Tuesday, December 9, 2014

ሴትን ልጅ በፍቅር ለማማለል እንዴት ማናገር ይሻላል?




ውድ ታደሰ ችግርህ ችግራችን ብለን እነሆ ተከታዩን ምላሽ አዘጋጅተናል፡፡ ብዙ ጊዜ በራሳቸው ሀሳቦች ሙሉ በሙሉ የተዋጡ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ለሰዎች ትኩረት የሚሰጡ ሰዎችን እንዲያዳምጡን ለማድረግ ይቸግረናል፡፡ ምክንያቱ ምናልባት የእኛ አንጀት ርቱዕ አለመሆን ወይንም ቀልብ የመሳብ ብቃት አንሶን ሊሆን ይችላል፤ የሆነው ሆኖ ቁም ነገሩ ይህ አይደለም፡፡ ቁም ነገሩ እንዲሰሙን ወይንም እንዲያዳምጡን ማድረግ መቻል ነው፡፡ ግን እንዴት?
የጨዋታችን ዋነኛ አላማ የፍቅር ሰለባን በእጅ ውስጥ ማስገባት ነው፤ ሰለባን ለመቆጣጠርም ተደማጭነትን ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ተመራጭ ነገር ነው፡፡ የሚደመጡ ወይንም ሌሎች ትኩረት የሚያደርጉባቸው ሰዎች ደግሞ ርቱዕ አንደበትን የተጎናፀፉ፤ ለሌሎች መልካም ስሜት ያላቸው ወይንም ቀና አሳቢዎች ብቻ ናቸው ካልን ተሳስተናል፡፡ ባህሪያቸው ያዝ ለቀቅ የሆነና ከየትኛውም ሰው ጋር የማይገጥም አፈጣጠር ያላቸው ሰዎች እንዲያውም ጉልህ በሆነ ሁኔታ ትኩረታችን ከመሻማታቸው በዘለለ በፍቅር እንድንጦፍላቸው ሊያደርጉን ይችላሉ፤ ለምን ከተባለም ምን ጊዜም የሰው ልጅ አእምሮ ግልፅ ያልሆነለትን ወይም ግራ ያጋባውን ነገር ለመረዳት ወይም ለማወቅ ያለው ጉጉት ከልክ ያለፈ በመሆኑ ነው፡፡ ታዲያ መች ያለ ምክንያት ሆነ ሁለት ፍፁም ተቃራኒ ባህሪን የያዙ ጥንዶች በአንድ ጣራ ስር በፍቅር የአብሮነት ዘመናቸውን የሚያሳልፉት?!
ሰለባህን በጣፋጭ ቃላት ማማለል አንደኛው ዘዴ ሊሆን ይችላል፤ ጣፋጭ ቃላትን ተጠቅሞ መቅረትም ትክክል አይደለም፤ ጣፋጭ ቃላቱን በመራራ ቃላት ለውሶ ግራ ማጋባት እንዲሁም ጠቃሚ ሀሳቦችን ነካክቶ በመተው ፍላጎት እንዲንር ማድረግ እጅግ አደገኛ የማማለያ መንገድ ነው፡፡
ማወቅ ያለብህ ቁልፍ ነገር
ማውራት ከመጀመራችን በፊት ስለምናወራው ነገር አስቀድመን የምናስብ እጅግ ጥቂቶች ነን፡፡ ለዚህም ነው አብዛኞቻችን በጭንቅላታችን ውስጥ ፈጥኖ የመጣውን ወዲያውኑ በምላሳችን የምናስተጋባው፤ በዚህም መሰረት የምንናገራቸው ነገሮች ከራሳችን ፍላጎትና ምቾት አንፃር የመነጩ ይሆናል፡፡ ሁኔታውን ከሰው ልጅ ተፈጥሯዊ የራስ ወዳድነት ባህሪ ነው ልንለውም እንችላለን፤ የሆነው ሆኖ ሁኔታው የፍቅር ወጥመድ የጉዞ ብቃትና ሃይልን የሚያሳንስ መሆኑን ማመን ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰዎችን በፍቅር ማማለል የሚቻለው በመናገር ብቃት አሊያም በድምፅ ዜማዊ ቅኝትን በመጠቀም ብቻ አይደለም፤ እንዲያውም ቆም ብሎ ማሰብና ወጥመዱን በመዘርጋት ሂደት ጊዜን በመሰዋት መጓዝ ከየትኞቹም የማማለያ ስልቶች ሁሉ የላቀ ነው፡፡ ምን ጊዜም በአእምሮህ የሚመጣውን ሀሳብህን ወዲያው ለመናገር የምትፈጥን ከሆነ ማንነትህን አንድም ሳታስቀር ለሌሎች እየነገርክ ከመሆንህም በተጨማሪ ራስ ወዳድ መሆንህንም አመላካች ነው፡፡ ሁኔታው ግልፅነት ነው ብለህም ራስህን ማታለል የለብህም፤ ምን ጊዜም ከራስህ ለራስህ ብቻ የሚቀር የውስጥ ባህሪ ማስቀረት መቻል የፍቅርን ወጥመድ ውጤታማ የሚያደርግ ነገር ነው፡፡ ግልፅነት መልካም ነገር ቢሆንም የተጋነነ የግልጽነት ባህሪ ግን በዚህ ሁኔታ የማይጠቅም ሲሆን በስተመጨረሻ የራስ የሆነ ነገር እንደሌለህ ሁላ እንዲሰማህ ሊያደርግ ይችላልና መጠንቀቀ ተገቢ ነው፡፡
