሽከርካሪ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት እንደሚቻል፣ ለምን ዓይነት ተግባር የሚውሉ መሆን እንዳለባቸው ውሳኔ ካሳለፈ፣ እኔ በእነሱ ቦታ ሆኜ ለመናገር ሳይሆን አሁን ግን  የትኛውም ዓይነት ያገለገለና አዲስ መኪና አቅርቦት ላይ እንሳተፋለን፡፡
ጥያቄ፡- ጥቂት የቻይናና የመንግሥት ድርጅቶች የመገጣጠም ሥራ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ይኼ ለእናንተ ምን ማለት ነው? በመጪዎቹ አምስት ወይም አሥር ዓመታት ውስጥ የቻይና አዳዲስ መኪኖች የኢትዮጵያን ገበያ፣ አልፎም የጎረቤት አገሮችን ሊቆጣጠሩ ይችላሉ የሚል ግምትም አለ፡፡
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- በቻይና ከሚሸጠው መኪና ውስጥ ምን ያህል እጁ እዚያው ቻይና የተሠራ ነው የሚለውን አኃዝ ብንመለከት ብዙ የሚባል አይደለም፡፡ ይልቁንም በርካታ የውጭ ምርቶች ናቸው የሚሸጡት፡፡ ደንበኞች አማራጭ ማግኘታቸው ተገቢ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ውድድርንም እቀበላለሁ፡፡ እኔ ግን ሰዎች ፎርድን እንዲመርጡ ነው የምፈልገው፡፡ ጥሩ እሴት ያለው በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ ከአምስት ዓመት በኋላ ቻይኖች የት ይደርሳሉ፣ ኮሪያዎች ይህንን ይሠራሉ በሚለው ነገር ላይ አስተያየት መስጠት አልፈልግም፡፡ ምክንያቱም እነሱ የራሳቸው የቢዝነስ ዕቅድ አላቸው፡፡ እኔን የሚያሳስበኝ የራሴ የቢዝነስ ዕቅድ ነው፡፡
ጥያቄ፡- በነገራችን ላይ በኢትዮጵያ በዓመት ምን ያህል መኪኖችን ትሸጣላችሁ?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- በሥሌታችን መሠረት የገበያውን ዘጠኝና አሥር በመቶ ድርሻ እንሸጣለን፡፡ ይህንን በሚገባ ለማሳየት በአውሮፓ ዘጠኝ በመቶ፣ በደቡብ አፍሪካ 13 በመቶ፣ በቻይና አራት በመቶ፣ በአሜሪካ 15 በመቶ የገበያ ድርሻ አለን፡፡ ስለዚህ አሥር በመቶ ጥሩ አኃዝ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ከዓለም ገበያ ድርሻችን ከአማካይ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡
ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ያላችሁ የገበያ ድርሻ እስከ አሥር ከበመቶ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በገንዘብ ደረጃ ሲገለጽ ምን ያህል ይሆናል?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- የግል ኩባንያ በመሆናችን የሽያጭ መጠናችንን ይፋ አናደርግም፡፡ እርግጥ የእኛም ሳይሆን የሬስ ኢንጂነሪንግ ዓመታዊ ሽያጭ ነው፡፡ ዓመታዊ ሽያጫችንን በቀጣና ደረጃ ነው ይፋ የምናደርገው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2014 ሁለተኛው ሩብ ዓመት የነበረን ዓመታዊ ሽያጭ 34 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡
ጥያቄ፡- የአገር ውስጥ ወኪሎች ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የሚያነሷቸው ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ኩባንያዎ ምን ይላል? የምንዛሪ እጥረቱ በፎርድ ኩባንያ ላይ ተፅዕኖ አድርሶበታል?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- ችግሩ ፎርድ ኩባንያን ለይቶ ተፅዕኖ የሚፈጥርበት አይደለም፡፡ የትኛውንም ዕቃ የሚያስመጣ ሁሉ ተፅዕኖው ያርፍበታል፡፡ የመንግሥት ሁኔታ ይገባኛል፡፡ የንግድ ሚዛኑን ማስጠበቅ አለባቸው፡፡ ከኢኮኖሚ ፖሊሲው ጋር የሚጣጣም የውጭ ምንዛሪና ዋጋ መኖሩን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይኼንን እረዳለሁ፡፡ ከተወያየንባቸው ጉዳዮች አንዱ ይኼ ሲሆን፣ መንግሥት የንግድ ሚዛኑን እንዴት ሊያስጠብቅ ይችላል በሚለው ላይ ሐሳባችንን አቅርበናል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ትልቅ ፋብሪካ አለን፡፡ ለዚህ ፋብሪካ የሚያቀርቡ 300 ድርጅቶችም አሉን፡፡ ከእነዚህ አንዱን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት፣ ከደቡብ አፍሪካ እንዲያመጣ ለማድረግ ይቻል እንደሆነ እያሰብን ነው፡፡ ምሳሌ ነው፡፡ አላውቅም፡፡ ገና በሐሳብ ደረጃ ነው የተወያየንበት፡፡ ሆኖም በዚህ መንገድ መንግሥትን ማገዝና የሚሠሩትን ሥራ መሥራት እንዲችሉ መርዳት ይቻል ይሆናል፡፡ የውጭ ምንዛሪው ነገር አገሪቱ ካላት ከወጪ ንግድ ይልቅ ገቢ ንግድ ላይ ያተኮረ የንግድ ሚዛን የሚመነጭ ነው፡፡ ፎርድ ወይም ሌሎች ኩባንያዎች ብቻቸውን ሊፈቱት አይችሉም፡፡ ትንንሹ ነገር ግን ሊያግዝ ይችላል፡፡ የምንዛሪው እጥረት ግን ጎታች ነው፡፡ በወቅቱ ማግኘት አለመቻል፣ በውጭ ምንዛሪ ላይ የተመሠረተ ግብይት ለማድረግ ፈቃድ ማግኘት፣ የታዘዘውን መኪና ማስገባት ሁሉ ከባድ ነው፡፡ እያማረርኩ አይደለም፡፡ ችግሩን እረዳለሁ፡፡ መንግሥት የተለያዩ ፖሊሲዎችን ሚዛን ለማስጠበቅ እንደሚጥር እረዳለሁ፡፡ ልንረዳቸው የምንችልባቸውን መንገዶች ለማየት እንሞክራለን፡፡
ጥያቄ፡- ፎርድ ፋውንዴሽን ከአራት አሥርታት በፊት በአፍሪካ ግብርና ላይ ለውጥ ያመጣል በተለባው አረንጓዴ አብዮት ዘመቻ ላይ ድጋፍ አድርጎ ነበር፡፡ የዚህ ዓይነት ዓላማ ያለው አዲሱ አፍሪካ አረንጓዴ አብዮትም ጉባዔውን እዚህ አካሂዷል፡፡ እንዲህ ያሉ መዋቅሮችን አሁንም ትደግፋላችሁ? 
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- የፎርድ ፈንድ ኩባንያው በአፍሪካ ከሚያካሂደው ኢንቨስትመንት አኳያ ገለልተኛ ነው፡፡ የቀጣና ጽሕፈት ቤት የመክፈት አንዱ ጥቅሙም በምንሠራበት አካባቢ ያሉ ማኅበረሰቦችን ልንደግፍ የምንችልባቸውን መንገዶች በማየት ከፎርድ ፈንድ ጋር እንነጋገራለን፡፡ ምንም እንኳ ዛሬ እንዲህ ብዬ ልናገረው የምችለው ነገር ይዤ ባልመጣም፣ ድጋፍ ይሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ክፍተቶችን እናያለን፡፡ ከምንሠራበት አካባቢ ማኅበረሰብ ጋር ጥሩ ማኅበራዊ አጋርነት መመሥረትን እንፈልጋለን፡፡ ሬስ ኢንጂነሪንግም በዚህ አኳኋን ጥሩ ይሠራል፡፡ የሚደግፋቸው ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ የአዕምሮ ዕድገት ውሱንነት ላለባቸው (ኦቲዝም) ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡ የግንባታና የጥገና ዕቃዎችን ይለግሳል፡፡ ለመንገድ፣ ለሆስፒታልና ለትምህርት ቤት መገንቢያ የሚረዱ መሣሪያዎችን ይረዳል፡፡ በዚህ ተግባር በጣም እንኮራለን፡፡
ጥያቄ፡- ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ ለኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነቱ ፎርድ ምን አስቧል?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- ከተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና በጎ አድራጎት ተቋማት ጋር አጋር በመሆን እንደየአገሩ ሁኔታ በምንንቀሳቀስባቸው፣ ምርታችንን በምናቀርብባቸው፣ የጥገናና ሌሎች ሥራዎችን በምናከናውንባቸው አካባቢ የሚገኙ ማኅበረሰቦች ያሏቸውን ፍላጎቶች በማየት ድጋፍ እንሰጣለን፡፡ አንዳንዶቹ ንፁህ ውኃ፣ አንዳንዶቹ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ሌሎቹ ትምህርት፣ የሕፃናት ክብካቤ ወይም ምግብ የሚፈልጉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በማኅበረሰቡ ፍላጎት ላይ በመመሥረትና ጥሩ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለንን ነገር በማጥናት ድጋፍ እንሰጣለን፡፡ እኛ የምግብ ባንክ ወይም የትምህርት ተቋማት ሳንሆን መኪና አምራቾች መሆናችንን መርሳት የለብንም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ መስክ ከተሰማሩ ጋር አጋር በመሆን ገንዘብ፣ መኪና ወይም ሌላ ቁሳቁስ በመስጠት ድጋፍ የምናደርገው፡፡ እንደየሁኔታው የተለያየ ነው፡፡ ከኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነታችን አኳያ አንድ ነገር ላይ ያጠነጠነ የፓን አፍሪካ ስትራቴጂ የለንም፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ኃላፊነታችንን በዓለም ላይ በአግባቡ የሚያራምድ ትልቅ ተቋም አለን፡፡ ለሥራችንና ለምንሰጠው ድጋፍ ተገቢውን ውጤት እያገኘንበት ነው፡፡
