Wednesday, September 3, 2014

Doctors Without Borders: 'World is losing the battle against Ebola

UNITED NATIONS (AP) - The international group Doctors Without Borders warned Tuesday that the world is losing the battle against Ebola and lamented that treatment centers in West Africa have been "reduced to places where people go to die alone."
In separate remarks after a United Nations meeting on the crisis, the World Health Organization chief said everyone involved had underestimated the outbreak, which has now killed more than 1,500 people in Guinea, Liberia, Sierra Leone and Nigeria. U.N. officials implored governments worldwide to send medical workers and material contributions.
Meanwhile in Liberia, a missionary organization announced that another American doctor has become infected.
Doctors Without Borders, which has treated more than 1,000 Ebola patients in West Africa since March, is completely overwhelmed by the disease, said Joanne Liu, the organization's president. She called on other countries to contribute civilian and military medical personnel familiar with biological disasters.
"Six months into the worst Ebola epidemic in history, the world is losing the battle to contain it," Liu said at a U.N. forum on the outbreak. "Ebola treatment centers are reduced to places where people go to die alone, where little more than palliative care is offered."
In Sierra Leone, she said, infectious bodies are rotting in the streets. Liberia had to build a new crematorium instead of new Ebola care centers.
At the U.N. meeting, WHO Director Margaret Chan thanked countries that have helped but said: "We need more from you. And we also need those countries that have not come on board."
Later at a news conference, she warned that the outbreak will get worse before it gets better.
President Barack Obama urged West Africans on Tuesday to wear gloves and masks when caring for Ebola patients or burying anyone who died of the disease. He discouraged the burial practice of directly touching the body of Ebola victims, which is one way the disease has been spreading.
"You can respect your traditions and honor your loved ones without risking the lives of the living," Obama said in the brief video message.
Dr. Tom Frieden, director of the U.S. Centers for Disease Control and Prevention, said the situation is now the world's first Ebola epidemic, given how widely it is spreading.
The latest missionary to come down with the disease, a male obstetrician, was not immediately identified by the group Serving In Mission. The group did not specify how he contracted the disease, but it can be spread through vaginal fluids. He did not work in an Ebola ward.
A Liberian doctor on the missionary's treatment team said it was too soon to tell whether he will be evacuated. The doctor would speak only on condition of anonymity because he was not authorized to discuss the matter with reporters.
Last month, two Americans, including one from the same missionary group, were evacuated to the United States for treatment after contracting Ebola in Liberia. The two recovered after receiving an experimental drug known as ZMapp. The manufacturer says it has run out of supplies of the drug and it will take months to produce more.
U.S. health officials on Tuesday announced a $24.9 million, 18-month contract with Mapp Biopharmaceutical Inc. to speed development of ZMapp. As part of the project, Mapp is to make a small amount of the drug for early-stage safety testing, while working with the Department of Health and Human Services to accelerate the manufacturing process.
The outbreak has taken a particularly high toll on health care workers, and nurses in Liberia and Sierra Leone have repeatedly gone on strike to demand hazard pay and better protective gear.
On Monday, nurses at a major hospital in the Liberian capital went on strike, according to spokesman Jerald P. Dennis III. While JFK hospital is treating Ebola patients, the striking nurses were all from non-Ebola wards.
Information Minister Lewis Brown said late Tuesday that the dispute had been resolved, but Dennis said discussions were ongoing.
Meanwhile, the Sierra Leone government said nurses were back at work Tuesday after a strike at a Freetown hospital this weekend. The government has said it will pay out all accrued hazard pay and double the allowance going forward.
Also Tuesday, the U.N. Food and Agriculture Organization warned that food in countries hit by Ebola is becoming more expensive and will become scarcer because some farmers can't reach their fields.
Authorities have cordoned off entire towns in an effort to halt the virus' spread. Surrounding countries have closed land borders, and airlines have suspended flights to and from the affected countries. Seaports are losing traffic, restricting food imports to the hardest-hit countries.
Those countries - Guinea, Liberia and Sierra Leone - all rely on grain from abroad to feed their people, according to the U.N. food agency. For instance, the price of cassava root, a staple in many West African diets, has gone up 150 percent in one market in Liberia's capital, Monrovia.
"Even prior to the Ebola outbreak, households in some of the affected areas were spending up to 80 percent of their incomes on food," said Vincent Martin, who is coordinating the food agency's response to the crisis. "Now these latest price spikes are effectively putting food completely out of their reach."
___
DiLorenzo reported from Dakar, Senegal. Associated Press writers Mike Stobbe in New York; Jonathan Paye-Layleh in Monrovia, Liberia; Clarence Roy-Macaulay in Freetown, Sierra Leone; Marc-Andre Boisvert in Abidjan, Ivory Coast; and Lauran Neergaard in Washington contributed to this report.