በንግግር ወቅት ጤነኛ ቋንቋንና የማማለያ ቋንቋ በምትጠቀምበት ሂደት ጥንቃቄ ማበጀት እጅግ የሚመከር ጉዳይ ነው፡፡ ከእናትህ ጋር የምትጠቀምበት የንግግር ለዛ አሊያም ዘይቤ ለታዳኝህ ይሆን ዘንድም ልትጠቀምበት አይገባም፤ እናትህና ታዳኝህ የተለያዩ ሰዎች ከመሆናቸውም በተጨማሪ እነርሱን የምትቀርብበት ዓላማም የተለያየ ነውና፡፡ ብዙዎቻችን ግን ከእናቶቻችን ጋር በምናወራበት መንገድ ወይም ቤተሰባዊ ቋንቋን በውጭው ዓለም (በተለይም በፍቅር) ግንኙነታችንም ልንጠቀምበት ስለምንሞክር ብዙም ሳንራመድ ውድቀት ያጋጥመናል፡፡
ቤተሰባዊ (normal) ቋንቋ የሚባለው ብዙውን ጊዜ አማላይነት የሌለውና ተራ ድምፅ ወይንም ‹‹noise›› የምንለው አይነት ሲሆን ትኩረትን የማይስብና ትኩረት የማይደረግበት ነው፡፡ በዚህ አይነቱ የንግግር ግንኙነታችን ሰዎች የምንለውን ሊሰሙ ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አያዳምጡንም፡፡ ሳያዳምጡ በፍቅር ማማለል ደግሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው ቤተሰባዊ ወይንም ‹‹ኖርማል›› ቋንቋን በዚህ ሂደት መጠቀም አያዋጣም የሚባለው፡፡ ስለሆነም ኖርማል ቋንቋን በርዞ አማላይነትን ማጎናፀፍ ከአጥማጁ የሚጠበቅ ሲሆን ይህን ለማድረግ ልክ እንደ አብዛኞቻችን የሚመጣልንን ከመናገር መቆጠብና ለእያንዳንዷ ጥቃቅን ጉዳይ ትኩረት መስጠትን መለማመድ ነው፤ አንዳንድ ሰዎችን ከሌሎች የተለዩና ተወዳጅ የሚያደርጋቸውም ይህ ባህሪያቸው ነው፡፡ በተፈጥሮ ባህሪያቸው ላይ ሰው ሰራሽ ባህሪያትን በመጨመር ህብረ ባህሪው እንዲብለጨለጭና የአብዛኞቻችን አይን (ቀልብ) እንዲያነጣጥርበት ያደርጉታል ማለት ነው፡፡ ታዳኝን በቀላሉ በወጥመድ ሊያስገቡ ከሚያስችሉት መንገዶች መካከልም አንዱ ይኸው ነው፡፡
እንደምናውቀው ሙዚቃ የማንኛችንም አዕምሮ የመጠምዘዝ ሃይል አለው፣ ሙዚቃ ማለት ደግሞ በሙዚቃ መሳሪያ የተቀነባበረ ጥዑም ዜማ ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ቃላትን አጣፋጭ ቅመማት ሲሞጅሩባቸው ሙሉ ሙዚቃ መሆን ይችላሉ፣ ስለሆነም ሙዚቃ አይነቱ ብዙ ሲሆን አንዱ ገፅታቸውም የገለፅነው የቃላት ዜማዊ ቅኝት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች አንዳንድ ቃላትን እንደፈለጉት በምላሳቸው የሚደፈጥጧቸው ወደው ሳይሆን ከፍጭቱ የሙዚቃ ዜማን ይፈጥሩላቸው ዘንድ ነው፡፡ ሙዚቃም ሌላ አይነት የድርጊት ገፅታ አለው፤ ቃላት የሰዎችን ስሜት በሚያነሳሳ መልኩ መጠቀምም ግለሰቦቹ ወይንም ታዳኞች ለሙዚቃ የሚሰጡትን ትኩረት ያህል ለንግግሩ ይሰጣሉ፡፡ ሙዚቃ ሲያጥርና አንዴ ተሰምቶ ፈጥኖ ሲያልቅ ጣፍጦና ተናፍቆ እንደሚቀረው ሁሉ ሙዚቃዊ ቅኝት የሰጧቸውን ቃላትም ተናፋቂ አድርጎ ዘወር ማለት የወጥመዱ ትክክለኛ አካሄድ ነው፡፡ ምክንያቱም ታዳኞቹ የቃላት ሙዚቃውን እንደገና ለማድመጥ በሚያደርጉት ፍለጋ ወይም ጥረት ፈጥነው በወጥመዱ ውስጥ ይገባሉና ነው፡፡
