በአምስት
አመቱ የጣሊያን ወረራ ወቅት በውስጥ አርበኛነታቸው የሚታወቁትን ወ/ሮ የሸዋረገድ ገድሌን የህይወት ታሪክ የሚዘክረው
መፅሐፍ ዛሬ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መጽሐፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር) አዳራሽ
ይመረቃል፡፡ “ሸዋረገድ ገድሌ፤ የአኩሪ ገድላት ባለቤት” በሚል ርዕስ የታተመው መጽሃፍ፤ ከ1878-1942
ስለኖሩትና በጣሊያን ወረራ ወቅት በዱር በገደሉ ላሉ አርበኞች መረጃዎችን በማቀበል ታላቅ ገድል ስለፈፀሙት እናት
አርበኛ ይተርካል፡፡ የመፅሐፉ ፀሐፊ ደራሲ ሺበሺ ለማ ሲሆኑ መጽሐፉን ያሳተሙት የአርበኛዋ የወንድም ልጅ ዶ/ር
ክፍሌ ማርቆስ ገድሌ መሆናቸው ታውቋል፡፡ መፅሐፉ ለአገር ውስጥ በ70ብር፣ ለውጭ በ25 ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን
በዛሬው የምረቃ ስነስርአት ላይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ እና ሌተናል ጃገማ ኬሎ እንደሚገኙ
ታውቋል፡፡