Tuesday, September 2, 2014

ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ

ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ሰነዱ አሜሪካን ጨምሮ ለሃያላን አገሮች ቀርቧል

ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች “እንሰጋለን” ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል።

ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረቡት ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች የተጠቀሰውን ሰነድ ማቅረባቸውን የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የሰነዱን ዝርዝርና ውህደቱ በምን መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ለጊዜው ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ራሳቸውን ከተበጠበጠችው እናት አገራቸው ነጥለው አገር ማስተዳደር ከጀመሩ ዓመታት ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ በአገርነት እውቅና አላገኙም። በዚህ መነሻ ይሁን በሌላ፣ ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች ኢትዮጵያን እናት አገራቸው ሆና እንድታስተዳድራቸው ሰነድ አዘጋጅተው ከማቅረባቸው በፊት ከኢህአዴግ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ሲመክሩ ቆይተዋል።

“ባለራዕዩና ወደር የሌለው የኢትዮጵያ ልጅ” እየተባሉ የሚጠሩት ሟቹ ጠ/ሚ/ር በህይወት እያሉ የተጀመረው ይህ የውህደት ጥያቄ ተግባራዊ ሊሆን ስለሚችልበት፣ ስለሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁ ዲፕሎማት “እኔም ሆንኩ ሌሎች ስጋት አለን” ይላሉ። ሲያስረዱም “ወደብ እናገኛለን። ቆዳችን ይሰፋል። ነገር ግን ችግሩ ደግሞ ከዚህ ሁሉ የከፋ ነው” ብለዋል።

ችግሮቹን መዘርዘር ምን አልባትም በአገር ቤት የተለያዩ የእምነት ተቋማትና ምዕመናን ዘንድ ቅሬታ ሊያስነሳ እንደሚችል ያመለከቱት ዲፕሎማት ኢህአዴግ እጁን ሰብስቦ ሊቀመጥ እንደሚገባ መክረዋል። በሶማሊያ አካባቢ ካለው የአክራሪ ሃይላት መስፋፋት ጋር በተያያዘ ለደህንነት ሲባል ሃያላን አገሮች ጥያቄውን ሊደግፉት እንደሚችሉ ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ “ውህደቱ በግፊትና በድጎማ ስም ተግባራዊ ይሁን እንኳን ቢባል ቅድሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ በይፋ ደምጽ ሊሰጥበት ይገባል፣ ከፍተኛ የእምነት ቁጥር አለመመጣጠን ያስከትላል” የሚል ጥቅል ሃሳብ ሰንዝረዋል።

ኢህአዴግ በቀድሞ መሪው አማካይነት የሶማሌ ወደቦችን አማራጭ አድርጎ የመጠቀም ስትራቴጂ እንዳለው በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። ለዚሁ ተግባራዊነት መጨረሻው በይፋ ባይታወቅም በኢትዮጵያ ወጪ ወደቡ ድረስ ዘልቆ የሚገባ የመኪና መንገድ ግንባታ ተጀምሮ አንደነበር የሚታወስ ነው። በተለይ የፑንትላንድ ፓርላማ ሰዎች በተደጋጋሚ አዲስ አበባ ይመላለሱ አንደነበርም አይዘነጋም።