ሌላው ኢ-ቀጥተኛ የሆነው የማማለያ መንገድ (anti-seduction) ወይንም ቴክኒክ ከልክ ያለፈ ተነታራኪ መሆን ነው፡፡ ንትርክ አሰልቺ በመሆኑ ምክንያት በሌሎች ሰዎች ዘንድ በቶሎ እንድንጠላ ሊያደርግ ይችል ይሆናል፤ ሁኔታው ሲደጋገም ግን ትኩረትን ያሰጣል፤ በተለይም ተነታራኪነቱ ከምክንያታዊነትና ከጨዋታ ጋር የተዋጀ ከሆነ በሌሎች ዘንድ ተናፋቂ የሚሆን ክስተት ነው፡፡
በ19ኛው ክፍለ ዘመን የእንግሊዝ ፓርላማ አባል የነበረው ፖለቲከኛው ቤንጃሚን ዲስራኤሊ በዚህ አይነቱ ተጨቃጫቂ ባህሪ ነበር የሚታወቀው፡፡ ዲስራኤሊ ከፓርላማው አባላት ከአንዱም ጋር የማይጣጣም ሲሆን ባህሪውን ግን ሁሉም የፓርላማው ሰዎች ይወዱለት ነበር አሉ፤ ምክንያቱ ደግሞ ዴስራኤሊ ክርክሩን የሚሰነዝረው መጀመሪያ ሁሉንም ካዳመጠ በኋላና የትኛውን ሀሳብ በየትኛው መንገድ በተለይም ሰዎችን በሚያስቅና በሚያዝናና ሁኔታ መምታት እንዳለበት ካወጣና ካወረደ በኋላ ነው፡፡ ዲስራኤሊ ይህን ካደረገ በኋላ በወሬና በሳቅ እያዋዛ የጓደኞቹን ንግግር ቀስ እያደረገ ማውጋቱን የሚቀጥል ሲሆን ንግግሩንም በትኩረት ያዳምጡታል፡፡ ሰውየው አሰልቺና ጥቃቅን ስህተቶችን የማያልፍ ቢሆንም ችግሮችን ወይንም እርሱ የማይቀበላቸውን ነገሮች የሚነቅፍበት መንገድ ኪነጥበባዊ በመሆኑ ምክንያት ግን ሁሉም እንዲወዱት ያደርግ ነበር፡፡
በአጠቃላይ ወጣ ገባ እያለ ግራ የሚያጋባ፣ እንደጉም ምስል ታይቶ የሚጠፋ፤ እንደገናም የሚከሰት አወዛጋቢ ባህሪ እጅግ አደገኛው የማማለያ ስልት ነው፡፡ በዚህ ሂደት ታዲያ ዘዴውን ትክክለኛ በሆነ መንገድ መግለፅ ተገቢ ነው፤ ልታወራቸው የሚገቡህ ነጥቦች ስለ ጓደኝነት ወይም ተቃራኒ ሃሳብን የምታንፀባርቅባቸው ተመሳሳይ ሃሳቦች ሳይሆን ስለ ፍቅርና ጥላቻ በማፈራረቅ ማውራት ይኖርብሃል፡፡ በእነኚህ ጉዳዮች ላይ የሚኖርህ የጨዋታ ሁኔታ መውጠንጠን ያለበትም ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ተጠማጁ ላይ መሆን ይኖርበታል፤ በተለይ ደግሞ ታዳኝህ ስለፍቅር አንድ ሀሳብ ካለው አንተ ሀሳቡን በማጣጣል የክርክሩን ድባብ አጧጡፈው፣ ታዳኝ ሳይሆን የታዳኝ ሀሳብን የሚያጥላላ ንግግር መጨመርም ጥቅም አለው፤ እዚህ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ የሚኖርብህ ይሆናል፤ በተለይም የሰዎችን ሀሳብ ለማጣጣል በምትሞክርበት ወቅት ፍፁም ጥላቻን የሚያንፀባርቅ ሀሳብ በአንተ ላይ ፍፁም ጥላቻን ሊያደርስብህ ይችላልና ነው፡፡ ቁም ነገሩ የምትናገረው ነገር ሁሉ ከየትኛው ጎራ እንደሚመደብ ግልፅ ያልሆነ ወይንም እንቆቅልሽ መሆኑ ነው፤ እንቆቅልሹ እንቆቅልሽ ሆኖ በታዳኝ ፊት መቅረብ ይኖርበታል እንጂ የእንቆቅልሹን መልስ አንተው መልሰህ መገኘት አይኖርብህም፡፡ ሁሉም ነገርህ ለታዳኝ የቤት ስራ መሆኑ ጥረቱን፣ ፍላጎቱንና ፍቅሩን የሚያንረው ይሆናል፡፡
ስለሆነም አንተም ከላይ የጠቃቀስካቸውን ሀሳቦች በሀሳብህ አሳድረህ፤ የተመለከቱትንም መፍትሄዎች ከተገበርክ መፍትሄ የምታገኝ ይመስለኛል፡፡ የትኛውንም ሴት ማናገር ብቻ ሳይሆን በፍቅርም መጣል ትችላለህ፡፡ መልካም ዕድል፤ ሰላም!
