Monday, September 8, 2014

የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ

Photo: የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ::

አንጀሊና ጆሊ ኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር የሆነችበትና ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም፣ በፍርድ ቤት እግድ ከተቋረጠ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማስነሳቱ ታወቀ፡፡ 

በአሜሪካ በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ ከሆነ በኋላ የፊልሙ በአዲስ አበባ መመረቅ በብዙዎች በጉጉት እየተጠበቀ ነበር፡፡ እንዲህ የተጠበቀው ፊልም ሊመረቅ በታሰበበት ዕለት ከአሥራ አምስት ደቂቃዎች በላይ ሊታይ አልቻለም፡፡ በብሔራዊ ቴአትር እየታየ ፌደራል ፖሊስ ደርሶ ሊያቋርጠው የግድ ሆኗል፡፡

ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያጠነጥነው አስገድዶ የደፈራትን የ29 ዓመት ወጣት በገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ አበራሽ በቀለ (በፊልሙ ሒሩት) ሕይወት ዙሪያ ነው፡፡ ደፋሪዋ ሕፃኗን በጠለፋ ሊያገባትም ሙከራ አድርጐ ነበር፡፡ 

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር መሥራች የሆኑት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ጉዳዩን ሰምተው ጥብቅና ቆመውላት ራስን ለመከላከል በሚል በነፃ እስከተለቀቀችበት ጊዜ ድረስ፣ አበራሽ በግድያ ክስ ተመሥርቶባት ማረሚያ ቤት ነበረች፡፡ 

በአቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ መሐሪ የተጻፈውና ዳይሬክት የተደረገው ይህ ፊልም በዚህ ዓመት በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ መሆኑን ተከትሎ፣ የታሪኩ ባለቤት በሆነችውና ፈቃደኝነቷን እንዳልተጠየቀች በምትናገረው ወ/ሪት አበራሽና የወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ወንድምና የታሪኩ ጸሐፊ ነኝ በሚሉት አቶ ፍቅሩ አሸናፊ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡ 

የፍርድ ቤት እግዱ እንደሚያሳየው በከሳሽነት የቀረቡት አቶ ፍቅሩ አሸናፊና ወ/ሪት አበራሽ በቀለ ሲሆኑ፣ ተከሳሾቹ ደግሞ አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ፣ ኃይሌ አዲስ ሥዕሎች ድርጅትና ትሩዝ ኤይድ ሚዲያ ድርጅት ናቸው፡፡

ክሱ እንደሚያስረዳው ድፍረት የተሰኘው ፊልም ተመርቆ ለሕዝብ ዕይታ ቢውል በከሳሾች ሞራላዊና ኢኮኖሚያዊ መብት ላይ የማይተካ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል በመገንዘብ፣ ፍርድ ቤቱ ፊልሙ ለሕዝብ ዕይታ እንዳይውል ወይም እንዳይመረቅ ጭምር እገዳ ጥሏል፡፡ በተጨማሪም በተከሳሾች ላይ ሊደርስ ለሚችል ኪሳራ ከሳሾች 50 ሺሕ ብር በዋስትና አስይዘዋል፡፡

ወ/ት አበራሽ እንደምትለው ፊልሙ በርሊን እስከተመረቀበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት መረጃ አልነበራትም፡፡ ከሰባት ወራት በፊት ግን አቶ ዘረሠናይን አግኝታው በፊልሙ ላይ ዕውቅና እንዲሰጣት፣ የተወሰነ ገንዘብም እንዲከፍላት እንደምትፈልግ ገልጻለት የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ 

የፊልሙ ሥራ የእሷን ደኅንነት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይደለም በማለት የምትወቅሰው ወ/ት አበራሽ፣ ምንም እንኳ ሁኔታውን ለማስረዳት ብትሞክርም ከአቶ ዘረሠናይ በመጨረሻ ያገኘችው መልስ አዎንታዊ አለመሆኑን ትናገራለች፡፡ ‹‹ከተፈጠረው ነገር ጋር በተያያዘ የምኖረው ተደብቄ ነበር፡፡ ይኼ ፊልም ግን ታሪኩን እንደ አዲስ ቀስቅሶ የእኔንም የቤተሰቦቼንም ሕይወት አደጋ ላይ ጥሎታል፤›› ትላለች፡፡