ጥያቄ፡- ከሰሐራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ገበያ አኳያ የኢትዮጵያን ገበያ እንዴት ይመለከቱታል? የገበያ ድርሻውስ ምን ይመስላል?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- በዓለም ጥሩ የሚባለውን ምርት ስለምናቀርብ የኢትዮጵያ ገበያ ጥሩ ነው እንላለን፡፡ ዕድገቱ ተፈጥሯዊ እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ በግብርና ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ ያላት በመሆኑ፣ ለዚህ ዘርፍ የሚሆኑ ሬንጀር ፒካፕ መኪኖች አሉን፡፡ ትልልቅ ጭነት መጫን የሚችሉ፣ ነዳጅ የሚቆጥቡና በዋጋ ደረጃም ተመጣጣኝ በመሆናቸው ለኢትዮጵያ ግብርና ተስማሚ መሆናቸውን አይተናል፡፡ በርከት ያሉ የሬንጀር ፒካፕ መኪኖች እዚህ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውም ጥሩ ድጋፍ ለመስጠታቸው ምስክር ነው፡፡ የሥራ ተሽከርካሪዎች ናቸው፡፡ ለንግድ፣ ለአነስተኛ ቢዝነሶችና ለገበሬዎች ጥሩ ጥቅም የሚሰጡ ናቸው፡፡ ምርቶቻቸውንና የዘር ዓይነቶችን ለማጓጓዝ ምቹ መሆናቸውንና ሌሎች ጥቅሞችን ልንዘረዝር እንችላለን፡፡ ሬስ እንጂነሪንግ የግብርና ማሽነሪዎችንና ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን የሚያመጡ በመሆናቸው የሁለታችን ጥምረት መልካም እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡
ጥያቄ፡- ኢትዮጵያ በሰፋፊ የልማት ሥራዎች ላይ ትገኛለች፡፡ ለአፍሪካና ለመካከለኛው ምሥራቅ 25 አዳዲስ ምርቶችን ይፋ ልታደርጉ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ እንቅስቃሴ አኳያ እነዚህ ምርቶች ምን ትርጉም ይኖራቸዋል?
ጄፍሪ ኒሜዝ፡- ከ25 አዳዲስ ምርቶች  በተለይ 17ቱ ከሰሐራ በታች ለሚገኙ የአፍሪካ አገሮች የሚውሉ ናቸው፡፡ ከእያንዳንዱ ገበያ ፍላጎት በመነሳት ምቹ አቀራረብ እንከተላለን፡፡ በአሁኑ ወቅት ምርቶቻችንን ከምንገኝባቸው ገበያዎች ፍላጎት አኳያ በመነሳት ለማምረት እያሰብን ነው፡፡ የቀጣና ጽሕፈት ቤት አንዱ ጥቅምም ይኼው ነው፡፡ ለምርምርና ጥናት እንዲሁም ለምህንድስና ክፍሎቻችን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነዳ መኪና ከመሬት ያለው ከፍታ እንዲስተካከል እንነግራቸዋለን፡፡ ስለዚህ አሁን የቀረቡት አዳዲስ መኪኖች ጥሩ ምሳሌ ናቸው፡፡ ምንጊዜም ደንበኞች ከሚፈልጓቸው ይዘቶች በመነሳት ምርት እናመርታለን፡፡ በጣም ውስብስብ ምርቶችን በምናቀርብባቸው ገበያዎች ላይ ጥናት እናደርጋለን፡፡ ደንበኞች ምን እንደሚፈልጉ እንጠይቃቸዋለን፡፡ ወደፊት በሚገዙት መኪና ውስጥ ምን ምን እንዲካተት እንደሚፈልጉ በመጠየቅ ጥናት እናካሂዳለን፡፡ በዳሽ ቦርድ ላይ ስልክ እያስገባን ነው፡፡ ‘አፕሌክ’ የተባለውን ዘመናዊና ታዋቂነት ያተረፈውን ሥርዓት እየገጠምን ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ የሞባይል ስልኮች መኪናው ውስጥ ከተገጠሙ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በመጫን መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡
ስለዚህ በማሽከርከር ወቅት የስልክ ጥሪዎችን መቀበል ሳያስፈልግ፣ መኪና ውስጥ በማስቀመጥ ብቻ ግንኙነት ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ይህ ቴክኖሎጂ በአፍሪካ የሚተገበር ይሆናል፡፡ ለኢትዮጵያም በምናቀርባቸው ተሽከርካሪዎች ውስጥ ተገጥሞ ይመጣል የሚል ሐሳብ አለን፡፡ ለአሁኑ ግን ከወኪሎች ጋር ደንበኞች ስለሚያስፈልጓቸው ነገሮች እየተነጋገርን ነው፡፡ ወደፊት ምን ይፈልጋሉ በሚለው ላይ ጥናት እያደረግን ነው፡፡ ፎርድ ኩባንያ ምን ዓይነት ጥቅም ለኢትዮጵያ ሊያመጣ ይችላል ለሚለው የተወሰኑ ነገሮችን ማየት አለብን፡፡ እንደ ፎርድ ያሉ የኮርፖሬት እሴቶቻችን ጠንካሮች ናቸው፡፡ ከማኅብረሰቡ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለን፡፡ መንግሥት አገሪቱን መውሰድ በሚፈልግበት አቅጣጫ በኩል ድጋፍ ለማድረግም ፍላጎት አለን፡፡ በተደጋጋሚ ሚኒስትሮችን እያነጋገርን ነው፡፡ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም በአገሪቱ ውስጥ አስፈላጊ ስለሆነው ነገር የሚያስቡትን እናወያያቸዋለን፡፡ ወደ አገሪቱ ምን ማምጣት እንደምንችል እንመክራለን፡፡ 