Source:http://www.tenaadam.com
አዲስ አበባ ህዳር 30/2007 ካለፈው ዓርብ ጀምሮ የሞባይል ተጠቃሚዎች ያጋጠማቸው የቅድመ ሂሳብ ክፍያ መሙላትና የመደወል ችግር እየተፈታ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ የሞባይል ተጠቃሚዎች "ችግሩ ተባብሶ ከመቀጠል ውጭ ምንም አይነት መሻሻል አላሳየም"ይላሉ።
የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለኢዜአ በስልክ እንደገለፁት ችግሩ የተፈጠረው ከሂሳብ መሙላትና ተጓዳኝ አገልግሎት ከመስጠት ጋር ተያይዞ አሮጌውን ሲስተም ወደ አዲስ በመቀየር ሂደት ነው።
የጥሪና ቅድመ ክፍያ ሂሳብ የመሙላት ችግር የሚስተዋልባቸው የሞባይል መስመሮች በ0911፣12፣14፣18፣20፣25፣34፣35፣36፣37 እና 42 የሚጀምሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ሲስተሙ ከአንድ እስከ ሁለት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቀጣይም ችግሩ አልፎ አልፎ ሊስተዋል እንደሚችል ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ የሞባይል ደንበኞች ችግሩ ቀስ በቀስ በመቃለል ላይ መሆኑ ቢገለፅም፤ በሞባይል የሚደረገው ግንኙነት፣የቅድመ ሂሳብ ክፍያ መሙላት እንዲሁም ሂሳብ ጠይቆ ማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ በመግለጽ ላይ ናቸው።
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/social/item/255-2014-12-09-20-50-12#sthash.MPl8sFDA.dpuf
አዲስ አበባ ህዳር 30/2007 ካለፈው ዓርብ ጀምሮ የሞባይል ተጠቃሚዎች ያጋጠማቸው የቅድመ ሂሳብ ክፍያ መሙላትና የመደወል ችግር እየተፈታ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ የሞባይል ተጠቃሚዎች "ችግሩ ተባብሶ ከመቀጠል ውጭ ምንም አይነት መሻሻል አላሳየም"ይላሉ።
የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለኢዜአ በስልክ እንደገለፁት ችግሩ የተፈጠረው ከሂሳብ መሙላትና ተጓዳኝ አገልግሎት ከመስጠት ጋር ተያይዞ አሮጌውን ሲስተም ወደ አዲስ በመቀየር ሂደት ነው።
የጥሪና ቅድመ ክፍያ ሂሳብ የመሙላት ችግር የሚስተዋልባቸው የሞባይል መስመሮች በ0911፣12፣14፣18፣20፣25፣34፣35፣36፣37 እና 42 የሚጀምሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ሲስተሙ ከአንድ እስከ ሁለት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቀጣይም ችግሩ አልፎ አልፎ ሊስተዋል እንደሚችል ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ የሞባይል ደንበኞች ችግሩ ቀስ በቀስ በመቃለል ላይ መሆኑ ቢገለፅም፤ በሞባይል የሚደረገው ግንኙነት፣የቅድመ ሂሳብ ክፍያ መሙላት እንዲሁም ሂሳብ ጠይቆ ማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ በመግለጽ ላይ ናቸው።
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/social/item/255-2014-12-09-20-50-12#sthash.MPl8sFDA.dpuf
አዲስ አበባ ህዳር 30/2007 ካለፈው ዓርብ ጀምሮ የሞባይል ተጠቃሚዎች ያጋጠማቸው የቅድመ ሂሳብ ክፍያ መሙላትና የመደወል ችግር እየተፈታ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ የሞባይል ተጠቃሚዎች "ችግሩ ተባብሶ ከመቀጠል ውጭ ምንም አይነት መሻሻል አላሳየም"ይላሉ።
የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለኢዜአ በስልክ እንደገለፁት ችግሩ የተፈጠረው ከሂሳብ መሙላትና ተጓዳኝ አገልግሎት ከመስጠት ጋር ተያይዞ አሮጌውን ሲስተም ወደ አዲስ በመቀየር ሂደት ነው።