የህወሃት ሰዎች የወደብ ጉዳይ ካሳሰባቸው የኢትዮጵያ ንብረት የሆነውን የአሰብን የባህር በር ወደ ቀድሞው መንበሩ የመመለስ ስራ አጠንክረው መስራት የሚያስችላቸው ሰፊ የህግና የመብት አግባብ ስለመኖሩ የተናገሩት ዲፕሎማት “ሶማሌ አሁን ችግር ውስጥ ብትሆንም ህጋዊ ክልሎቿን ለመጠቅለል መስማማት የአንድን አገር ሉአላዊነት የመዳፈር ያህል በመሆኑ ጊዜ ጠብቆ ዋጋ ያስከፍላል። የህግ ድጋፍም የለውም፤ በፌዴሬሽን ለመቀላቀልም ቢሆን የሚያስችል አግባብ የለም” ብለዋል።

በቅርቡ ለመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት “ፓርላማው” ሳያውቅ ከኢትዮጵያ ተቆርጦ የተሰጠውን መሬት አስመልክቶ ለተፈጠረው ቅሬታ መልስ የሰጡት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ “ከጅቡቲ ጋር የሚፈጸመው ውህደት አንዱ አካል ነው” በማለት የመሬቱን አላግባብ መሰጠት ማስተባበላቸው የሚታወስ ነው። ሪፖርተር ቃል አቀባዩን ጠቅሶ በወቅቱ እንደጠቆመው ኢህአዴግ ለጅቡቲ ያቀረበው የመሬት ግብር /ስጦታ/ በሂደት “ለመጠቃለል” የሚያስችል ውለታ ተደርጎ የሚቆጠር መሆኑን ነው። ኢትዮጵያ በራሷ ወጪ በጅቡቲ ወደብ ላይ የወደብ ኮሪዶር ለመስራት ከስምምነት መድረሷንም አስቀድሞ በቃል አቀባዩ አማካይነት መገለጹ አይዘነጋም። ይህንን የሚያስታውሱ የቀደመው ወደብ የመገንባት ውል እያለ ባቋራጭ “የውህደት ሃሳብ እንዴት ተሰነቀረ?” ሲሉ ይጠይቃሉ።

በተመሳሳይ ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ፍላጎት ቢኖራቸውም በተግባር ሊውል የማይችል ቅዠት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች አመልክተዋል። ሁለቱ ክፍለ ሃገሮች የኢትዮጵያ አካል ከሆኑ በኋላ በአንቀጽ 39 ንዑስ ቁጥር 1 መሠረት “የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን እስከ መገንጠል ድረስ ያለው ያልተገደበ መብት” መሰረት በማድረግ ዳግም የመገንጠል ጥያቄ በማቅረብ ኢህአዴግ አስቀድሞ እውቅና እንዲሰጣቸውና አንደ ኤርትራ ውለታ እንዲሰራላቸው ተመኝተው ሊሆን አንደሚችል የሸረደዱም አሉ።
**********************************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ  ወይም የድረገጻችንን አድራሻ  አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