ኤልጂ ኩባንያ አዲሱን ባለ 55 ኢንች ቴሌቪዥን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያስገባ አስታወቀ

የደቡብ ኮሪያው ኤልጂ (ላይፍ ኢዝ ጉድ) ኩባንያ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እያስተዋወቀው የሚገኘው፣ የተራቀቀና ቅንብብ ቅርጽ ያለው ባለ 55 ኢንች ቴሌቪዥን ከጥቅምት ወር ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደሚጀምር ይፋ አደረገ፡፡
ሪፖርተር ከኩባንያው ባገኘው መረጃ መሠረት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ይገባል የተባለው ይህ ቴሌቪዥን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሸጥበት ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ እስካሁን አለመወሰኑን በኢትዮጵያ የኤልጂ ኩባንያ ተወካይ ዮንግ ጊዩን ቾይ አስታውቀዋል፡፡ ይህ የሆነው ምን ያህል ታክስ እንደሚጣልበት ባለመታወቁ ነው ብለዋል፡፡ በመጪው ጥቅምት ወር አገር ውስጥ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ ቅንብብ ወይም ክበብ ቅርጽ ያለው ቴሌቪዥን በአራት ቀለማት የምስል ቅንብሮችን ለማየት የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በሁለትና በሦስት ማዕዘናት (2D and 3D) ከየትኛውም አቅጣጫ ለማየት የሚያስችል ነው ተብሎለታል፡፡ 
‹‹ኦርጋኒክ ላይት-ኢሚቲንግ ዳዮድ-ኦኤልኢዲ›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ቴሌቪዥን፣ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ለመጀመሪያ ዙር ብዛታቸው ሰባቱ እንደሚገቡም ተወካዩ አስታውቀዋል፡፡ ከምሥራቅ አፍሪካ ኬንያ ከስምንት ወራት ቀድማ የአዲሱ ቴክኖሎጂ ቴሌቪዥን መገኛ እንደሆነች መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከኬንያ በመቀጠል ይህንን ቅንጡ ቴሌቪዥን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ኤልጂ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል፡፡
ኦኤልኢዲ በክብደቱ ቀላል፣ የጎን ስፋቱ ቀጭን ከመሆኑ ባሻገር በኃይል ቆጣቢነቱ ብዙ የተባለለት አዲሱ ቴሌቪዥን፣ እዚህ የሚሸጥበት ዋጋ ባይገለጽም ለአሜሪካ ገበያ በአሥር ሺሕ ዶላር ሲቀርብ መቆየቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ኤልጂ የመጀመሪያውን ቅንብብ ቅርጽ ያለው፣ አልትራ ሃይ ዴፊኒሽን የተባለውን ይዘት በመያዝ ለሲኒማ የተመቸ ቴሌቪዥን አቅርቤያለሁ ቢልም፣ ከወደ ቻይና የሚደመጠው ደግሞ ይህንን ቴክኖሎጂ በመቀናቀን በግማሽ የቀነሰ ግን ደግሞ 55 ኢንች ቁመት ያለው ኳንተም ዶት የተሰኘ አልትራ ሃይ ዴፊኒሽን ቴሌቪዥን ይፋ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ ቲሲኤል በተባለ የቻይና ኩባንያ ተፈበረከ የተባለው ይህ ቴሌቪዥን፣ የኤልጂው ኦኤልኢዲ ከሚሸጥበት ዋጋ በአንድ ሦስተኛ ይቀንሳል የሚል መግለጫ ከቲሲኤል መውጣቱ ተሰምቷል፡፡ ኤልጂ ባለፈው ዓመት ሁለተኛ መንፈቅ ላይ በአሜሪካ ይፋ ያደረገው ኦኤልኢዲ ቴሌቪዥን፣ ከ500 ያላነሰ ብዛት ሊሸጥ መቻሉም ታውቋል፡፡

የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ

Photo: የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ::

አንጀሊና ጆሊ ኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር የሆነችበትና ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም፣ በፍርድ ቤት እግድ ከተቋረጠ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማስነሳቱ ታወቀ፡፡ 

በአሜሪካ በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ ከሆነ በኋላ የፊልሙ በአዲስ አበባ መመረቅ በብዙዎች በጉጉት እየተጠበቀ ነበር፡፡ እንዲህ የተጠበቀው ፊልም ሊመረቅ በታሰበበት ዕለት ከአሥራ አምስት ደቂቃዎች በላይ ሊታይ አልቻለም፡፡ በብሔራዊ ቴአትር እየታየ ፌደራል ፖሊስ ደርሶ ሊያቋርጠው የግድ ሆኗል፡፡

ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያጠነጥነው አስገድዶ የደፈራትን የ29 ዓመት ወጣት በገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ አበራሽ በቀለ (በፊልሙ ሒሩት) ሕይወት ዙሪያ ነው፡፡ ደፋሪዋ ሕፃኗን በጠለፋ ሊያገባትም ሙከራ አድርጐ ነበር፡፡ 

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር መሥራች የሆኑት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ጉዳዩን ሰምተው ጥብቅና ቆመውላት ራስን ለመከላከል በሚል በነፃ እስከተለቀቀችበት ጊዜ ድረስ፣ አበራሽ በግድያ ክስ ተመሥርቶባት ማረሚያ ቤት ነበረች፡፡ 

በአቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ መሐሪ የተጻፈውና ዳይሬክት የተደረገው ይህ ፊልም በዚህ ዓመት በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ መሆኑን ተከትሎ፣ የታሪኩ ባለቤት በሆነችውና ፈቃደኝነቷን እንዳልተጠየቀች በምትናገረው ወ/ሪት አበራሽና የወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ወንድምና የታሪኩ ጸሐፊ ነኝ በሚሉት አቶ ፍቅሩ አሸናፊ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡ 

የፍርድ ቤት እግዱ እንደሚያሳየው በከሳሽነት የቀረቡት አቶ ፍቅሩ አሸናፊና ወ/ሪት አበራሽ በቀለ ሲሆኑ፣ ተከሳሾቹ ደግሞ አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ፣ ኃይሌ አዲስ ሥዕሎች ድርጅትና ትሩዝ ኤይድ ሚዲያ ድርጅት ናቸው፡፡

ክሱ እንደሚያስረዳው ድፍረት የተሰኘው ፊልም ተመርቆ ለሕዝብ ዕይታ ቢውል በከሳሾች ሞራላዊና ኢኮኖሚያዊ መብት ላይ የማይተካ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል በመገንዘብ፣ ፍርድ ቤቱ ፊልሙ ለሕዝብ ዕይታ እንዳይውል ወይም እንዳይመረቅ ጭምር እገዳ ጥሏል፡፡ በተጨማሪም በተከሳሾች ላይ ሊደርስ ለሚችል ኪሳራ ከሳሾች 50 ሺሕ ብር በዋስትና አስይዘዋል፡፡

ወ/ት አበራሽ እንደምትለው ፊልሙ በርሊን እስከተመረቀበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት መረጃ አልነበራትም፡፡ ከሰባት ወራት በፊት ግን አቶ ዘረሠናይን አግኝታው በፊልሙ ላይ ዕውቅና እንዲሰጣት፣ የተወሰነ ገንዘብም እንዲከፍላት እንደምትፈልግ ገልጻለት የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ 

የፊልሙ ሥራ የእሷን ደኅንነት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይደለም በማለት የምትወቅሰው ወ/ት አበራሽ፣ ምንም እንኳ ሁኔታውን ለማስረዳት ብትሞክርም ከአቶ ዘረሠናይ በመጨረሻ ያገኘችው መልስ አዎንታዊ አለመሆኑን ትናገራለች፡፡ ‹‹ከተፈጠረው ነገር ጋር በተያያዘ የምኖረው ተደብቄ ነበር፡፡ ይኼ ፊልም ግን ታሪኩን እንደ አዲስ ቀስቅሶ የእኔንም የቤተሰቦቼንም ሕይወት አደጋ ላይ ጥሎታል፤›› ትላለች፡፡

