1. እንክብካቤ አብዛበት
የትኛዋም ሴት ብትሆን ከወንድ ልጅ የሚደረግላትን እንክብካቤ አትጠላውም፡፡ ዓይን አፋር ሴት ደግሞ በማፈሯ የተነሳ ከብዙ ሰዎች የመራቅ ዝንባሌዋ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ አንተ ፍፁም የሆነ እንክብካቤ ልታደርግላት ይገባል፡፡ እንክብካቤ እያደረክላት ስትመጣ ለካ ወንድ ልጅ እንዲህ ያስብልኛል ልትል ሁሉ ትችላለች፡፡ በዚህም የመጀመሪያውን ጥያቄ በውስጧ ማሰላሰል ትጀምራለች፡፡ ይህ ደግሞ በቀጣይነት ለምታደርገው ነገሮችህ የልቤን መንገድ አስቀድመህ የምታንኳኳበት ይሆናል፡፡ ስለ እሷ ባሰብክና በተጨነቅላት ቁጥር ምንም ይሁን ምን ስለአንተ ሁኔታ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ የፍቅርን ምንነት በአንተ እንክብካቤ መነሻነት እንድታውቀው ያስገድዳታል፡፡ ስለዚህም አንተን ፈጽሞ የማትለይበት አይነት እንክብካቤ አድርግላት፡፡
2. ስለ ሌሎች ሰዎች የፍቅር ህይወት አጫውታት
ዓይን አፋር ሴት ራሷን ከብዙ ነገር እንደማራቋ መጠን ከፍቅር ጋር ያላት ግንዛቤም የቀነሰና ጥሩ አመለካከት ላይኖራት ስለሚችል ስለ ፍቅር ምንነት በቀልድና በጨዋታ እያዋዛህ ለማሳወቅ ሞክር፡፡ በተለይም ነጻና ዘና የምትልበትን ጊዜ ጠብቀህ የተለያዩ ሰዎችን የፍቅር ታሪክና አስደሳች የፍቅር ህይወታቸውን አጫውታት፡፡ እዚህ ጋር በቃ አንተ ፍፁም የፍቅር አስተማሪዋ እንደሆንክ መንገዶችን አመቻች፡፡ ከዚህ በፊት የነበራትንም ህይወት ለማወቅ በቀስታ እያወጣጣሀት ታሪኳን ለማወቅ ሞክር፡፡
3. ደስ የሚል ጊዜን አብራችሁ ለማሳለፍ ሞክር
የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ወጣ ባለ መልኩ ከእሷ ጋር መዝናናትና መደሰትን ተግብረው፡፡ በእያንዳንዷ አስደሳች የመዝናኛ ሰዓቶቹ አንተ አፍ አውጥተህ ከምትናገረው ይልቅ የውስጥህን ምኞት ነገሮችህና እንቅስቃሴዎችህ እንዲያሳውቃት አድርግ፡፡ አስደሳች ጊዜን እያሳለፋችሁ ስትመጡ ዓይን አፋርነቷን እየተወችው ስለ አንተ ፍቅር አቀራረብ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ ስለዚህም ባገኘኸው አጋጣሚ ይህን ለመተግበር የእሷን አመቺ ጊዜ ልትጠብቅ ይገባሃል፡፡
4. የሚያስደምሙ ስጦታዎችን አበርክትላት
ከአንተ ጋር ያለች ሴት ዓይን አፋርና ለወንድ ልጅ በፍቅር በቀላሉ የማትሸነፍ ከሆነች በጣም የሚማርኩ ስጦታዎችን በተለይም የተለያዩ በዓላትንና የልደቷ ቀንን ጠብቀህ ስጣት፡፡ ስጦታዎችህ በራሳቸው የውስጥህን ፍላጎት የሚናገሩልህ አድርገህ ምረጣቸው፡፡ ስትመርጣቸው ግን የእሷንም ፍላጎት የጠበቀና በጣም ሊያስደስታትና በመደምም ሌላ ነገር እንድታስብ የሚያደርጋት ይሁን፡፡ ታዲያ ስጦታዎችህን መሳሪያ አድርገህ በውለታ ፍቅሯን ለማግኘት እንዳይሆን ተጠንቀቅ፡፡ ይልቁንስ ስጦታዎችህ የውስጥህን ስሜትና ፍላጎት ከማሳወቅና የመልካም ነገር አቅርቦትህ ብቻ እንዲሆኑ ልታውቅም ልታሳውቃትም ይገባል፡፡ ያኔ የአንተን ማንነት የበለጠ ትረዳለች፡፡ ሳትወድ በግዷም ዓይን አፋርነቷ የበለጠ ሊጎዳት ስለሚችል ያንተን ዕድል ልታሳልፍ አትችልም፡፡
