Monday, September 21, 2015

ታሪክን የኋሊት

መስከረም 06፣2008
የጀርመን ናዚዎች፣ ዓለምን የመቆጣጠር ክፉ ኃሳብ ባደረባቸው ጊዜ፣ ክፉ ኃሳባቸውን ፖላንድን በመውረር አንድ ብለው ጀመሩ፡፡ አገሪቱን፣ በ20 ቀናት ሙሉ ለሙሉ፣ በመዳፋቸው አስገቧት፡፡ ፓላንዳውያን ፣አገራቸውን ከናዚዎች ወረራ ለመከላከል፣ የተቻላቸውን አደረጉ፡፡ የናዚዎች ዘመቻ፣ 16ኛ ቀኑን ባስቆጠረ ማግስት፣ ከምስራቅ አቅጣጫ፣ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ቀይ ጦር ወረራ መክፈቱ፣ ለፖላንዳውያኑ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነባቸው፡፡ ይህ ከሆነ፣ ዛሬ ልክ 76 ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡ ጀርመኖቹ ወረራ በጀመሩ በ20 ቀናቸው፤ ሶቪየቶቹ በ4 ቀናት ውጊያ ፖላንድን ተቃረጧት፡፡ ሶቪየት ህብረት፣ የፖላንድን ምስራቃዊ ግዛት የያዝኩት፣ የዩክሬንና የቤሎሩሲያን ግዛቶቼን ደህንነት ለማስጠበቅ ነው፣ የሚል ምክንያት አቀረበች፡፡
እውነታው ግን፣ ፖላንድ፣ በጀርመን ናዚዎች ልትወረር አንድ ሳምንት ሲቀራት፣ በጀርመንና በቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ በተፈራረሙት፣ ሚስጥራዊ ስምምነት መነሻ ነበር፡፡ ሚስጥራዊው ስምምነት፣ የዚያን ጊዜዎቹን የሁለቱን አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስም በመያዝ፣ በታሪክ የሪቨንትሮፕ ሞሎቶቭ ስምምነት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ስምምነቱ፣ ላይ ላዩን ያለመጠቃቃት ውለታ ቢመስልም፣ ሚስጥራዊ ክፍሉ የግዛት መሸንሰንና የተፅዕኖ ክልልን መፍጠርን የተመለከተ ነው፡፡ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት፣ የፖላንድን ምስራቃዊ ግዛት የያዘችውና ሦስቱን የባልቲክ አገሮች ኢስቶኒያ፣ላቲቪያና ሊትዌንያን ወደ ራሷ የቀላቀለችው፣ በዚሁ ሚስጥራዊ ስምምነት መነሻ ነው ይባላል፡፡ የሶቪየት ህብረትና የናዚዎቹ ያለ መጠቃቃት ውለታም ሆነ፣ ሚስጥራዊው ስምምነት፣ ብዙ ርቀት አልተጓዘም፡፡ የጀርመን ናዚዎች፣ ስምምነቱን ሶቪየት ህብረትን ለማዘናጋት ተጠቅመውበታል፡፡ ናዚዎቹ አቅማቸው መፈርጠሙ በተሰማቸው ጊዜ፣ ከሞስኮ ጋር የገቡትን ያለመጠቃቃት ውለታ አሸቀንጥረው ጣሉት፡፡ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ፣ ናዚ ጀርመን ሶቪየት ህብረትን ወረረች፡፡ ወረራው የቀድሞዋን ሶቪየት ህብረት በጦርነቱ ከተሳተፉ አገሮች ሁሉ፣ የላቀውን ዋጋ አስከፈላት፡፡ የ2ኛው የዓለም ጦርነት፣ ዋነኛዋ ቀንበር ተሸካሚ ሆነች፡፡ ሌላ ሌላው፣ ጥፋትና ውድመት፣ ወደ ጐን ቢባል እንኳ ፣ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጐቿን ሕይወት አስገብሯታል፡፡