ወ/ት አበራሽ የደፈራትን ሰው ከገደለች በኋላ በኦሮሞ የእርቅ ባህል ጉማ መሠረት ቤተሰቦቿ ካሳ ከፍለው ነገሩ ተቋጭቶ ነበር፡፡ በስምምነቱ መሠረት እሷም ቀዬዋን ጥላ ለመውጣት ተስማምታ እንደነበር የምትናገረው አበራሽ፣ ‹‹በባህሉ መሠረት ሴት ገድላ ካሳ መክፈል አትችልም፡፡ ስለዚህም ወደ አካባቢዬ እንዳልመለስ የሟች ቤተሰቦች ያስጠነቀቁኝን በመስማትና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስል ለዓመታት እዚያ ሳልደርስ ቀረሁ፤›› ብላለች፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን ለማገዝ የሚሠራ ሀረም በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ በመሥራት ላይ የምትገኘው ወ/ት አበራሽ፣ በሕይወቷ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈች ትናገራለች፡፡ የትውልድ ቦታዋ ቀርሳ አርሲን የለቀቀችው ወ/ት አበራሽ ሁለተኛ ደረጃ እስክትደርስ የኖረችው ቀጨኔ ሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ነበር፡፡ ታሪኳ ተካትቶ በተሠራ ዘጋቢ ፊልም አማካይነት ታገኝ የነበረው ገንዘብ ኮሌጅ ስትገባ መቋረጡን ታስታውሳለች፡፡ ስለዚህም በነበረባት የገንዘብ ችግር የኮሌጅ ትምህርቷን ለማቋረጥ መገደዷን፣ ከዚያም ወደ ዱባይ እስከሄደችበት ጊዜ ድረስ በአንድ ትንሽ የፊልም ሲዲ ማከራያ ሱቅ ውስጥ መሥራቷን ለሪፖርተር ገልጻለች፡፡ 

አቶ ዘረሠናይ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ እንደተናገረውና አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት ስለታሪኩ መጀመሪያ አቶ ዘረሠናይ የነገረው ለእርሳቸው ነው፡፡ ይህ የሆነው እ.ኤ.አ. በ2005 ሲሆን፣ አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት የፊልሙ ሐሳብ የተወሰደው ከእሳቸው በመሆኑ ፊልሙን በጋራ ለመሥራት አስበው ነበር፡፡ ‹‹ከ2008 በኋላ አቶ ዘረሠናይ እኔን ለማናገር አልፈለገም፡፡ እንዲያውም ይደበቀኝ ጀመር፤›› ይላሉ፡፡

የፊልሙን መሠራት ሲጠባበቁና ነገሮችን ሲከታተሉ እንደነበር፣ የአበራሽን ይሁንታም እንዳገኙ አቶ ፍቅሩ ይናገራሉ፡፡ አቶ ዘረሠናይ ግን ለእሷም ለእሱም የታሪኩ ሐሳብ ባለቤት እንደመሆኑ ዕውቅና ሳይሰጥ መቅረቱን ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ያለሷ ታሪክ ፊልሙ አይሠራም ነበር፡፡ ባትደፈር፣ በጥንካሬ ደፋሪዋን ባትገድለው ኖሮ ታሪክ አይኖርም ነበር፤›› ይላሉ አቶ ፍቅሩ፡፡

በፊልሙ ውስጥ ሌላ ባለታሪክ የሆኑትና በወቅቱ የ14 ዓመቷ ታዳጊ ጠበቃ የነበሩት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለፊልሙ ዳይሬክተር ታሪካቸው በፊልሙ እንዲካተት ፈቃድ መስጠታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ያደረጉት ታሪኩ በፊልም መሠራቱ የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ጥያቄን ያራምዳል፣ ስለጠለፋና ስለጥቃት ግንዛቤ ለመፍጠር ያስችላል በሚል እንጂ ‹‹የእኔ ታሪክ ይነገር›› በሚል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ 

ለአበራሽ ጥብቅና በቆሙላት ጊዜ ከዚያም በኋላ አበራሽ በመኖሪያ ቤታቸው ተቀምጣ እንደነበር ቅርበትም እንደነበራቸው የሚያስታውሱት ወ/ሮ መዓዛ፣ ለረዥም ዓመታት ግን ከአበራሽ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖራቸው እንደቆዩም ይናገራሉ፡፡ 

ከፊልሙ መሠራት በኋላ ግን የታሪካቸው በፊልም መሠራት ለአበራሽ የሚከፍተው የዕድል በር ይኖራል በሚል ማፈላለግ መጀመራቸው የሚናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ስለጉዳዩ በነገሯት መሠረት በመጨረሻ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ደራርቱ ቱሉ የአበራሽን ስልክ ቁጥር እንደሰጠቻቸውና እንዳገኙዋት ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ 

