በወታደር እሸቱ ወንድሙ የተፃፈው “ህይወት በመንግስቱ ቤተ መንግስት ቁጥር 2” መፅሃፍ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡
የመፅሃፉ ደራሲ ቀድሞ የልዩ ሃይል አባል የነበረ መሆኑን በመፅሃፉ ሽፋን ላይ የገለፀ ሲሆን መፅሃፉም የጓድ
መንግስቱ ኃይለማርያምና የአስተዳደራቸውን ምስጢራት ይበረብራል ተብሏል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም በሳተመው “ቁጥር 1”
መፅሃፉ ውስጥ የተለያዩ ግለሰቦችን ስም መጥቀሱ ለዛቻና ማስፈራሪያ እንደዳረገው ጠቁሞ በሁለተኛው መፅሃፉ
የግለሰቦችን ስም ከመጥቀስ መቆጠቡን አስታውቋል፡፡
መፅሃፉ በ220 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ50.66 ብር ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ ደራሲው ወታደር እሸቱ ወንድሙ፤ “ህይወት በመንግስቱ ቤተ መንግስት ቁጥር 1” መፅሃፍን ጨምሮ “የሌ/ኮ መንግስቱ ያልተነገሩ ሚስጥሮች” የተሰኙ መፅሃፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡
መፅሃፉ በ220 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ50.66 ብር ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ ደራሲው ወታደር እሸቱ ወንድሙ፤ “ህይወት በመንግስቱ ቤተ መንግስት ቁጥር 1” መፅሃፍን ጨምሮ “የሌ/ኮ መንግስቱ ያልተነገሩ ሚስጥሮች” የተሰኙ መፅሃፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡
No comments:
Post a Comment