የዘንድሮው
የምርጫ ሂደት በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ መገኘቱ ከበፊቶቹ የምርጫ ሂደቶች ከፍተኛ የሆነ ትምህርት በመወሰዱ
ነው ያሉት የቀድሞ የኢዴፓ ፕሬዝደንት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው ሲሆኑ
ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም እንደገለፁት ህዝቡ በተለያየ ጊዜ የሚፈልገውን ፓርቲ መምረጥ መቻሉ እና መብቱን በአግባቡ
መጠቀሙ አንዱ የዴሞክራሲ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡ የምርጫ ስርዓት ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው፤ ይህም
ለእድገታችን ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አለውም ሲሉ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ምርጫ ማለት የሀሳብ ልዩነቶችን ለውድድር የምናቀርብበት እንጂ አላስፈላጊ የሆነ ችግር ውስጥ የምንገባበት ሊሆን አይገባም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
source :ZAMI RADIO
No comments:
Post a Comment