ምንጭ:shegerfm.com

ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ፣ አለምን እየመራ ነው አዲስ አልበሙ፣ በሳምንት 412 ሺህ ኮፒ ተሽጦለታል

“ዘ ዊኪንድ” በሚል ቅፅል ስሙ የሚታወቀው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ፣ ባለፈው ሳምንት በአለም ደረጃ በቢልቦርድ ምርጥ አልበሞችሰንጠረዥ የ1ኛነትን ደረጃ በዚህ ሳምንትም አለምን እየመራ ይቀጥላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘገበ፡፡“ቢዩቲ ቢሃይንድ ዘ ማድነስ” የተሰኘው አዲሱ የአቤል አልበም፣ ለገበያ በቀረበበት የመጀመሪያው ሳምንት በሽያጭ ብዛት መሪነቱን እንደሚይዝ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም፣ ከተገመተው በላይ እንደተሳካለት ፎርብስ ዘግቧል፡፡ በ350 ሺህ የአልበም ሽያጭ አንደኛ እንደሚሆን የተገመተው የአቤል አልበም፣በ412 ሺህ ያህል ተቸብችቧል፡፡ በአዲሱ አልበሙ ውስጥ የተካተቱት 12 ሙዚቃዎችም በያዝነው ሳምንት የቢልቦርድ 50 ምርጥ ሙዚቃዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል፡፡ካለፉት ሰባት አመታት ወዲህ፣ በቢልቦርድ የምርጥ ዘፈኖች ሰንጠረዥ፣ በአንድሳምንት ሁለት ዘፈኖቹ፣ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ባለው ደረጃ ውስጥየተካተቱለት የመጀመሪያው ወንድ ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ ብቻ መሆኑን ቢል ቦርድ ገልጿል የሰሞኑን የአቤል ስኬት ሲዘግብም፤ በ57 አመታት የቢልቦርድ ሰንጠረዥ ታሪክ፣ አቤል በአንድ ሳምንት ውስጥ ብዙ ዘፈኖቹ፣ በምርጥ 100 ዘፈኖች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱለት ስድስተኛው ድምጻዊ ነው ብሏል፡፡ ዘንድሮ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ፣ ከአቤል የአልበም ሽያጭ የሚበልጥ ሪከርድ ያስመዘገበ ድምፃዊ የለም ከድሬክ በስተቀር፡፡ አመቱ የአቤል ተስፋዬ ነው ያለው ፎርብስ መጽሄት፤ የድምጻዊው የሙዚቃ ስራዎች የካናዳንና የአሜሪካን ሬዲዮ ጣቢዎች በስፋት መቆጣጠራቸውንና ከፍተኛ ተወዳጅነት ማትረፋቸውን ዘግቧል፡፡ የአቤል ዘፈን በአሜሪካ ሬዲዮ ጣቢያዎች በብዛት በመሰራጨት አቻ አልተገኘላትም፡፡ “ስድ” ቃላትን በሙዚቃዎቹ ውስጥ ይደጋግማል በሚል ትችት የሚሰነዘርበት አቤል ተስፋዬ፤ በሙዚቃዎቹ ኢትዮጵያዊኛ ቃና ይንፀባረቃል የሚለው አስተያየት ከሁሉም በላይ እንደሚያስደስተው ገልጿል፡፡ በዘፈን መሃልም አልፎ አልፎ አማርኛ ያስገባል፡፡

