መሳሳም
የሁለት ሰዎች ፍቅር መገለጫ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሁለት ፍቅረኛሞችን የበለጠ ያጣምራል፡፡ መሳሳም
ጥልቅ ፍቅራዊ፣ ሀይል ያለው፣ ወይም የሰላምታ መግለጫ ሊሆን ይችላል፡፡ በአማካይ አንድ ሰው በህይወቱ 20,000
ደቂቃዎችን በመሳሳም ያሳልፋል፡፡ ይህ ማለት ወደ ሁለት ሳምንት ይጠጋል፡፡ ይህን ያህል ሰዓት በመሳሳም ለማሳለፍ
የሆነ ምክንያት መኖር አለበት፡፡ እርግጥ ነው፤ ከመሳሳም በስተጀርባ ያለ ሳይንሳዊ ምክንያት አለ፡፡ ይህ ከመሳሳም
ጀርባ ያለው ሳይንስ በፍቅር ወቅት ብዙ ጊዜ ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡ ነገር ግን ይበልጥ እንድንሳሳም የሚያደርገን
ይህ ሳይንስ ነው፡፡
የመሳሳም
ሳይንሳዊ ጥናት Philematology በመባል ይታወቃል፡፡ የማንኛውም ሰው ከንፈርና ምላስ በነርቮች የተሞሉ
ስለሆኑ በመሳሳም ወቅት አዕምሮአችን የተለየ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም በምንሳሳምበት ጊዜ ሰላሳ
አራት የፊት ጡንቻዎችን እንጠቀማለን፡፡
ለምን እንሳሳማለን? (Why do we kiss?)
እኛ
ለመሳሳማችን የማህበረሰብና የዝግመተ- ለውጥ (evolution) አስተዋጾ ከፍተኛ ነው፡፡ የእኛ የመሳሳም ፍላጎት
ከማህበረሰቡ ሊመነጭ የቻለው በሰዎች መካከል በሚፈጠር መቀራረብ ነው፡፡ ከማህበረሰብ ብዙ የምንማራቸው ነገሮች
እንዳሉ ሁሉ በተለያዩ ማህበረሰቦች መሳሳም የፍቅር መግለጫ ሆኖ ስለሚታይ ይህንን ከአካባቢያችን እንማራለን፡፡ ይህ
በሌሎች ማህበረሰባዊ አጥቢ እንስሳቶች ላይም ይታያል፡፡ ለመቀራረብ የምናሳየው ፍላጎት እናትና ልጅን እንደሚያገናኘው
የሆርሞንና የኒውሮን የጥምረት መሠረት የተገነባ ነው፡፡
በዝግመተ-ለውጥ
በኩል ስንመጣ ደግሞ ጦጣና የጦጣ ዘሮች ለምሳሌ ልጆቻቸውን በመሳም ምግብ በአፋቸው ያቀብሏቸዋል፡፡ ይህ ድርጊት
ከዘመን ዘመን እንደፍቅር መግለጫ ተስፋፍቶ በሰዎች ላይ ተፅእኖ ያሳደረ ነው፡፡
ዋነኛውና
ቀላሉ ምክንያት ደግሞ በመሳሳም ወቅት የሚፈጠረው ጥሩ ስሜት ነው፡፡ በምንሳሳምበት ወቅት ከአስራ ሁለቱ የአዕምሮ
ነርቮች አምስቱ ተሳታፊ ናቸው፡፡ ይህ ስሜት በኑሮአችን እርካታን ስለሚፈጥርልን ይበልጥ እንድንሳሳም ያደርገናል፡፡
ሌላው
የመሳሳም ምክንያት ሊሆን የሚችለው ደግሞ የተቃራኒ ፆታን የበሽታ መከላከያ አቅም (Immune system)
መገምገም ስለሚያስችላቸው ነው፡፡ የሚያፈሩት ልጆች ጠንካራ እንዲሆኑ የበለጠ ጠንካራ የበሽታ መከላከያ አቅም
ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ሴቶች ሳያውቁት የጓደኛቸውን የአቅም ተስማሚነት የመገምገም ችሎታ አላቸው፡፡
በመሳሳም ወቅት፡
- የልብ ትርታ እና የደም ግፊት ይጨምራል
- ትንፋሽ ይጨምራል
- ጉንጫችን እና ፊታችን ይቀላል
- የአይን ቀዳዳ ይለጠጣል
- አዕምሮ ዘና ይላል
መሳሳምና ጥቅሙ (Benefits of Kissing)
መሳሳም
የደስታ ምንጭ የሚሆኑ ኬሚካሎችን ያመነጫል፡፡ Dopamine (ዶፓሚን) አንዱ ኬሚካል ነው፡፡ ይህ ኬሚካል አዕምሮ