‹‹ደውዬ ወደ አዲስ አበባ አስመጣኋት፡፡ አሁንም ያለችው እናቴ ቤት ነው፡፡ የእኔ ቤት ወጣ ስለሚል ነው እዚያ እንድትቀመጥ ያደረግኩት፡፡ ከመጣች ወደ ሰባት ወራት ገደማ ሆኗል፤›› የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፣ ወ/ት አበራሽን አሁን እየሠራችበት ያለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንድትቀጠር ያደረጉት እሳቸው እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ 

ወ/ሮ መዓዛ እንደገለጹት ወ/ት አበራሽ ወደ አዲስ አበባ እንድትመጣ ያደረጉት ፊልሙ ጀርመን በርሊን ውስጥ ሊመረቅ በተቃረበበት ጊዜ ነበር፡፡ 

ለታሪኳ ባለቤት ወ/ት አበራሽ በፊልሙ ሥራ ተሳታፊ ከሆኑት ግለሰቦች ሁሉ ቅርበት ያላት እርሷ እንደመሆኗ የታሪኳ ባለቤት ተጠቃሚነትን በሚመለከት ለወ/ሮ መዓዛ ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹መጠቀም እንዳለባት አምናለሁ፡፡ አቶ ዘረሠናይም በዚህ ያምናል፡፡ ይህን ለማድረግም በጣም ፈቃደኛ ነው፡፡ እሷም የምትጠብቀው ነገር አለ፡፡ ችግር የፈጠረው እንዴት በሚለው ላይ አለመነጋገር ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

ወንድማቸው አቶ ፍቅሩ አሸናፊም ፊልሙ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን በሚመለከት፣ ወንድማቸውና የድፍረት ፊልም ዳይሬክተርና ከፕሮዲዩሰሮቹ መካከል አንዱ የሆነው አቶ ዘረሠናይ ምንም እንኳ የጓደኝነታቸውን ደረጃ መናገር ባይችሉም፣ ጓደኛማቾች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ወንድማቸው ስለ እርሳቸው ለጓደኛው አቶ ዘረሠናይ ሲያወሩ የፊልም ባለሙያ የሆነው አቶ ዘረሠናይም ታሪኩን ወደ ፊልም ለመቀየር ትልቅ ፍላጐት እንዳደረበትና የፊልሙ መነሻ እንዲህ እንደነበር፣ ከዚህ ውጪ ግን በወንድማቸውና በአቶ ዘረሠናይ መካከል ሌላ ጉዳይ ይኑር አይኑር የሚያውቁት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡ ግጭቱ ቀላል እንደሆነ ስለዚህም በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው አክለዋል፡፡ 

የፊልሙ ዳይሬክተር አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ በእጁ ላይ ያለው የፍርድ ቤት እግድ ብቻ በመሆኑ ስለክሱ ዝርዝር ነገር ሳያውቅ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይፈልግ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡ የባለታሪኳ ወ/ሮ አበራሽ ፈቃድን ማግኘት አለማግኘቱን በተመለከተም አቶ ዘረሠናይ ምንም ማለት አለመፈለጉን ገልጿል፡፡ ጠበቃው ዓርብ ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የክሱን ቻርጅ ለማግኘት ፍርድ ቤት እንደነበሩና የክሱን ዝርዝር እንዳወቁ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ዓርብ እኩለ ሌሊት ድረስ ከእሱ በኩል የተሰማ ነገር አልነበረም፡፡ 

የፊልሙ እግድ ለብሔራዊ ቴአትር ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. አሥራ አንድ ሰዓት ላይ መድረሱን ከሳሾች ቢጠቁሙም፣ የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ እግዱ የደረሰው አሥራ አንድ ሰዓት ከሃያ አምስት ላይ እንደነበር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት እግዱ በደረሰበት ወቅት 1,200 ያህል እንግዶች አዳራሹ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አሥር ያህሉ አምባሳደሮችና ባለሥልጣናት ነበሩ፡፡ በአሳጋጆቹ በኩል የነበረው አቀራረብ አስቸጋሪ ስለነበርና በሌላኛውም በኩል ፊልሙን ለማቋረጥ ያለመፈለግ ነገር ስለነበር፣ በአጋጣሚው የአገር ገጽታ እንዳይበላሽ በጥንቃቄ ለመያዝ ቴአትር ቤቱ የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል ብለዋል፡፡

‹‹የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይከበራል፡፡ ይህ ምንም ዓይነት ጥያቄ የለውም፡፡ ነገር ግን በሁሉቱም በኩል የነበረው ነገር ወደ ግጭት የሚያመራ ዓይነት ስለነበር ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ፖሊስ ጠርተናል፡፡ ምክንያቱም እኛ ያለን የፀጥታ ኃይል ያን ማድረግ አይችልም ነበር፤›› ሲሉ አቶ ተስፋዬ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡
            