Friday, September 4, 2015

Your brand new phone could still have malware



A new phone is supposed to be a clean slate. But alarmingly, that's not always the case.
Security company G Data has identified more than 20 mobile phones that have malware installed despite being marketed as new, according to a research report. And it doesn't appear the infection is occurring during manufacturing.
"Somebody is unlocking the phone and putting the malware on there and relocking the phone," said Andy Hayter, security evangelist for G Data.
Many of the suspect phones are sold in Asia and Europe through third parties or middleman and aren't coming directly from the manufacturers, Hayter said.
Brands of affected phones include Xiaomi, Huawei, Lenovo, Alps, ConCorde, DJC, Sesonn and Xido.
G Data has contacted some manufacturers, including Lenovo, whose S860 Android smartphone in one instance was found to have the malware.
Ray Gorman, Lenovo's executive director of external communications, wrote in an email that the device G Data analyzed came from a third-party marketplace. The malware was installed by middlemen, he wrote.
"This is the only such occurrence we have been made aware of," Gorman wrote. "We always recommend customers transact with authorized distribution channels and only accept merchandise that comes in an official box with original factory seals."
The malware is embedded in a legitimate app, such as Facebook, which is sometimes preinstalled on phones, Hayter said. It can read and send text messages, install other apps, collect and change call data, grab location information, record phone calls or send premium SMSes, according to G Data's report.
It's impossible for consumers to remove since it resides inside the phone's firmware.
"You can't take it off there unless you unlock the phone," Hayter said.
G Data was alerted to the problem after receiving support calls from users who said a file had been quarantined but that it couldn't be removed.
The problem has been around for a while. In June 2014, G Data said it found malware in the firmware of a relatively inexpensive Android device made by the Chinese manufacturer Star.
The company's analysts bought Star's N9500 and found malware that purported to be an app for Google's Play Store. The malware, they found, could not be deleted.
In early 2014, Marble Security found malware embedded within Netflix's app that had been preinstalled on six mobile devices made by Samsung Electronics.
That malware grabbed credit card information and passwords and sent it to a server in Russia.

Thursday, August 27, 2015

High-Tech 'Smart' Cane Helps Blind People Recognize Faces


A new, high-tech cane for the blind is designed to recognize the faces of the person's friends and family members.
Using smartphone technology, the device — known as the "XploR" mobility cane — can identify faces from up to about 33 feet (10 meters) away, researchers say.
If the cane recognizes someone, it alerts a visually impaired user by vibrating and transmitting a sound signal. The cane is also equipped with GPS to help the user navigate. [Bionic Humans: Top 10 Technologies]

"My grandfather is blindand I know how useful this device could be for him," Steve Adigbo, one of the cane's developers and a student at Birmingham City University in England, said in a statement, adding,"There’s nothing else out there like this at the moment."
The cane works by taking pictures of people in the environment and comparing them to a bank of images stored on an internal memory card, using facial-recognition software. When it finds a match, it produces a vibration and sends a signal to an earpiece via Bluetooth, the researchers said.
The team conducted market research at the Beacon Centre for the Blind in the British town of Wolverhampton, and found that in addition to high-tech features, the cane needed to be lightweight and easy to use.
The researchers have already presented the cane to medical professionals and scientists in Luxembourg and France, and plan to take their device to Germany later this year. They also plan to return to Beacon to test the product and show off its training and security features.
Meanwhile, American researchers have been developing a vibrating vest that uses a variety of sensors to help blind people navigate. The device, dubbed Eyeronman and developed by New York-based company Tactile Navigation Tools, could also help soldiers, firefighters and others in poor visual conditions, researchers say.