የጥሪና ቅድመ ክፍያ ሂሳብ የመሙላት ችግር የሚስተዋልባቸው የሞባይል መስመሮች በ0911፣12፣14፣18፣20፣25፣34፣35፣36፣37 እና 42 የሚጀምሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ሲስተሙ ከአንድ እስከ ሁለት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቀጣይም ችግሩ አልፎ አልፎ ሊስተዋል እንደሚችል ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ የሞባይል ደንበኞች ችግሩ ቀስ በቀስ በመቃለል ላይ መሆኑ ቢገለፅም፤ በሞባይል የሚደረገው ግንኙነት፣የቅድመ ሂሳብ ክፍያ መሙላት እንዲሁም ሂሳብ ጠይቆ ማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ በመግለጽ ላይ ናቸው።
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/social/item/255-2014-12-09-20-50-12#sthash.MPl8sFDA.dpuf

የታህሳስ ወር የነዳጅ ማስተካከያ ተደረገ


አዲስ አበባ፣ ህዳር 30/2007 (ዋ.ኢማ)  - ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 30/2007 የሚቆይ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ህዳር 29 ቀን 2007 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ለሚቀጥለው አንድ ወር በነዳጅ ዋጋ ላይ አንጻራዊ የዋጋ ቅናሽ የተደረገው በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ በመምጣቱ ነው ብሏል፡፡
በዚሁ ማስተካከያ መሰረት ተራ ቤንዚን በሊትር ብር 19 ከ41፣  ነጭ ናፍጣ ብር 17ከ49፣ ኬሮሲን ብር 15 ከ40 እንዲሁም ቀላል ጥቁር ናፍታ ብር 17ከ49 ሆኗል ፡፡
ከባድ ጥቁር ናፍታ በሊትር ብር 15 ከ14 ሳንቲም ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ ብር 19 ከ43 ሳንቲም መሆኑን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም 23 ቀን 2001 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በየወሩ እንዲከለስ መወሰኑ ይታወሳል።(ኢብኮ)

ምርጥ የፍቅር ቅመሞች! ወንዶች ብቻ ቢያነቡት ይመረጣል

1. እንክብካቤ አብዛበት
የትኛዋም ሴት ብትሆን ከወንድ ልጅ የሚደረግላትን እንክብካቤ አትጠላውም፡፡ ዓይን አፋር ሴት ደግሞ በማፈሯ የተነሳ ከብዙ ሰዎች የመራቅ ዝንባሌዋ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ አንተ ፍፁም የሆነ እንክብካቤ ልታደርግላት ይገባል፡፡ እንክብካቤ እያደረክላት ስትመጣ ለካ ወንድ ልጅ እንዲህ ያስብልኛል ልትል ሁሉ ትችላለች፡፡ በዚህም የመጀመሪያውን ጥያቄ በውስጧ ማሰላሰል ትጀምራለች፡፡ ይህ ደግሞ በቀጣይነት ለምታደርገው ነገሮችህ የልቤን መንገድ አስቀድመህ የምታንኳኳበት ይሆናል፡፡ ስለ እሷ ባሰብክና በተጨነቅላት ቁጥር ምንም ይሁን ምን ስለአንተ ሁኔታ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ የፍቅርን ምንነት በአንተ እንክብካቤ መነሻነት እንድታውቀው ያስገድዳታል፡፡ ስለዚህም አንተን ፈጽሞ የማትለይበት አይነት እንክብካቤ አድርግላት፡፡
2. ስለ ሌሎች ሰዎች የፍቅር ህይወት አጫውታት
ዓይን አፋር ሴት ራሷን ከብዙ ነገር እንደማራቋ መጠን ከፍቅር ጋር ያላት ግንዛቤም የቀነሰና ጥሩ አመለካከት ላይኖራት ስለሚችል ስለ ፍቅር ምንነት በቀልድና በጨዋታ እያዋዛህ ለማሳወቅ ሞክር፡፡ በተለይም ነጻና ዘና የምትልበትን ጊዜ ጠብቀህ የተለያዩ ሰዎችን የፍቅር ታሪክና አስደሳች የፍቅር ህይወታቸውን አጫውታት፡፡ እዚህ ጋር በቃ አንተ ፍፁም የፍቅር አስተማሪዋ እንደሆንክ መንገዶችን አመቻች፡፡ ከዚህ በፊት የነበራትንም ህይወት ለማወቅ በቀስታ እያወጣጣሀት ታሪኳን ለማወቅ ሞክር፡፡