ወ/ት አበራሽ የደፈራትን ሰው ከገደለች በኋላ በኦሮሞ የእርቅ ባህል ጉማ መሠረት ቤተሰቦቿ ካሳ ከፍለው ነገሩ ተቋጭቶ ነበር፡፡ በስምምነቱ መሠረት እሷም ቀዬዋን ጥላ ለመውጣት ተስማምታ እንደነበር የምትናገረው አበራሽ፣ ‹‹በባህሉ መሠረት ሴት ገድላ ካሳ መክፈል አትችልም፡፡ ስለዚህም ወደ አካባቢዬ እንዳልመለስ የሟች ቤተሰቦች ያስጠነቀቁኝን በመስማትና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስል ለዓመታት እዚያ ሳልደርስ ቀረሁ፤›› ብላለች፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን ለማገዝ የሚሠራ ሀረም በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ በመሥራት ላይ የምትገኘው ወ/ት አበራሽ፣ በሕይወቷ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈች ትናገራለች፡፡ የትውልድ ቦታዋ ቀርሳ አርሲን የለቀቀችው ወ/ት አበራሽ ሁለተኛ ደረጃ እስክትደርስ የኖረችው ቀጨኔ ሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ነበር፡፡ ታሪኳ ተካትቶ በተሠራ ዘጋቢ ፊልም አማካይነት ታገኝ የነበረው ገንዘብ ኮሌጅ ስትገባ መቋረጡን ታስታውሳለች፡፡ ስለዚህም በነበረባት የገንዘብ ችግር የኮሌጅ ትምህርቷን ለማቋረጥ መገደዷን፣ ከዚያም ወደ ዱባይ እስከሄደችበት ጊዜ ድረስ በአንድ ትንሽ የፊልም ሲዲ ማከራያ ሱቅ ውስጥ መሥራቷን ለሪፖርተር ገልጻለች፡፡ 

አቶ ዘረሠናይ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ እንደተናገረውና አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት ስለታሪኩ መጀመሪያ አቶ ዘረሠናይ የነገረው ለእርሳቸው ነው፡፡ ይህ የሆነው እ.ኤ.አ. በ2005 ሲሆን፣ አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት የፊልሙ ሐሳብ የተወሰደው ከእሳቸው በመሆኑ ፊልሙን በጋራ ለመሥራት አስበው ነበር፡፡ ‹‹ከ2008 በኋላ አቶ ዘረሠናይ እኔን ለማናገር አልፈለገም፡፡ እንዲያውም ይደበቀኝ ጀመር፤›› ይላሉ፡፡

የፊልሙን መሠራት ሲጠባበቁና ነገሮችን ሲከታተሉ እንደነበር፣ የአበራሽን ይሁንታም እንዳገኙ አቶ ፍቅሩ ይናገራሉ፡፡ አቶ ዘረሠናይ ግን ለእሷም ለእሱም የታሪኩ ሐሳብ ባለቤት እንደመሆኑ ዕውቅና ሳይሰጥ መቅረቱን ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ያለሷ ታሪክ ፊልሙ አይሠራም ነበር፡፡ ባትደፈር፣ በጥንካሬ ደፋሪዋን ባትገድለው ኖሮ ታሪክ አይኖርም ነበር፤›› ይላሉ አቶ ፍቅሩ፡፡

በፊልሙ ውስጥ ሌላ ባለታሪክ የሆኑትና በወቅቱ የ14 ዓመቷ ታዳጊ ጠበቃ የነበሩት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለፊልሙ ዳይሬክተር ታሪካቸው በፊልሙ እንዲካተት ፈቃድ መስጠታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ያደረጉት ታሪኩ በፊልም መሠራቱ የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ጥያቄን ያራምዳል፣ ስለጠለፋና ስለጥቃት ግንዛቤ ለመፍጠር ያስችላል በሚል እንጂ ‹‹የእኔ ታሪክ ይነገር›› በሚል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ 

