Tuesday, December 9, 2014

የታህሳስ ወር የነዳጅ ማስተካከያ ተደረገ


አዲስ አበባ፣ ህዳር 30/2007 (ዋ.ኢማ)  - ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 30/2007 የሚቆይ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ህዳር 29 ቀን 2007 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ለሚቀጥለው አንድ ወር በነዳጅ ዋጋ ላይ አንጻራዊ የዋጋ ቅናሽ የተደረገው በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ በመምጣቱ ነው ብሏል፡፡
በዚሁ ማስተካከያ መሰረት ተራ ቤንዚን በሊትር ብር 19 ከ41፣  ነጭ ናፍጣ ብር 17ከ49፣ ኬሮሲን ብር 15 ከ40 እንዲሁም ቀላል ጥቁር ናፍታ ብር 17ከ49 ሆኗል ፡፡
ከባድ ጥቁር ናፍታ በሊትር ብር 15 ከ14 ሳንቲም ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ ብር 19 ከ43 ሳንቲም መሆኑን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም 23 ቀን 2001 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በየወሩ እንዲከለስ መወሰኑ ይታወሳል።(ኢብኮ)

No comments:

Post a Comment