3. ደስ የሚል ጊዜን አብራችሁ ለማሳለፍ ሞክር
የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ወጣ ባለ መልኩ ከእሷ ጋር መዝናናትና መደሰትን ተግብረው፡፡ በእያንዳንዷ አስደሳች የመዝናኛ ሰዓቶቹ አንተ አፍ አውጥተህ ከምትናገረው ይልቅ የውስጥህን ምኞት ነገሮችህና እንቅስቃሴዎችህ እንዲያሳውቃት አድርግ፡፡ አስደሳች ጊዜን እያሳለፋችሁ ስትመጡ ዓይን አፋርነቷን እየተወችው ስለ አንተ ፍቅር አቀራረብ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ ስለዚህም ባገኘኸው አጋጣሚ ይህን ለመተግበር የእሷን አመቺ ጊዜ ልትጠብቅ ይገባሃል፡፡
4. የሚያስደምሙ ስጦታዎችን አበርክትላት
ከአንተ ጋር ያለች ሴት ዓይን አፋርና ለወንድ ልጅ በፍቅር በቀላሉ የማትሸነፍ ከሆነች በጣም የሚማርኩ ስጦታዎችን በተለይም የተለያዩ በዓላትንና የልደቷ ቀንን ጠብቀህ ስጣት፡፡ ስጦታዎችህ በራሳቸው የውስጥህን ፍላጎት የሚናገሩልህ አድርገህ ምረጣቸው፡፡ ስትመርጣቸው ግን የእሷንም ፍላጎት የጠበቀና በጣም ሊያስደስታትና በመደምም ሌላ ነገር እንድታስብ የሚያደርጋት ይሁን፡፡ ታዲያ ስጦታዎችህን መሳሪያ አድርገህ በውለታ ፍቅሯን ለማግኘት እንዳይሆን ተጠንቀቅ፡፡ ይልቁንስ ስጦታዎችህ የውስጥህን ስሜትና ፍላጎት ከማሳወቅና የመልካም ነገር አቅርቦትህ ብቻ እንዲሆኑ ልታውቅም ልታሳውቃትም ይገባል፡፡ ያኔ የአንተን ማንነት የበለጠ ትረዳለች፡፡ ሳትወድ በግዷም ዓይን አፋርነቷ የበለጠ ሊጎዳት ስለሚችል ያንተን ዕድል ልታሳልፍ አትችልም፡፡
5. የጓደኛነት አቀራረብህን ቀይርባት
እሷን ከማወቅህ ጀምሮ ያሉ አቀራረቦችህን የጓደኝነት ወይም ደግሞ የወንድምነት መምሰሉ እየበዛ ሲመጣ አንተን እየጎዳህ ስለሚመጣ ጊዜውንና አመቺ ሁኔታዎችን አይተህ ወደ ፍቅር ፈላጊነት ራስህን ልትቀይርበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ከአንተ ስለ ፍቅር ምንነት እንደዚሁ በመቅረብህ ብቻ እያገኘች እንጂ በአንተ ልብ ውስጥ ፍቅር መፈለጓን በደንብ ላትገነዘበው ትችላለች፡፡ ምክንያቱም የዓይን አፋር ሴቶች መገለጫ ነውና፡፡ ልቧን በማትጠብቀው ሁኔታ ፍፁም በፍቅር አስደንብረው፡፡ በፍቅር የደነበረ ልብ ደግሞ ልጓሙና መያዣው በአንተ እጅ ውስጥ እንዲሆን አድርገው፡፡
6. ፍፁም አማላይ ሁንባት
የተለያዩ የፍቅር መግቢያ ቴክኒኮችን እየተጠቀምክ በመጣህ ቁጥር አንተ የፍቅር አማላይነትም አብሮ የሚታይ ነው፡፡ ነገር ግን ራሱን በቻለ መልኩ አማላይነትህ በየጊዜው እንዲታያት አድርግ፡፡ የፈለገ ዓይን አፋር ብትሆንም እንኳን የአንተ የአማላይነት አቀራረብህ ውስጡን ሊገዛው ይችላል፡፡ አንተ ያለምንም ፍራቻ በቀረበችህ ሰዓት ደባብሳት፣ እጇን ጭምቅ እያደረግክ ያዛት፣ አሳሳሞችህ ደስ የሚላትና የምትናፍቀው አይነት አድርግባት፣ እያቀፍካት ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ እየሳምካት ፍቅር ውስጥ ክተታት፡፡ ነገር ግን አሁንም የዓይን አፋርነቷ ባህሪይ ስለሚታወሳት ፀባይዋ ሊለዋወጥ ስለሚችል ሰው በተሰበሰበበት ልትስማትም ሆነ ልታቅፋት አትሞክር፡፡ ቀስ በቀስ ግን የምታደርጉት ነገር ምንም እንዳልሆነ በራስ መተማመንም እንድታዳብር አድርጋት፡፡ ይህን መፈፀም ከቻልክ ልቧ ውስጥ ትልቅ ፍቅር ማስቀመጥ ተችላለህ፡፡
7. በፍቅርህ ክንፍ እንድትል አድርግ