ለአበራሽ ጥብቅና በቆሙላት ጊዜ ከዚያም በኋላ አበራሽ በመኖሪያ ቤታቸው ተቀምጣ እንደነበር ቅርበትም እንደነበራቸው የሚያስታውሱት ወ/ሮ መዓዛ፣ ለረዥም ዓመታት ግን ከአበራሽ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖራቸው እንደቆዩም ይናገራሉ፡፡ 

ከፊልሙ መሠራት በኋላ ግን የታሪካቸው በፊልም መሠራት ለአበራሽ የሚከፍተው የዕድል በር ይኖራል በሚል ማፈላለግ መጀመራቸው የሚናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ስለጉዳዩ በነገሯት መሠረት በመጨረሻ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ደራርቱ ቱሉ የአበራሽን ስልክ ቁጥር እንደሰጠቻቸውና እንዳገኙዋት ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ 

‹‹ደውዬ ወደ አዲስ አበባ አስመጣኋት፡፡ አሁንም ያለችው እናቴ ቤት ነው፡፡ የእኔ ቤት ወጣ ስለሚል ነው እዚያ እንድትቀመጥ ያደረግኩት፡፡ ከመጣች ወደ ሰባት ወራት ገደማ ሆኗል፤›› የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፣ ወ/ት አበራሽን አሁን እየሠራችበት ያለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንድትቀጠር ያደረጉት እሳቸው እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ 

ወ/ሮ መዓዛ እንደገለጹት ወ/ት አበራሽ ወደ አዲስ አበባ እንድትመጣ ያደረጉት ፊልሙ ጀርመን በርሊን ውስጥ ሊመረቅ በተቃረበበት ጊዜ ነበር፡፡ 

ለታሪኳ ባለቤት ወ/ት አበራሽ በፊልሙ ሥራ ተሳታፊ ከሆኑት ግለሰቦች ሁሉ ቅርበት ያላት እርሷ እንደመሆኗ የታሪኳ ባለቤት ተጠቃሚነትን በሚመለከት ለወ/ሮ መዓዛ ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹መጠቀም እንዳለባት አምናለሁ፡፡ አቶ ዘረሠናይም በዚህ ያምናል፡፡ ይህን ለማድረግም በጣም ፈቃደኛ ነው፡፡ እሷም የምትጠብቀው ነገር አለ፡፡ ችግር የፈጠረው እንዴት በሚለው ላይ አለመነጋገር ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

ወንድማቸው አቶ ፍቅሩ አሸናፊም ፊልሙ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን በሚመለከት፣ ወንድማቸውና የድፍረት ፊልም ዳይሬክተርና ከፕሮዲዩሰሮቹ መካከል አንዱ የሆነው አቶ ዘረሠናይ ምንም እንኳ የጓደኝነታቸውን ደረጃ መናገር ባይችሉም፣ ጓደኛማቾች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ወንድማቸው ስለ እርሳቸው ለጓደኛው አቶ ዘረሠናይ ሲያወሩ የፊልም ባለሙያ የሆነው አቶ ዘረሠናይም ታሪኩን ወደ ፊልም ለመቀየር ትልቅ ፍላጐት እንዳደረበትና የፊልሙ መነሻ እንዲህ እንደነበር፣ ከዚህ ውጪ ግን በወንድማቸውና በአቶ ዘረሠናይ መካከል ሌላ ጉዳይ ይኑር አይኑር የሚያውቁት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡ ግጭቱ ቀላል እንደሆነ ስለዚህም በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው አክለዋል፡፡ 

