"…የእኛን
የልማት ጉዞ ከተራራ ላይ በፍጥነት ከሚወርድና በየደቂቃው ፍጥነት እየጨመረ ከሚጓዝ ናዳ አምልጦ ወደ ጠንካራ ከለላ
ለመጠጋት ከሚሮጥ ሰው ጋር ማመሳሰል ይቻላል፡፡ ይህ ሰው ከለላው ያለበትን አቅጣጫ አውቆ ወደዚያ የሚያመራ አቋራጭ
መንገድ ይዞ ካልተጓዘ በስተቀር በናዳው እንደሚዳፈን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ከዚህ አኳያ ቀና አቅጣጫ ተይዞም
ቢሆን ሰውየው ከናዳው ፍጥነት በላይ መሮጥ ካላተቻለ ባለበትም ቢቀር፣ወደ መጠለያው ለመግባት አንድ እርምጃ ሲቀረውም
ቢቀበር ለውጥ የለውም፡፡ ዞሮ ዞሮ በፍጥነት ችግር ምክንያት መሞቱ አልቀረም፡፡ በሌላ አነጋገገር የፍጥነትም
ጉዳይ ከየእጣጫው ባላነሰ መንገድ የህልውና ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡ የሆነ ፍጥነትም ሳይሆን አደጋው እየተጓዘበት
ካለው ፍጥነት ወሳኝ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡ እኛም ያለንበት ሁኔታ ቀና መንገድ ይዘን፣ ከአደጋው ለማምለጥ
የሚያስችል ብቃት ያለው ፍጥነት ስለሌን በእርግጠኝነት የምንሸነፍበት አደጋ እየተከሰተ ነው፡፡ ስለዚህ ሀገራችንን፣
መንግስታችንና ድርጅታችንን ሊበታትን ከሚችለው ናዳ እጅግ በላቀ ሁኔታ መፍጠን ይገባናል፡፡…"ታላቁ መሪ ጓድ መለስ
ዜናዊ በፍጥነት ስለማደግ አስመልክተው በአንድ ወቅት ካቀረቡት ትንታኔ የተወሰደ፡፡
No comments:
Post a Comment