በአገሪቱ መግቢያና መውጫ ኬላዎች የኢቦላ ቅኝት ተጀመረ

በአገሪቱ መግቢያና መውጫ ኬላዎች የኢቦላ ቅኝት ተጀመረ 

በሞያሌ፣ በመተማ፣ በሁመራ፣ በቶጐ ጫሌና በጋምቤላ ከኢቦላ ጋር በተያያዘ ቅኝት መጀመሩን፣ የብሔራዊ ኮሚቴው አባልና የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና የምግብ ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ 
የቅኝት ሥራው ከጥቂት ቀናት በፊት የተጀመረው ለሚመለከታቸው የክልልና የፌደራል የጤና ባለሙያዎች አስፈላጊው ሥልጠና ከተሰጠ በኋላ መሆኑን ለሪፖርተር የገለጹት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አበባው ገሠሠ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የአገሪቱ መግቢያ መውጫ ኬላዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም፣ የተጠቀሱት ኬላዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ቅኝቱ መጀመሩን አስረድተዋል፡፡ አሁን በተወሰነ ደረጃ የተጀመረው ቅኝት መጠናከር እንደሚገባውም ጠቁመዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ከስደተኞች ጋር በተያያዘ ትኩረት መስጠት ቢያስፈልግም፣ በጋምቤላ ኬላ ባለመኖሩ በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጅማ ቅርንጫፍ ሥር ያሉ ኬላዎችን ለቅኝት ሥራው ለመጠቀም ሥራዎች መጀመራቸውን አመልክተዋል፡፡
አቶ አበባው እንዳሉት፣ የቅኝት ሥራው በሚሠራባቸው ኬላዎች ላይ የኅብረተሰብ ጤና ኮሚቴዎች  ተቋቁመዋል፡፡ ኬላዎቹ ላይ የቅኝት ሥራ መጀመሩ በሞያሌ፣ በመተማ ወይም በሁመራ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቋርጠው በሚገቡ ሰዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የቫይረሱን ሥርጭት ለመከታተል ብቻም ሳይሆን፣ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ወደተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚሄዱ፣ በተለይም ለኢቦላ ተጋላጭ ከሆኑ አገሮች የሚመጡትን የቫይረሱ ምልክት ለ21 ቀናት ስለማይታይ ለመከታተል ያስችላል፡፡ ይህ ደግሞ የመከላከል ሥራውን ያጠናክረዋል ብለዋል፡፡ 
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ያለው አካባቢያዊ እውነታ ታሳቢ እየተደረገ ዕርምጃዎች እንደሁኔታው ተለዋዋጭ እንደሚሆኑ የጠቆሙ ሲሆን፣ በኬንያ ሞያሌና በሌሎች ኬላዎች ላይ ከቅኝት አልፎ ምርመራ (ስክሪኒንግ) ማድረግ ቢያስፈልግ፣ ይህን የሚያስችል ዝግጅትና አቅም ስለመኖሩ ለአቶ አበባው ጥያቄ ቀርቦላቸው ለሪፖርተር በሰጡት ምላሽ፣  -የመከላከያ መሣሪያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ ሌሎችም የተሠሩ ሥራዎች አሉ በመገዛት ላይ ያሉ ነገሮችም አሉ፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት ኬንያ በከፍተኛ ደረጃ ለኢቦላ ተጋላጭ መሆኗን በማስታወቁ ምክንያት፣ በምሥራቅ አፍሪካ የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል ቁጥጥሮችና የመከላከል ዕርምጃዎች እየተወሰዱ ነው፡፡ አገሪቱ በዚህ ደረጃ ለቫይረሱ ተጋላጭ ናት የተባለችው ከምዕራብ አፍሪካ ወደ ምሥራቅ፣ ከምሥራቅም ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚደረግ ጉዞ መተላለፊያ በመሆኗ ነው፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት ነሐሴ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. በምዕራብ አፍሪካ ለተከሰተው የኢቦላ በሽታ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያደረገ ያለውን ምላሽ ለመምራትና ለማቀናጀት የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የፍኖተ ካርታው ዓላማ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ወራት በሚሆን ጊዜ ውስጥ የቫይረሱን ቀጣይ ዓለም አቀፍ ሥርጭት መግታት ነው፡፡
ፍኖተ ካርታው በቫይረሱ የተጠቁ አገሮች የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ የአፍሪካ ኅብረትን፣ የልማት ባንኮችን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎችን፣ የሜዲስን ሳንፍሮንቲየርስና የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ አገሮችን አስተያየት ከግንዛቤ ያስገባ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የኢቦላ ምልክት ለሚታይባቸው መታከሚያ የተለየ ሆስፒታል መዘጋጀቱን፣ የኢቦላ ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ ይመራ ዘንድ ብሔራዊ ኮሚቴ ፡
መቋቋሙ ይታወሳል ፡፡