 አንጀሊና ጆሊ ኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር የሆነችበትና ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም፣ 
በፍርድ ቤት እግድ ከተቋረጠ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማስነሳቱ ታወቀ፡፡

በአሜሪካ በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ ከሆነ በኋላ የፊልሙ በአዲስ አበባ መመረቅ በብዙዎች በጉጉት እየተጠበቀ ነበር፡፡ እንዲህ የተጠበቀው ፊልም ሊመረቅ በታሰበበት ዕለት ከአሥራ አምስት ደቂቃዎች በላይ ሊታይ አልቻለም፡፡ በብሔራዊ ቴአትር እየታየ ፌደራል ፖሊስ ደርሶ ሊያቋርጠው የግድ ሆኗል፡፡

ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያጠነጥነው አስገድዶ የደፈራትን የ29 ዓመት ወጣት በገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ አበራሽ በቀለ (በፊልሙ ሒሩት) ሕይወት ዙሪያ ነው፡፡ ደፋሪዋ ሕፃኗን በጠለፋ ሊያገባትም ሙከራ አድርጐ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር መሥራች የሆኑት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ጉዳዩን ሰምተው ጥብቅና ቆመውላት ራስን ለመከላከል በሚል በነፃ እስከተለቀቀችበት ጊዜ ድረስ፣ አበራሽ በግድያ ክስ ተመሥርቶባት ማረሚያ ቤት ነበረች፡፡

በአቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ መሐሪ የተጻፈውና ዳይሬክት የተደረገው ይህ ፊልም በዚህ ዓመት በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ መሆኑን ተከትሎ፣ የታሪኩ ባለቤት በሆነችውና ፈቃደኝነቷን እንዳልተጠየቀች በምትናገረው ወ/ሪት አበራሽና የወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ወንድምና የታሪኩ ጸሐፊ ነኝ በሚሉት አቶ ፍቅሩ አሸናፊ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡

የፍርድ ቤት እግዱ እንደሚያሳየው በከሳሽነት የቀረቡት አቶ ፍቅሩ አሸናፊና ወ/ሪት አበራሽ በቀለ ሲሆኑ፣ ተከሳሾቹ ደግሞ አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ፣ ኃይሌ አዲስ ሥዕሎች ድርጅትና ትሩዝ ኤይድ ሚዲያ ድርጅት ናቸው፡፡

ክሱ እንደሚያስረዳው ድፍረት የተሰኘው ፊልም ተመርቆ ለሕዝብ ዕይታ ቢውል በከሳሾች ሞራላዊና ኢኮኖሚያዊ መብት ላይ የማይተካ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል በመገንዘብ፣ ፍርድ ቤቱ ፊልሙ ለሕዝብ ዕይታ እንዳይውል ወይም እንዳይመረቅ ጭምር እገዳ ጥሏል፡፡ በተጨማሪም በተከሳሾች ላይ ሊደርስ ለሚችል ኪሳራ ከሳሾች 50 ሺሕ ብር በዋስትና አስይዘዋል፡፡

ወ/ት አበራሽ እንደምትለው ፊልሙ በርሊን እስከተመረቀበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት መረጃ አልነበራትም፡፡ ከሰባት ወራት በፊት ግን አቶ ዘረሠናይን አግኝታው በፊልሙ ላይ ዕውቅና እንዲሰጣት፣ የተወሰነ ገንዘብም እንዲከፍላት እንደምትፈልግ ገልጻለት የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

የፊልሙ ሥራ የእሷን ደኅንነት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይደለም በማለት የምትወቅሰው ወ/ት አበራሽ፣ ምንም እንኳ ሁኔታውን ለማስረዳት ብትሞክርም ከአቶ ዘረሠናይ በመጨረሻ ያገኘችው መልስ አዎንታዊ አለመሆኑን ትናገራለች፡፡ ከተፈጠረው ነገር ጋር በተያያዘ የምኖረው ተደብቄ ነበር፡፡ ይኼ ፊልም ግን ታሪኩን እንደ አዲስ ቀስቅሶ የእኔንም የቤተሰቦቼንም ሕይወት አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ትላለች፡፡

ወት አበራሽ የደፈራትን ሰው ከገደለች በኋላ በኦሮሞ የእርቅ ባህል ጉማ መሠረት ቤተሰቦቿ ካሳ ከፍለው ነገሩ ተቋጭቶ ነበር፡፡ በስምምነቱ መሠረት እሷም ቀዬዋን ጥላ ለመውጣት ተስማምታ እንደነበር የምትናገረው አበራሽ፣ በባህሉ መሠረት ሴት ገድላ ካሳ መክፈል አትችልም፡፡ ስለዚህም ወደ አካባቢዬ እንዳልመለስ የሟች ቤተሰቦች ያስጠነቀቁኝን በመስማትና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስል ለዓመታት እዚያ ሳልደርስ ቀረሁ፤ ብላለች፡፡