5. የጓደኛነት አቀራረብህን ቀይርባት
እሷን ከማወቅህ ጀምሮ ያሉ አቀራረቦችህን የጓደኝነት ወይም ደግሞ የወንድምነት መምሰሉ እየበዛ ሲመጣ አንተን እየጎዳህ ስለሚመጣ ጊዜውንና አመቺ ሁኔታዎችን አይተህ ወደ ፍቅር ፈላጊነት ራስህን ልትቀይርበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ከአንተ ስለ ፍቅር ምንነት እንደዚሁ በመቅረብህ ብቻ እያገኘች እንጂ በአንተ ልብ ውስጥ ፍቅር መፈለጓን በደንብ ላትገነዘበው ትችላለች፡፡ ምክንያቱም የዓይን አፋር ሴቶች መገለጫ ነውና፡፡ ልቧን በማትጠብቀው ሁኔታ ፍፁም በፍቅር አስደንብረው፡፡ በፍቅር የደነበረ ልብ ደግሞ ልጓሙና መያዣው በአንተ እጅ ውስጥ እንዲሆን አድርገው፡፡
6. ፍፁም አማላይ ሁንባት
የተለያዩ የፍቅር መግቢያ ቴክኒኮችን እየተጠቀምክ በመጣህ ቁጥር አንተ የፍቅር አማላይነትም አብሮ የሚታይ ነው፡፡ ነገር ግን ራሱን በቻለ መልኩ አማላይነትህ በየጊዜው እንዲታያት አድርግ፡፡ የፈለገ ዓይን አፋር ብትሆንም እንኳን የአንተ የአማላይነት አቀራረብህ ውስጡን ሊገዛው ይችላል፡፡ አንተ ያለምንም ፍራቻ በቀረበችህ ሰዓት ደባብሳት፣ እጇን ጭምቅ እያደረግክ ያዛት፣ አሳሳሞችህ ደስ የሚላትና የምትናፍቀው አይነት አድርግባት፣ እያቀፍካት ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ እየሳምካት ፍቅር ውስጥ ክተታት፡፡ ነገር ግን አሁንም የዓይን አፋርነቷ ባህሪይ ስለሚታወሳት ፀባይዋ ሊለዋወጥ ስለሚችል ሰው በተሰበሰበበት ልትስማትም ሆነ ልታቅፋት አትሞክር፡፡ ቀስ በቀስ ግን የምታደርጉት ነገር ምንም እንዳልሆነ በራስ መተማመንም እንድታዳብር አድርጋት፡፡ ይህን መፈፀም ከቻልክ ልቧ ውስጥ ትልቅ ፍቅር ማስቀመጥ ተችላለህ፡፡
7. በፍቅርህ ክንፍ እንድትል አድርግ
ከላይ ያሉትን ሁሉ ከተገበርካቸው አንተ በቃ የፍቅር ሰው ነህና ፍቅር መስጠት ተችላለህ፡፡ ታዲያ ፍቅርህን ስትሰጣት እሷንም በአንት ፍቅር ክንፍ እንድትል አድርጋት፡፡ በፍቅር የነካካኸውና የቆሰቆስከውን ልቧን መጋረጃና ማረፊያው አንተው ጋር እንዲሆን አድርግክ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ታዲያ የምን ማፈር ማለት ትጀምራለች፡፡ ምክንያቱም በአንተ የፍቅር ሰው መሆን አይን አፋርነቷን ገልጠህላታልና አንተ የእኔ ‹‹የፍቅር ላምባዲናዬ›› ነህ ማለት ትጀምራለች፡፡ ከዚህ በኋላ ድንቅ የፍቅር ሽሚያ ውስጥ ታስገባትና እሷው ፍቅር ላስተምርህ ሁሉ ማለት ትጀምራለች፡፡ ፍቅራችሁም በምሽት እንደጨረቃና ከዋክብት በቀን ደግሞ እንደ ፀሐይ እየበራ ይታያቸዋል፡፡ መልካም ፍቅር

No comments:
Post a Comment