የፊልሙ ዳይሬክተር አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ በእጁ ላይ ያለው የፍርድ ቤት እግድ ብቻ በመሆኑ ስለክሱ ዝርዝር ነገር ሳያውቅ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይፈልግ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡ የባለታሪኳ ወ/ሮ አበራሽ ፈቃድን ማግኘት አለማግኘቱን በተመለከተም አቶ ዘረሠናይ ምንም ማለት አለመፈለጉን ገልጿል፡፡ ጠበቃው ዓርብ ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የክሱን ቻርጅ ለማግኘት ፍርድ ቤት እንደነበሩና የክሱን ዝርዝር እንዳወቁ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ዓርብ እኩለ ሌሊት ድረስ ከእሱ በኩል የተሰማ ነገር አልነበረም፡፡ 

የፊልሙ እግድ ለብሔራዊ ቴአትር ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. አሥራ አንድ ሰዓት ላይ መድረሱን ከሳሾች ቢጠቁሙም፣ የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ እግዱ የደረሰው አሥራ አንድ ሰዓት ከሃያ አምስት ላይ እንደነበር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት እግዱ በደረሰበት ወቅት 1,200 ያህል እንግዶች አዳራሹ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አሥር ያህሉ አምባሳደሮችና ባለሥልጣናት ነበሩ፡፡ በአሳጋጆቹ በኩል የነበረው አቀራረብ አስቸጋሪ ስለነበርና በሌላኛውም በኩል ፊልሙን ለማቋረጥ ያለመፈለግ ነገር ስለነበር፣ በአጋጣሚው የአገር ገጽታ እንዳይበላሽ በጥንቃቄ ለመያዝ ቴአትር ቤቱ የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል ብለዋል፡፡

‹‹የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይከበራል፡፡ ይህ ምንም ዓይነት ጥያቄ የለውም፡፡ ነገር ግን በሁሉቱም በኩል የነበረው ነገር ወደ ግጭት የሚያመራ ዓይነት ስለነበር ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ፖሊስ ጠርተናል፡፡ ምክንያቱም እኛ ያለን የፀጥታ ኃይል ያን ማድረግ አይችልም ነበር፤›› ሲሉ አቶ ተስፋዬ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡
            
 አንጀሊና ጆሊ ኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር የሆነችበትና ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም፣ 
በፍርድ ቤት እግድ ከተቋረጠ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማስነሳቱ ታወቀ፡፡

በአሜሪካ በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ ከሆነ በኋላ የፊልሙ በአዲስ አበባ መመረቅ በብዙዎች በጉጉት እየተጠበቀ ነበር፡፡ እንዲህ የተጠበቀው ፊልም ሊመረቅ በታሰበበት ዕለት ከአሥራ አምስት ደቂቃዎች በላይ ሊታይ አልቻለም፡፡ በብሔራዊ ቴአትር እየታየ ፌደራል ፖሊስ ደርሶ ሊያቋርጠው የግድ ሆኗል፡፡

ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያጠነጥነው አስገድዶ የደፈራትን የ29 ዓመት ወጣት በገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ አበራሽ በቀለ (በፊልሙ ሒሩት) ሕይወት ዙሪያ ነው፡፡ ደፋሪዋ ሕፃኗን በጠለፋ ሊያገባትም ሙከራ አድርጐ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር መሥራች የሆኑት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ጉዳዩን ሰምተው ጥብቅና ቆመውላት ራስን ለመከላከል በሚል በነፃ እስከተለቀቀችበት ጊዜ ድረስ፣ አበራሽ በግድያ ክስ ተመሥርቶባት ማረሚያ ቤት ነበረች፡፡

በአቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ መሐሪ የተጻፈውና ዳይሬክት የተደረገው ይህ ፊልም በዚህ ዓመት በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ መሆኑን ተከትሎ፣ የታሪኩ ባለቤት በሆነችውና ፈቃደኝነቷን እንዳልተጠየቀች በምትናገረው ወ/ሪት አበራሽና የወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ወንድምና የታሪኩ ጸሐፊ ነኝ በሚሉት አቶ ፍቅሩ አሸናፊ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡

የፍርድ ቤት እግዱ እንደሚያሳየው በከሳሽነት የቀረቡት አቶ ፍቅሩ አሸናፊና ወ/ሪት አበራሽ በቀለ ሲሆኑ፣ ተከሳሾቹ ደግሞ አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ፣ ኃይሌ አዲስ ሥዕሎች ድርጅትና ትሩዝ ኤይድ ሚዲያ ድርጅት ናቸው፡፡

ክሱ እንደሚያስረዳው ድፍረት የተሰኘው ፊልም ተመርቆ ለሕዝብ ዕይታ ቢውል በከሳሾች ሞራላዊና ኢኮኖሚያዊ መብት ላይ የማይተካ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል በመገንዘብ፣ ፍርድ ቤቱ ፊልሙ ለሕዝብ ዕይታ እንዳይውል ወይም እንዳይመረቅ ጭምር እገዳ ጥሏል፡፡ በተጨማሪም በተከሳሾች ላይ ሊደርስ ለሚችል ኪሳራ ከሳሾች 50 ሺሕ ብር በዋስትና አስይዘዋል፡፡

ወ/ት አበራሽ እንደምትለው ፊልሙ በርሊን እስከተመረቀበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት መረጃ አልነበራትም፡፡ ከሰባት ወራት በፊት ግን አቶ ዘረሠናይን አግኝታው በፊልሙ ላይ ዕውቅና እንዲሰጣት፣ የተወሰነ ገንዘብም እንዲከፍላት እንደምትፈልግ ገልጻለት የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

የፊልሙ ሥራ የእሷን ደኅንነት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይደለም በማለት የምትወቅሰው ወ/ት አበራሽ፣ ምንም እንኳ ሁኔታውን ለማስረዳት ብትሞክርም ከአቶ ዘረሠናይ በመጨረሻ ያገኘችው መልስ አዎንታዊ አለመሆኑን ትናገራለች፡፡ ከተፈጠረው ነገር ጋር በተያያዘ የምኖረው ተደብቄ ነበር፡፡ ይኼ ፊልም ግን ታሪኩን እንደ አዲስ ቀስቅሶ የእኔንም የቤተሰቦቼንም ሕይወት አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ትላለች፡፡

ወት አበራሽ የደፈራትን ሰው ከገደለች በኋላ በኦሮሞ የእርቅ ባህል ጉማ መሠረት ቤተሰቦቿ ካሳ ከፍለው ነገሩ ተቋጭቶ ነበር፡፡ በስምምነቱ መሠረት እሷም ቀዬዋን ጥላ ለመውጣት ተስማምታ እንደነበር የምትናገረው አበራሽ፣ በባህሉ መሠረት ሴት ገድላ ካሳ መክፈል አትችልም፡፡ ስለዚህም ወደ አካባቢዬ እንዳልመለስ የሟች ቤተሰቦች ያስጠነቀቁኝን በመስማትና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስል ለዓመታት እዚያ ሳልደርስ ቀረሁ፤ ብላለች፡፡

በአሁኑ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን ለማገዝ የሚሠራ ሀረም በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ በመሥራት ላይ የምትገኘው ወ/ት አበራሽ፣ በሕይወቷ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈች ትናገራለች፡፡ የትውልድ ቦታዋ ቀርሳ አርሲን የለቀቀችው ወ/ት አበራሽ ሁለተኛ ደረጃ እስክትደርስ የኖረችው ቀጨኔ ሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ነበር፡፡ ታሪኳ ተካትቶ በተሠራ ዘጋቢ ፊልም አማካይነት ታገኝ የነበረው ገንዘብ ኮሌጅ ስትገባ መቋረጡን ታስታውሳለች፡፡ ስለዚህም በነበረባት የገንዘብ ችግር የኮሌጅ ትምህርቷን ለማቋረጥ መገደዷን፣ ከዚያም ወደ ዱባይ እስከሄደችበት ጊዜ ድረስ በአንድ ትንሽ የፊልም ሲዲ ማከራያ ሱቅ ውስጥ መሥራቷን ለሪፖርተር ገልጻለች፡፡