ከላይ ያሉትን ሁሉ ከተገበርካቸው አንተ በቃ የፍቅር ሰው ነህና ፍቅር መስጠት ተችላለህ፡፡ ታዲያ ፍቅርህን ስትሰጣት እሷንም በአንት ፍቅር ክንፍ እንድትል አድርጋት፡፡ በፍቅር የነካካኸውና የቆሰቆስከውን ልቧን መጋረጃና ማረፊያው አንተው ጋር እንዲሆን አድርግክ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ታዲያ የምን ማፈር ማለት ትጀምራለች፡፡ ምክንያቱም በአንተ የፍቅር ሰው መሆን አይን አፋርነቷን ገልጠህላታልና አንተ የእኔ ‹‹የፍቅር ላምባዲናዬ›› ነህ ማለት ትጀምራለች፡፡ ከዚህ በኋላ ድንቅ የፍቅር ሽሚያ ውስጥ ታስገባትና እሷው ፍቅር ላስተምርህ ሁሉ ማለት ትጀምራለች፡፡ ፍቅራችሁም በምሽት እንደጨረቃና ከዋክብት በቀን ደግሞ እንደ ፀሐይ እየበራ ይታያቸዋል፡፡ መልካም ፍቅር

ወሲብ ለጤንነት – (ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ማንበብ የተከለከለ)

ሁላችንም ወሲብ አስደሳች እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይሁን እንጂ ለጤና ጠቃሚ ነው ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተን አናውቅ ይሆናል፡፡ መልሱ ‹እጅግ በጣም› የሚል ነው፡፡ ነዋሪነታቸውን ኒውዮርክ ከተማ ያደረጉ እና ‹‹She comes first›› በሚል መጽሐፋቸው የሚታወቁት የወሲብና ወሲብ ነክ ጉዳዮች አማካሪ አየር ኬርነር ‹‹የወሲብ ህይወታችን ጤና የአጠቃላይ ጤና ነፀብራቅ ነው›› ይላሉ፡፡
በወሲብ ዙሪያ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ባለሙያዎች ወሲብ ለራሳችን የሚኖረንን አመለካከት (Self Esteem) ከማሻሻል ጀምሮ ለውስን በሽታዎች የሚኖረንን ተጋላጭነት እስከ መቀነስ ድረሰ ብዙ ጥቅም እንደሚሰጥ ያስረዳሉ፡፡ በአንፃሩ፣ እምብዛም ወሲብ የማይፈፅሙ ከሆነ አንዳች ችግር ሊኖር ይችላል፡፡
make love
እነዚህን ችግሮች ለይቶ መፍታት አስፈላጊ ነው ይላሉ ኬርነር፡፡ ምክንያቱም የወሲብ ህይወታችን በብዙ መልኩ ከልዩ ልዩ የህይወት ክፍሎቻችን ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው፡፡ ለአብነት ያህል፣ የወሲብ ፍላጎትዎና አፈፃፀምዎ አናሳ ከሆነ ምንአልባት የድብርት ተጋላጭ ሊሆን ይችላል፣ የተመጣጠነ ምግብ አይበሉ ይሆናል፣ ውጥረት ውስጥ ይገኙ ይሆናል ወዘተ፡፡
ወሲብ ተከታዮቹን በመድሃኒት መልክ ሊገኙ የማይችሉ ጤና ነክ ጥቅሞች ያስገኛል፤-
የልብ ጤንነትን ያሻሽላል
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የብልት መጠንከር ከልብ መጠንከር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ በ2008 ዓ.ም የአሜሪካን የልብ ህክምና ጆርናል ላይ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያብራራው የብልት መቆም እና መጠንከር ችግር (Erectile Dysfunction) ከልብ ጥንካሬ ማጣት ጋር ግንኙነት አለው፡፡
ተመራማሪዎች 2300 ወንዶች ላይ ባደረጉት ምርምር መሰረት የብልት መቆም እና መጠንከር ችግር ያለባቸው ወንዶች ለልብ ህመም ያላቸው ተጋላጭነት ችግሩ ከሌለባቸው ይልቅ በ58% ከፍ ያለ ነው፡፡
ለፕሮስቴት ካንሰር የሚዳርግ ተጋላጭነት ይቀንሳል
በ2004 ዓ.ም የአሜሪካ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ጆርናል ላይ 2400 ወንዶችን አሳትፎ የተሰራና ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው በአንድ ወር ውስጥ 21 ጊዜ ወሲብ የሚያደርጉ ሰዎች በወር ውስጥ ከ4-7 ጊዜ ያህል ወሲብ ከሚያደርጉ ሰዎች ይልቅ ኋላ ላይ ለፕሮስቴት ካንሰር የሚኖራቸው ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
ለስራ ይጠቅማል
ሔለን ፌሸር የሚባሉ አንትሮፖሎጂት ወሲብ የፈጠራ አቅምን፣ ችግር የመፍታት ችሎታን እና የመግባባት ክህሎትን እንደሚያሻሽል ይገልፃሉ፡፡ ይህንን ሁሉ ነገር ሊያሻሽል የሚችልበት ዐቢይ ምክንያት ወሲብ ስንፈፅም አንጎላችን ዶፓሚን እና ኦክሲቶሲም አካ የሚሰኙ የደስታ ስሜትን የሚያጎናፅፉ ኬሚካሎችን በብዛት አምርቶ ስለሚሰራጭ ነው፡፡
የወጣትነት መልክና ቁመና ተጠብቆ እንዲቆይ ይረዳል