Wednesday, July 15, 2015

ተዋናይት-ቤዛዊት-መስፍን-በእስራት-ተቀጣች

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 8፣ 2007 (ኤፍ. ቢ. ሲ) በተለያዩ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመተወን የምትታወቀው ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን እና ግብረ አበሯ በእስራት ተቀጡ።
በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራንዮ ነዋሪ የሆኑት ተከሳሾቹ በእስራት የተቀጡት ከታዘዘላቸው ውጭ ተጨማሪ ገንዘብ ከባንክ ቤት በማውጣት ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ነው።
የ22 አመቷ ተዋናይት ከግብረ አበሯ ጋር በመሆን በተሰጣቸው የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት ለፊቱ ሁለት ቁጥርን በመጨመር ያልተፈቀደላቸውን 24 ሺህ ብር ከወጋገን ባንክ ሰባራ ባቡር ቅርንጫፍ አውጥተዋል።
ተከሳሾቹ ለአቶ ዮናታን ባልቻ መኪና በማከራየት የኪራይ ስምምነት ውል ያላቸው ሲሆን፥ በውላቸው መሰረትም ሚያዚያ 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ የ4 ሺህ ብር ቼክ ተቀብለዋል።
ግለሰቦቹ ሚያዚያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ላይም ከመኪና ተከራዩ አቶ ዮናታን በተቀበሉት የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት ለፊቱ 2 ቁጥርን በመጨመር ተጨማሪ 20 ሺህ ብር ከባንክ ቤቱ አውጥተዋል።
በዚህም መሰረት የፌደራሉ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ የማይገባቸውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ በፈፀሙት ወንጀል ክስ በመመስረት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል ችሎትም ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ ብሏቸዋል ።
ተከሳሾቹ ወንጀሉን በስምምነት በማበር የፈፀሙት በመሆኑ ቅጣቱ ከፍ ብሎ እንዲወሰን አቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ አቅርቧል።  
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተከሳሾቹ ያላቸውን የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ቤዛዊት መስፍን የዕድሜዋን ወጣትነት፣ ከዚህ ቀደም በምንም አይነት የወንጀል ድርጊት አለመሳተፏንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኗን በቅጣት ማቅለያነት አቅርባለች።
2ኛ ተከሳሽ አቶ ነቢል ይማም ምንም አይነት የቅጣት ማቅለያዎችን አላቀረበም።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል ችሎትም 1ኛ ተከሳሽን በ6 ወር ቀላል እስራትና በ1 ሺህ 500 ብር እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽን በ1 አመት ከ6 ወር እና በ3 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።
ምንጭ:— FBC

Thursday, July 9, 2015

የእኛን የልማት ጉዞ

"…የእኛን የልማት ጉዞ ከተራራ ላይ በፍጥነት ከሚወርድና በየደቂቃው ፍጥነት እየጨመረ ከሚጓዝ ናዳ አምልጦ ወደ ጠንካራ ከለላ ለመጠጋት ከሚሮጥ ሰው ጋር ማመሳሰል ይቻላል፡፡ ይህ ሰው ከለላው ያለበትን አቅጣጫ አውቆ ወደዚያ የሚያመራ አቋራጭ መንገድ ይዞ ካልተጓዘ በስተቀር በናዳው እንደሚዳፈን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ከዚህ አኳያ ቀና አቅጣጫ ተይዞም ቢሆን ሰውየው ከናዳው ፍጥነት በላይ መሮጥ ካላተቻለ ባለበትም ቢቀር፣ወደ መጠለያው ለመግባት አንድ እርምጃ ሲቀረውም ቢቀበር ለውጥ የለውም፡፡ ዞሮ ዞሮ በፍጥነት ችግር ምክንያት መሞቱ አልቀረም፡፡ በሌላ አነጋገገር የፍጥነትም ጉዳይ ከየእጣጫው ባላነሰ መንገድ የህልውና ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡ የሆነ ፍጥነትም ሳይሆን አደጋው እየተጓዘበት ካለው ፍጥነት ወሳኝ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡ እኛም ያለንበት ሁኔታ ቀና መንገድ ይዘን፣ ከአደጋው ለማምለጥ የሚያስችል ብቃት ያለው ፍጥነት ስለሌን በእርግጠኝነት የምንሸነፍበት አደጋ እየተከሰተ ነው፡፡ ስለዚህ ሀገራችንን፣ መንግስታችንና ድርጅታችንን ሊበታትን ከሚችለው ናዳ እጅግ በላቀ ሁኔታ መፍጠን ይገባናል፡፡…"ታላቁ መሪ ጓድ መለስ ዜናዊ በፍጥነት ስለማደግ አስመልክተው በአንድ ወቅት ካቀረቡት ትንታኔ የተወሰደ፡፡