አቶ ዘረሠናይ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ እንደተናገረውና አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት ስለታሪኩ መጀመሪያ አቶ ዘረሠናይ የነገረው ለእርሳቸው ነው፡፡ ይህ የሆነው እ.ኤ.አ. በ2005 ሲሆን፣ አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት የፊልሙ ሐሳብ የተወሰደው ከእሳቸው በመሆኑ ፊልሙን በጋራ ለመሥራት አስበው ነበር፡፡ ‹‹ከ2008 በኋላ አቶ ዘረሠናይ እኔን ለማናገር አልፈለገም፡፡ እንዲያውም ይደበቀኝ ጀመር፤›› ይላሉ፡፡

የፊልሙን መሠራት ሲጠባበቁና ነገሮችን ሲከታተሉ እንደነበር፣ የአበራሽን ይሁንታም እንዳገኙ አቶ ፍቅሩ ይናገራሉ፡፡ አቶ ዘረሠናይ ግን ለእሷም ለእሱም የታሪኩ ሐሳብ ባለቤት እንደመሆኑ ዕውቅና ሳይሰጥ መቅረቱን ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ያለሷ ታሪክ ፊልሙ አይሠራም ነበር፡፡ ባትደፈር፣ በጥንካሬ ደፋሪዋን ባትገድለው ኖሮ ታሪክ አይኖርም ነበር፤›› ይላሉ አቶ ፍቅሩ፡፡

በፊልሙ ውስጥ ሌላ ባለታሪክ የሆኑትና በወቅቱ የ14 ዓመቷ ታዳጊ ጠበቃ የነበሩት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለፊልሙ ዳይሬክተር ታሪካቸው በፊልሙ እንዲካተት ፈቃድ መስጠታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ያደረጉት ታሪኩ በፊልም መሠራቱ የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ጥያቄን ያራምዳል፣ ስለጠለፋና ስለጥቃት ግንዛቤ ለመፍጠር ያስችላል በሚል እንጂ ‹‹የእኔ ታሪክ ይነገር›› በሚል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ለአበራሽ ጥብቅና በቆሙላት ጊዜ ከዚያም በኋላ አበራሽ በመኖሪያ ቤታቸው ተቀምጣ እንደነበር ቅርበትም እንደነበራቸው የሚያስታውሱት ወ/ሮ መዓዛ፣ ለረዥም ዓመታት ግን ከአበራሽ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖራቸው እንደቆዩም ይናገራሉ፡፡

ከፊልሙ መሠራት በኋላ ግን የታሪካቸው በፊልም መሠራት ለአበራሽ የሚከፍተው የዕድል በር ይኖራል በሚል ማፈላለግ መጀመራቸው የሚናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ስለጉዳዩ በነገሯት መሠረት በመጨረሻ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ደራርቱ ቱሉ የአበራሽን ስልክ ቁጥር እንደሰጠቻቸውና እንዳገኙዋት ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

‹‹ደውዬ ወደ አዲስ አበባ አስመጣኋት፡፡ አሁንም ያለችው እናቴ ቤት ነው፡፡ የእኔ ቤት ወጣ ስለሚል ነው እዚያ እንድትቀመጥ ያደረግኩት፡፡ ከመጣች ወደ ሰባት ወራት ገደማ ሆኗል፤›› የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፣ ወ/ት አበራሽን አሁን እየሠራችበት ያለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንድትቀጠር ያደረጉት እሳቸው እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ እንደገለጹት ወ/ት አበራሽ ወደ አዲስ አበባ እንድትመጣ ያደረጉት ፊልሙ ጀርመን በርሊን ውስጥ ሊመረቅ በተቃረበበት ጊዜ ነበር፡፡