ውስጥ የሚመነጭ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ ከመሳሳም ሌላ በአደንዛዥ ዕፆችና በመብላት
ይህ ኬሚካል ሊመነጭ ይችላል፡፡ በዚህ ደስታ ምክንያት ሰዎች መሳሳምን ያዘወትራሉ፡፡
መሳሳም
በትዳርም ሆነ በጓደኝነት ወቅት አስፈላጊ ነው፡፡ ሰዎችን የበለጠ ያቀራርባል፡፡ ኢንዶርፊን (endorphin)
የተባለውን ሆርሞን በማመንጨት በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ደስተኛ እንድንሆን ይረዳል፡፡ የሰውነታችንን ቀመር
ወዲያውኑ ይቀይረዋል፡፡ ሁለቱም አጋሮች በዚህ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ከሆኑ ሰውነታችን ኢንዶርፊን (endorphin)
እያመነጨ የበለጠ ደስተኛና የበለጠ እንዲቀራረቡ ያደርጋል፡፡
በተጨማሪም
መሳሳም ኦክሲቶሲን (Oxytocin) የተባለውን ሆርሞን በማመንጨት ይታወቃል፡፡ ይህ ሆርሞን ‹‹የፍቅር ሆርሞን››
እየተባለ በተለምዶ ይጠራል፡፡ በፍቅረኛሞች መካከል ፍቅርን እያጧጧፈ አብረው እንዲቆዩ ያግዛቸዋል፡፡
በ2009
የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው መሳሳም ለሴቶች Cytomegalovirus ከተባለው ቫይረስ የመከላከያ አቅም
ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ በሰው ልጅ ምራቅ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ቫይረሱ ጎጂ ባይሆንም በእርግዝና ወቅት ግን ያልተወለዱ
ህፃናትን ሊገድልና የተለያዩ የአዕምሮ ችግሮችን ሊያስከትልባቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ቫይረስ ከበፊቱ ከሴቷ
ጋር ከተዋወቀ የመከላከያ አቅም ስለምታዳብር ምንም አይነት ችግር በፅንሱ ላይ አይደርስበትም፡፡
መሳሳም በደቂቃ እስከ 6 ካሎሪ ያቃጥላል፡፡ ይህም ማለት በአንድ ሰዓት ቢሰላ ከአንድ ሰዓት ሩጫ የምናጠፋው የበለጠ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል፡፡
የበሽታ
መከላከያ አቅም በመሳሳም ልናዳብር እንችላለን፡፡ እርግጥ ነው በአፍ ውስጥ የተለያዩ ባክቴሪያዎች ይገኛሉ፡፡
በዚህም በሽታ ልናመጣ እንችላለን፡፡ ነገር ግን ከመሳሳም ይልቅ እጅ በመጨባበጥ የበለጠ በሽታ ልናተርፍ
እንችላለን፡፡ ስለዚህ ተገቢውን የአፍ ፅዳት አድርገን ከተሳሳምን ምንም አይነት ችግር አይመጣም፡፡
የመሳሳምና ባህል (Kissing and Culture)
አንድ
ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ቢኖር መሳሳም በሁሉም ባህል አንድ አይነት እንዳልሆነ ነው፡፡ እንዲያውም መሳሳምን
የማይፈቅዱና የማይተገብሩ ብዙ ባህሎች አሉ፡፡ ይህም ማለት መሳሳም በማህበረሰቡ ተፅእኖ ሊያድርበት የሚችልና
በትምህርት ልናገኘው የምንችለው ነገር መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ምንም እንኳን ተፈጥሮአዊ የመሳሳም ፍላጎት ቢኖረንም
ባህሉ ካልፈቀደ አንተገብረውም፡፡
Source : http://www.wanawtenanew.com/
No comments:
Post a Comment