ስኮትላንድ ውስጥ 3500 አሜሪካውያንን እና አውሮፓዊያንን ያሳተፈ አንድ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ ጥናቱ ለአስር ዓመቶች ያህል ቢያንስ ቢያንስ ከ7-12 ዓመት ከዕድሜአቸው ይልቅ ወጣት የሚመስሉ ሰዎችን አፈላልጎ ማግኘትና የጋራ ጠባያቸውን ማጥናት ነበር፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ታስሰው ከተገኙ በኋላ ጥናቱ የእነዚህን ሰዎች የጋራ መለያ ጠባይ ምን እንደሆነ ለመረዳት እና ለመተንተን ሙከራ አድርጓል፡፡ በግንባር ቀደምትነት እነዚህን ወንዶች የሚያመሳስላቸው ነገር መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መቻላቸው ነው፡፡
ሁለተኛው የጋራ መለያ ጠባያቸው በመደበኛነት ወሲብ መፈፀም ነው፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ከ2-3 ጊዜ በሳምንት ከፍቅር ወይም ትዳር አጋራቸው ጋር ወሲብ ይፈፅማሉ፡፡
ውጥረትን ይቀንሳል
ሴቶች የእርካታ ጣሪያ ላይ ከመድረሳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ በከፊል ንቁ በከፊል ንቁ ያልሆነ ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ፡፡ በዚህ ወቅት ውጥረትን የመቀነስ እና የማርገብ ሚና የሚጫወተው የአንጎላቸው ክፍል ስራ ይጀምራል፡፡
አንጎልን ያነቃቃል
ኬርነር ‹‹የወሲብ ፍላጎት መነቃቃት የአካልና አንጎል በጋራ መነቃቃት ነው›› ይላሉ፡፡ እኚህ ባለሙያ ብዙ ጊዜ አንጎላችንን ማነቃቃት የሚችለው ሐሳብ ወሲብ ውስጥ ድርሻ ሊኖረው እንደሚገባ እንዘነጋለን ይላሉ፡፡
ኬርነር፣ ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የስሜት ህዋሳቶቻችን ወሲብ ሲፈፀም ቦታ እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡ እይታ፣ ድምፅ፣ ንክኪ፣ ጣዕም፣ እና ጠረን፡፡
ስለዚህ፣ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ወሲብ መፈፀም ብቻ ሳይሆን በተቻለ መጠን ሁሉንም የስሜት ህዋሳቶች እና ሁኔታዎች ያካተተ አይነት ወሲብ መፈፀምን ያበረታታሉ፡፡ ሐሳብን፣ አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እና ሁሉንም የስሜት ሕዋሳቶች ተሳታፊ ማድረግ፡፡
ወሲብን የሚደግፉ እና የሚያበረታቱ ጥናቶች ቁጥር ስፍር የላቸውም፡፡ ስለዚህ የወሲብ አምሮታችሁ እና አድራጎታችሁ አናሳ ከሆነ ከዚህ ልምድ ልትወጡ የምትችሉበትን ነገር ለማድረግ ሞክሩ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲብ የወሲብ ፍላጎታችሁ ማሽቆልቆል ከጀመረ ይህ ለምን ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት ሞክሩ፡፡ የሳይኮሎጂ እና የህክምና ባለሙያ እንደየችግሩ ሁኔታ እገዛ ሊያደርጉላችሁ ይችላሉ፡፡ አለበለዚያ የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ ለአካላችሁ እና አለባበሳችሁ ቦታ በመስጠት ቀላል የማይባል ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡ ኬርነር ‹‹ሰዎች ጤናማ ወሲብ ከፍቅር አልያም ትዳር አጋራቸው ጋር ማድረግ ሲችሉ ህይወታቸው ይበልጥ ይደምቃል›› ይላሉ፡፡ ክብደታቸውን ለማስተካከልና ለመቆጣጠር ይበልጥ ተነሳሽነት ውስጣቸው ይፈጠራል፣ ራሳቸውን መንከባከብ ያዘወትራሉ፣ እንደተፈቀሩ ይሰማቸዋል፣ እርካታቸው ይጨምራል፡፡ በስራ ቦታ መነጫነጭም ሆነ መጋጨት ይቀንሳሉ፡፡ በጥቅሉ ወሲብ ለሁለንተናዊ ጤና መሻሻል በብዙ መልኩ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
Source : http://www.tenaadam.com/amharic/archives/2100