ለታሪኳ ባለቤት ወ/ት አበራሽ በፊልሙ ሥራ ተሳታፊ ከሆኑት ግለሰቦች ሁሉ ቅርበት ያላት እርሷ እንደመሆኗ የታሪኳ ባለቤት ተጠቃሚነትን በሚመለከት ለወ/ሮ መዓዛ ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹መጠቀም እንዳለባት አምናለሁ፡፡ አቶ ዘረሠናይም በዚህ ያምናል፡፡ ይህን ለማድረግም በጣም ፈቃደኛ ነው፡፡ እሷም የምትጠብቀው ነገር አለ፡፡ ችግር የፈጠረው እንዴት በሚለው ላይ አለመነጋገር ነው፤›› ብለዋል፡፡

ወንድማቸው አቶ ፍቅሩ አሸናፊም ፊልሙ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን በሚመለከት፣ ወንድማቸውና የድፍረት ፊልም ዳይሬክተርና ከፕሮዲዩሰሮቹ መካከል አንዱ የሆነው አቶ ዘረሠናይ ምንም እንኳ የጓደኝነታቸውን ደረጃ መናገር ባይችሉም፣ ጓደኛማቾች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ወንድማቸው ስለ እርሳቸው ለጓደኛው አቶ ዘረሠናይ ሲያወሩ የፊልም ባለሙያ የሆነው አቶ ዘረሠናይም ታሪኩን ወደ ፊልም ለመቀየር ትልቅ ፍላጐት እንዳደረበትና የፊልሙ መነሻ እንዲህ እንደነበር፣ ከዚህ ውጪ ግን በወንድማቸውና በአቶ ዘረሠናይ መካከል ሌላ ጉዳይ ይኑር አይኑር የሚያውቁት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡ ግጭቱ ቀላል እንደሆነ ስለዚህም በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው አክለዋል፡፡

የፊልሙ ዳይሬክተር አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ በእጁ ላይ ያለው የፍርድ ቤት እግድ ብቻ በመሆኑ ስለክሱ ዝርዝር ነገር ሳያውቅ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይፈልግ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡ የባለታሪኳ ወ/ሮ አበራሽ ፈቃድን ማግኘት አለማግኘቱን በተመለከተም አቶ ዘረሠናይ ምንም ማለት አለመፈለጉን ገልጿል፡፡ ጠበቃው ዓርብ ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የክሱን ቻርጅ ለማግኘት ፍርድ ቤት እንደነበሩና የክሱን ዝርዝር እንዳወቁ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ዓርብ እኩለ ሌሊት ድረስ ከእሱ በኩል የተሰማ ነገር አልነበረም፡፡

የፊልሙ እግድ ለብሔራዊ ቴአትር ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. አሥራ አንድ ሰዓት ላይ መድረሱን ከሳሾች ቢጠቁሙም፣ የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ እግዱ የደረሰው አሥራ አንድ ሰዓት ከሃያ አምስት ላይ እንደነበር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት እግዱ በደረሰበት ወቅት 1,200 ያህል እንግዶች አዳራሹ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አሥር ያህሉ አምባሳደሮችና ባለሥልጣናት ነበሩ፡፡ በአሳጋጆቹ በኩል የነበረው አቀራረብ አስቸጋሪ ስለነበርና በሌላኛውም በኩል ፊልሙን ለማቋረጥ ያለመፈለግ ነገር ስለነበር፣ በአጋጣሚው የአገር ገጽታ እንዳይበላሽ በጥንቃቄ ለመያዝ ቴአትር ቤቱ የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል ብለዋል፡፡

‹‹የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይከበራል፡፡ ይህ ምንም ዓይነት ጥያቄ የለውም፡፡ ነገር ግን በሁሉቱም በኩል የነበረው ነገር ወደ ግጭት የሚያመራ ዓይነት ስለነበር ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ፖሊስ ጠርተናል፡፡ ምክንያቱም እኛ ያለን የፀጥታ ኃይል ያን ማድረግ አይችልም ነበር፤›› ሲሉ አቶ ተስፋዬ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment