Tuesday, December 9, 2014

ወሲብ ለጤንነት – (ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ማንበብ የተከለከለ)

ሁላችንም ወሲብ አስደሳች እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይሁን እንጂ ለጤና ጠቃሚ ነው ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተን አናውቅ ይሆናል፡፡ መልሱ ‹እጅግ በጣም› የሚል ነው፡፡ ነዋሪነታቸውን ኒውዮርክ ከተማ ያደረጉ እና ‹‹She comes first›› በሚል መጽሐፋቸው የሚታወቁት የወሲብና ወሲብ ነክ ጉዳዮች አማካሪ አየር ኬርነር ‹‹የወሲብ ህይወታችን ጤና የአጠቃላይ ጤና ነፀብራቅ ነው›› ይላሉ፡፡
በወሲብ ዙሪያ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ባለሙያዎች ወሲብ ለራሳችን የሚኖረንን አመለካከት (Self Esteem) ከማሻሻል ጀምሮ ለውስን በሽታዎች የሚኖረንን ተጋላጭነት እስከ መቀነስ ድረሰ ብዙ ጥቅም እንደሚሰጥ ያስረዳሉ፡፡ በአንፃሩ፣ እምብዛም ወሲብ የማይፈፅሙ ከሆነ አንዳች ችግር ሊኖር ይችላል፡፡
make love
እነዚህን ችግሮች ለይቶ መፍታት አስፈላጊ ነው ይላሉ ኬርነር፡፡ ምክንያቱም የወሲብ ህይወታችን በብዙ መልኩ ከልዩ ልዩ የህይወት ክፍሎቻችን ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው፡፡ ለአብነት ያህል፣ የወሲብ ፍላጎትዎና አፈፃፀምዎ አናሳ ከሆነ ምንአልባት የድብርት ተጋላጭ ሊሆን ይችላል፣ የተመጣጠነ ምግብ አይበሉ ይሆናል፣ ውጥረት ውስጥ ይገኙ ይሆናል ወዘተ፡፡
ወሲብ ተከታዮቹን በመድሃኒት መልክ ሊገኙ የማይችሉ ጤና ነክ ጥቅሞች ያስገኛል፤-
የልብ ጤንነትን ያሻሽላል
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የብልት መጠንከር ከልብ መጠንከር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ በ2008 ዓ.ም የአሜሪካን የልብ ህክምና ጆርናል ላይ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያብራራው የብልት መቆም እና መጠንከር ችግር (Erectile Dysfunction) ከልብ ጥንካሬ ማጣት ጋር ግንኙነት አለው፡፡
ተመራማሪዎች 2300 ወንዶች ላይ ባደረጉት ምርምር መሰረት የብልት መቆም እና መጠንከር ችግር ያለባቸው ወንዶች ለልብ ህመም ያላቸው ተጋላጭነት ችግሩ ከሌለባቸው ይልቅ በ58% ከፍ ያለ ነው፡፡
ለፕሮስቴት ካንሰር የሚዳርግ ተጋላጭነት ይቀንሳል
በ2004 ዓ.ም የአሜሪካ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ጆርናል ላይ 2400 ወንዶችን አሳትፎ የተሰራና ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው በአንድ ወር ውስጥ 21 ጊዜ ወሲብ የሚያደርጉ ሰዎች በወር ውስጥ ከ4-7 ጊዜ ያህል ወሲብ ከሚያደርጉ ሰዎች ይልቅ ኋላ ላይ ለፕሮስቴት ካንሰር የሚኖራቸው ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
ለስራ ይጠቅማል
ሔለን ፌሸር የሚባሉ አንትሮፖሎጂት ወሲብ የፈጠራ አቅምን፣ ችግር የመፍታት ችሎታን እና የመግባባት ክህሎትን እንደሚያሻሽል ይገልፃሉ፡፡ ይህንን ሁሉ ነገር ሊያሻሽል የሚችልበት ዐቢይ ምክንያት ወሲብ ስንፈፅም አንጎላችን ዶፓሚን እና ኦክሲቶሲም አካ የሚሰኙ የደስታ ስሜትን የሚያጎናፅፉ ኬሚካሎችን በብዛት አምርቶ ስለሚሰራጭ ነው፡፡
የወጣትነት መልክና ቁመና ተጠብቆ እንዲቆይ ይረዳል
ስኮትላንድ ውስጥ 3500 አሜሪካውያንን እና አውሮፓዊያንን ያሳተፈ አንድ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ ጥናቱ ለአስር ዓመቶች ያህል ቢያንስ ቢያንስ ከ7-12 ዓመት ከዕድሜአቸው ይልቅ ወጣት የሚመስሉ ሰዎችን አፈላልጎ ማግኘትና የጋራ ጠባያቸውን ማጥናት ነበር፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ታስሰው ከተገኙ በኋላ ጥናቱ የእነዚህን ሰዎች የጋራ መለያ ጠባይ ምን እንደሆነ ለመረዳት እና ለመተንተን ሙከራ አድርጓል፡፡ በግንባር ቀደምትነት እነዚህን ወንዶች የሚያመሳስላቸው ነገር መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መቻላቸው ነው፡፡
ሁለተኛው የጋራ መለያ ጠባያቸው በመደበኛነት ወሲብ መፈፀም ነው፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ከ2-3 ጊዜ በሳምንት ከፍቅር ወይም ትዳር አጋራቸው ጋር ወሲብ ይፈፅማሉ፡፡
ውጥረትን ይቀንሳል
ሴቶች የእርካታ ጣሪያ ላይ ከመድረሳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ በከፊል ንቁ በከፊል ንቁ ያልሆነ ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ፡፡ በዚህ ወቅት ውጥረትን የመቀነስ እና የማርገብ ሚና የሚጫወተው የአንጎላቸው ክፍል ስራ ይጀምራል፡፡
አንጎልን ያነቃቃል
ኬርነር ‹‹የወሲብ ፍላጎት መነቃቃት የአካልና አንጎል በጋራ መነቃቃት ነው›› ይላሉ፡፡ እኚህ ባለሙያ ብዙ ጊዜ አንጎላችንን ማነቃቃት የሚችለው ሐሳብ ወሲብ ውስጥ ድርሻ ሊኖረው እንደሚገባ እንዘነጋለን ይላሉ፡፡
ኬርነር፣ ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የስሜት ህዋሳቶቻችን ወሲብ ሲፈፀም ቦታ እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡ እይታ፣ ድምፅ፣ ንክኪ፣ ጣዕም፣ እና ጠረን፡፡
ስለዚህ፣ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ወሲብ መፈፀም ብቻ ሳይሆን በተቻለ መጠን ሁሉንም የስሜት ህዋሳቶች እና ሁኔታዎች ያካተተ አይነት ወሲብ መፈፀምን ያበረታታሉ፡፡ ሐሳብን፣ አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እና ሁሉንም የስሜት ሕዋሳቶች ተሳታፊ ማድረግ፡፡
ወሲብን የሚደግፉ እና የሚያበረታቱ ጥናቶች ቁጥር ስፍር የላቸውም፡፡ ስለዚህ የወሲብ አምሮታችሁ እና አድራጎታችሁ አናሳ ከሆነ ከዚህ ልምድ ልትወጡ የምትችሉበትን ነገር ለማድረግ ሞክሩ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲብ የወሲብ ፍላጎታችሁ ማሽቆልቆል ከጀመረ ይህ ለምን ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት ሞክሩ፡፡ የሳይኮሎጂ እና የህክምና ባለሙያ እንደየችግሩ ሁኔታ እገዛ ሊያደርጉላችሁ ይችላሉ፡፡ አለበለዚያ የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ ለአካላችሁ እና አለባበሳችሁ ቦታ በመስጠት ቀላል የማይባል ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡ ኬርነር ‹‹ሰዎች ጤናማ ወሲብ ከፍቅር አልያም ትዳር አጋራቸው ጋር ማድረግ ሲችሉ ህይወታቸው ይበልጥ ይደምቃል›› ይላሉ፡፡ ክብደታቸውን ለማስተካከልና ለመቆጣጠር ይበልጥ ተነሳሽነት ውስጣቸው ይፈጠራል፣ ራሳቸውን መንከባከብ ያዘወትራሉ፣ እንደተፈቀሩ ይሰማቸዋል፣ እርካታቸው ይጨምራል፡፡ በስራ ቦታ መነጫነጭም ሆነ መጋጨት ይቀንሳሉ፡፡ በጥቅሉ ወሲብ ለሁለንተናዊ ጤና መሻሻል በብዙ መልኩ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
Source : http://www.tenaadam.com/amharic/archives/2100

No comments:

Post a Comment